
የወሎን አርሶ አደር የአንበጣ መንጋ ከጋረጠበት አደጋ እንታደገው!
Donation protected
በወሎ በተከሰተው የአንበጣ መንጋ እስካሁን በደረሰው ጉዳት ብቻ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ አርሶ አደር አዲስ ምርት በሚጠብቅበት በዚህ ወቅት ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጧል፡፡
በእነዚህ አካባቢዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የማይቀርብ ከሆነም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ማኅበረሰቡ ለስደትና ለረሀብ እንደሚጋለጥ የወሎ ኀብረት በአካል በመገኘት ባደረገው ግምገማም አረጋግጧል፡፡ በሌላ በኩል የአንበጣ መንጋውን የመከላከል እንቅስቃሴን ለማስተባበር፣ የኬሚካልና የመርጫ መሣሪያዎችን ለማቅረብ እንዲሁም የመረጃ ልውውጥን ለማሳለጥ ከፍተኛ የሀብት እጥረት አለ፡፡ በመሆኑም የወሎ ኅብረት በዚህ ረገድ እያከናወናቸው ያሉና በዕቅድ የያዛቸውን ሥራዎች ለማገዝ የምትወዱ ወሎየዎች/የወሎ ወዳጆች ኢትዮጵያውያን እርዳታችሁን በመለገስ ለገራገሩና ከደጉ የወሎ አርሶ አደር ዘንድ እንድትቆሙ እንጠይቃለን፡፡
አገር ቤት ለምትገኙ፣ ድጋፋችሁን በሚከተሉት የባንክ አካውንቶች ማስገባት ትችላላችሁ:
***********//*************
Organizer and beneficiary
Wollo Alliance
Organizer
Washington D.C., DC
Abel Shiferaw
Beneficiary