
Hayemanot Abebe Mekonne (ሃይማኖት አበበ መኮንን)
Donation protected


ወ/ት ሃይማኖት መኮንን ትባላለች በዴንቨርና በላስ ቬጋስ ከተማ ለብዙ ዓመታት ስትኖር ቆይታለች። በደ/ም/ቅ/ሚ/ካ ቤ/ክ ዘማሪና አገልጋይ ነበረች። ይህች እህታችን ሰው ሳትለይና ሳትመርጥ ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ቀድማ ደራሽ እና የጎደለ ጓዳችንን የምትሞላ እህታችን ነበረች። ይህች እህታችን ወደ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት ባጋጠማት ሕመም ምክን ያት ለ4ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆናለች። እግዚአብሔር ስለረዳን ከበፊት ጀምሮ በነበረችበት አስቸጋሪ ቦታ በማስታመምና ወጪዎችንም በመሸፈን ጥቂት ወዳጆቿ ባደረግነው ከፍተኛ ጥረት ወደ ጎንደር በማስመጣት በሆስፒታል ተኝታ እንድትታከም በማድረግ ላይ ነን። አሁን ግን ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ቀጥሎም ወደ ላስ ቬጋስ እንድትመጣ፣ የተሻለ ሕክምና እንድታገኝና ወደ ቀደመ መልካም ሕይወቷ እንድትመለስ የሁላችንንም የእርዳታ እጆች ትጠብቃለች ።
ስለዚህ በአቶ ዳንኤል ቸኮል አማካኝነት በከፈትነው የጎፈንድሚ የገንዘብ ማሰባሰቢያ በኩል የየአቅማችሁን በመለገስ ለሰዎች ሁሉ ደራሽና አጉራሽ የሆነች እህታችንን ሕይወት እንታደግ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም የእርዳታ እጆቻችሁን ትዘርጉላት ዘንድ ይህንንም መልዕክት ታስተላልፉልን ዘንድ በትሕትና እንጠይቃለን። የማቴ.ወ. 25፥ 35-45
ማሳሰቢያ፦ እርዳታዎን በሚለግሱበት ጊዜ የጎፈንድሚ ገፅ የሚጠይቅዎት ተጨማሪ ችሮታ (TIP) ወደ ተጎጂዋ እህታችን መዋጮ ውስጥ ስለማይገባ (TIP) የሚለው ላይ (OTHER ) የሚለውን ከመረጡ በኋላ በቲፑ ሳጥን ውስጥ ዜሮ (00) ይምሉ። በመቀጠልም የሚረዱትን የገንዘብ መጠን በዕርዳታ መስጫ ሳጥን ውስጥ ብቻ ይምሉ።
ለተጨማሪ መረጃ አቶ ዳንኤል ቸኮል [phone redacted] ይደውሉ
እናመሰግናለን።
Organizer
Daniel Chekol
Organizer
Las Vegas, NV