Main fundraiser photo

የወገን ደራሽ ወገን ነው

Donation protected

የወገን ደራሽ ወገን ወገን ነው!

አርቲስት መላኩ ቢረዳ በጠና ታሟል። አርቲስት መላኩ ቢረዳ አሁን በስልጣን ያለውን ስርዓት በቃወም "ወያኔ" የሚል የጉራግኛ ዘፈን በመዝፈኑ ምክንያት ብዙ እንግልትና ድብደባ ደርሶበት፣ ሀብትና ንብረቱ ተዘርፎ ከአገር እንዲወጣ መገደዱ የሚታወቅ ነው። አርቲስቱ በደረሰበት ድብደባ እጁ ከመሰበሩም አልፎ ብዙ የጤና እክሎች እንዲደርስበት ምክንያት ሆኗል። አሁን ላይ በተሰደደበት አገር በጠና ታሞ ህክምናውን በመከታተል ላይ ነው። ህክምናው ከባድ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ የሁላችንም እርዳታ ይፈልጋል። አርቲስት መላኩ ቢረዳ ከአገር ከተሰደደበት ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ ማንንም ላለማስጀገርና የሰው ፊት ላለመቅረብ ህክምናውን በራሱ ወጪ እየሸፈነ ሲታከም ቆይቷል። ዛሬ ሁላችንም አለንልህ ልንለው ይገባናል።

አርቲስት መላኩ ቢረዳ ከአገር ከመሰደዱ በፊት "ትዊስት በጉራግኛ"፤ "ሟን ተሟን ያርስ" ና "ወያኔ/ተሳንዴ ጉራጌ" የተሰኙ ሶስት አልበሞች ለህዝብ በማቅረብ ከሦስቱም አልበሞች የሚገኘው ገቢ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሆን አበርክቷል። ከአገር ከተሰደደም በኋላ ድምፃ አልባ ለሆነው ህዝባችን በማህበራዊ ድረ-ገፅና በሌሎች ሚዲያዎች ድምፁን ሲያሰማ ቆይቷል። የዚህን ሰው ወዳድ፣ አክባሪ፣ አዛኝና ታጋይ ወንድማችን ጤና ይመለስ ዘንድ ሁላችንም የበኩላችን እንድናደርግ ጥሪያችን እናቀርባለን።

ጓደኞቹ

Organizer

Seyoum Workneh
Organizer
Dallas, TX

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.