Main fundraiser photo

ዓለም አቀፍ ጥምረት ለጣና ሐይቅ ጤንነት

ጣናን የመታደግ ዓለማቀፍ ጥሪ - ጤና ለጣና፤ ያለ ልዩነት ለጣና ጤንነት!

ጣና ሐይቅ በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ሲሆን በዉስጡም በያዘዉ ዕምቅ ሥነ ህይዎታዊ ብዝሃነት፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ምክንያት የዓለም ቅርስ እና  የብዝሃ ህይወት መጠበቂያ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ተመዝግቦ ይገኛል። ጣና ሃይቅ በውስጡ በሌላ ቦታ የማይገኙ የተለያዩ የዓሳና ብርቅዬ አእዋፋት ዝርያዎች መኖሪያ ሲሆን  የሃገሪቱን ታሪክ የያዙ ጥንታዊና ባህላዊ ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናትን አቅፎ ይገኛል። በሃይቁ ተፋሰስ ዙሪያ  ለሚኖሩ ከ ፪-፫ ሚሊዮን ለሚጠጉ  የአካባቢው ማህበረሰቦች የእለት ከእለት እንቅስቃሴና የኑሮ ዋስትና መሰረት ሴሆን ጣና የዓለም አቀፍ የቱሪስት መስህብ በመሆን ለሃገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭም ያስገኛል::  ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ጣና ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተጋርጦበት፤ የመኖር ህልውናው አደጋ ላይ ወድቋል። ጣናን የወረረው መጤ አረምም በየቀኑ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ በአሁኑ ወቅት ከ 5,000 ሄክታር በላይ የጣናን ክፍል ሸፍኖ የሃይቁን ተፈጥሮአዊ መስተጋብር አናግቷታል። ጣናም ከመቸውም ጊዜ በላይ የእኛ የኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ ይሻል።


Picture showing water hyacinth infestation at Lake Tana

ይህን መጤ አረም ለመቆጣጠርና ዘላቂ የሃይቅ ስነ-ምህዳራዊ ቁጥጥርና እንክብካቤ ስራዎችን ለመስራት በጥናት ላይ የተመሰረተ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን መስራት ይጠይቃል። የዓለማቀፍ ጣናን መልሶ የማቋቋም ጥምረት (Global Coalition for Lake Tana Restoration ) ጣናን ለመታደግ በአሜሪካን ሃገር ተመዝግቦ  የሚገኝ ግብረ-ሰናይ ማህበር ነው። ማህበሩ የጣናን ችግሮች በማጥናት መፍትሄ ለመስጠት ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንና ሃገር-በቀል ማህበራት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ማህበሩ የአጭርና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን አውጥቶ በመተግበር ላይ ሲሆን የአጭር ጊዜ እቅዶቹም በዋናነት፤ 3 አረም አስወጋጃ ማሽኖችን መግዛት፤ ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች መስጠትና የተጠና የእምቦጭ ቁጥጥርና ክትትል አሰራር መዘርጋትን ያካትታል። እነዚህን ዕቅዶች ለማስፈጸም ከ250,000 የአሜሪካን ዶላር በላይ ያስፈልጋል። ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ የማቋቋም ጥምረት ይህንን ዕቅድ ለማስፈጸም የዳበረ ልምድ ባላቸው ባላሙያዎች እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለ ማህበሩ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን የማህበሩን ድህረ-ገጽ  ይጎብኙ፤ www.tanacoalition.org 


Satellite picture showing the coverage of water hyacinth infestation in north-eastern parts of Lake Tana (Jan 2018)

በቅርቡ በታላላቅ የአሜሪካን ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ የሚዘጋጅ ቢሆንም ከችግሩ አሳሳቢነት አኳያ በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ የሚጠይቅ ሆኖ ተገኝቷል። እርስዎም በዚህ አጋጣሚ በ GoFundMe በሚደረገው የገቢ ማሰባሰብ የበኩልዎትን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በአክብሮት ተጋብዘዋል:: ይህ ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ ከሚያሰፈለጉ ፫ የማጬጃ ማሺኞች የአንዱን ሙሉ ወጪ ($85,000 የአሜሪካን ዶላር) ከነ መለዋወጫውና ማጓጓዣው  እንዲሁም የGoFundMeን ክፍያ ጨምሮ ለማሰባሰብ ነው::
  

Global Coalition for Lake Tana Restoration 

This is a call for a mission to save Lake Tana from its current challenges. The Global Coalition for Lake Tana Restoration, a US-based non-profit organization, aims to support the implementation of research-proven lake management activities around Lake Tana. The Organization is composed of highly trained expertise on environmental and aquatic ecosystem management. This fundraising aims to collect funds required to buy aquatic weed harvesters, train local staff and design monitoring and evaluation tools.

ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ አባላት፤

1. ዶ/ር አሰፋ መለሰ (የቦርድ አባል)
2. ዶ/ር ይርጋለም አሰግድ (የቦርድ አባል)
3. ዶ/ር ሰለሞን ክብረት (ሰብሳቢ)
4. ዶ/ር ማርታ ዳኘው (ም/ሰብሳቢ)
5. ዶ/ር ይሁን ድሌ (የሳይንስ ቡድን መሪ)

Alternatively, you may use our PayPal account and credit cards for donations. Thank you.

For more information visit us :

http://tanacoalition.org/

Address - 4600 14th St. NW
Washington DC 20011
United States


ጣና ውሃ አይደለም -Tana Wuha Ayidelem - Amazing poem by Solomon Nurga - December,2017

https://www.youtube.com/watch?v=m-vYEDmM4yU&t=111s


Global coalition for lake Tana Restoration Fundraising Event in Washington DC March,17  2018

https://www.youtube.com/watch?v=O9P0ucEebVA



 GoFundMe Giving Guarantee

This fundraiser mentions donating through another platform, but please know that only donations made on GoFundMe are protected by the GoFundMe Giving Guarantee.

Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $5 
    • 5 yrs
Donate

Organizer

Global Coalition for Lake Tana Restoration
Organizer
Washington D.C., DC

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.