176
176
3

Support Colonel Tadesse Muluneh

$17,500 of $50,000 goal

Raised by 179 people in 5 months

የሰማይ አሞራው ጀት አብራሪ..
የሐገር ድንበር አስከባሪ...
ገድለ ሰፊ ታሪክ ሰሪ...

በእስር ማቆ...
ተሸማቅቆ...
ከሐገር እርቆ...
ቅስሙ ደቆ...
ገላው ደርቆ...
ወገን ናፍቆ...
መጣ ልቆ.....

በሰው ሐገር ተሰቃይቶ...
መከራ ግፍ ፅልመት አይቶ...
ልቡን ሰብሮ አንገት ደፍቶ...
ዛሬ ካሰው አምላክ ሰምቶ...

ይኽው እንግዲ መጣ ዛሬ...
ብርቅዬው ልጅ የሐገር ፍሬ...

ይብላኝልን ለኛ ለኛ...
ውለታ እረሺ ከዳተኛ..
ለሞተልን የማንተኛ..

ምን እንክፈለው መካካሻ..
ብድር ውለታውን መመለሻ..
ለበደላችን ማረሳሻ....
ለዚህ ጀግና የለው ድርሻ..

መስዎት ሆኖ የታገለ...
የመኖር ህልሙን የገደለ...
የማይከፈለውን የከፈለ...

በህይወት ኖሮ ገባ ሐገሩ..
አብቅቶለት ጭንቅ አሳሩ..
ከናፈቃት ከእናት ምድሩ...

ጀግናው የአይር ተዎጊ ጀት አብራሪው ኮ/ኔል ታደሰ ሙሉነህ ለዘመናት በኤርትራ መንግስት ወይኒ ከተወረወረበት እስር ተፈትቶ ዎጋ ከከፈለላት ሐገሩ በሰላም ተመለስ ።

በማራኪ ከስዊድን

*********************************************************************************************************


በቅርብና በሩቅ ላላችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የማክበር ሰላምታችንን እናቀርባለን። የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባለደረባ የነበረው ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ለወገኑና ላገሩ ያበረከተው አገልግሎት በሶማሌው ጦርነት ብቻ አላበቃም:: ህወሃት ወያኔ የፋሽስት ሰርዐት መሆኑን ቀድሞ ስለተረዳ ወያኔን ለመዋጋት ኤርትራ ውስጥ በመግባት የአርበኞችን ግንባር በመመስረት የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን ሲታገል ቆይቷል።

የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ዓላማም ሆነ ተግባራዊ እርምጃ፡ ለሀገሩ ነጻነት ሲፋለም በሀገሩ ምድር ላይ መውደቅ እንደነበር፡ ለትግል አብረውት ተሰልፈው የነበሩ ሁሉ፡ አጽኖት ሰጥተው የሚመሰክሩለት ኢትዮጵያዊ ከመሆኑም በላይ በተለያዬ ጊዜ አውሮፓንና አሜሪካንን እየጎበኘ በነበረበት አጋጣሚ በዚያው እንዲቀር ሲመከረና ሲለመን እንቢ እያለ ወደትግል ሜዳው መመለሱ፡ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊእነት መከበር ከአእምሮና ከጉልበት አልፎ፡ የአካልና የህይወት ዋጋ ለመክፈል፡ የወሰነ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ምስክር ነው።

በትግል ላይ እያለ ለስምንት አመታት የተስወረው ወንድማችን ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ በቅርቡ ተግንቷል። በዚህ አጋጣሚ በወንድማችን መስወር አብሮን ሲጨነቅ ለነበረው ወገናችን ሁሉ የመገኘቱን ደስታ ስንገጽ ከታላቅ ምስጋና ጋር ነው።

ወንድማችን ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ አሁን የሚገኝበት የጤና እና የኑሮ ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል።ለትናንት ጀግኖቻችን ስራ፡ እውቅና ካልስጠን፣ ለዛሬ ጀግኖቻችን በችግራቸው ካልደረስን፣ እንዴት ነው ለወደፊት፡ ሃገርን ከጥፋት፣ ወገንን ከውርደት ሊታደግ የሚችል፡ ጀግና የምናፈራው?

የወንድማችን ሁኔታ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም። ስለዝህ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተከፈተው “Go Fund Me” የምትችሉትን እንድትለግሱ ቤተስቦችና ጓደኞቹ በትህትና በአክብሮት እንጠይቃለን።

" ጀግኖቻችንን በሕይወት እያሉ ልናከብራቸው፤ ሲቸገሩም ልንደግፋቸው ይገባናል። ስለዚህ ይህን ለኢትዮጵያ አገራችን ከወጣትነቱ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መስዋዕትነት ሲከፍል የኖረ የጀግኖች ጀግና የሆነ ወገናችንን ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን በዚህ ወቅት ካልደረስንለት ውድቀቱ የእኛ የወገኖቹ እንጂ የእርሱ አይደለም።"

በዚህ አጋጣሚ በማስተባበርና በማበረታት ለተባበሩን የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ሀይል አባላት የከበረ ምስጋናችን እናቀርባለን::

ለወገን ደራሽ ወገን ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በ tadessemuluneh288@gmail.com ይጻፉልን።

ወይንሸት ታደሰ ሙሉነህ
ዮሐንስ አድማሱ
We offer our greetings to all Ethiopians near and far. Colonel Tadesse Muluneh joined the Ethiopian Air Force at the young age and served his country as a Pilot rising to the rank of Colonel. As a Pilot he was always ready to defend his country from foreign invaders.
 
Colonel Tadesse Muluneh  is also  a founder and former leader of the Ethiopian People's Patriotic Front (EPPF) because he believed that Patriotism is supporting your country all the time, and your people when it deserves it.

It is  to be remembered that Col. Tadesse Muluneh,, disappeared in Eritrea in October 2010 and was found alive recently. The Family would like to thank God Almighty for keeping him safe and giving us the strength. Again, thanks to everyone for your prayers! We love you all and we never could have made it on this journey without all of your support!

 However, as you may know, Col. Tadesse Muluneh is ill  and currently dealing with so much health complications and life challenges. It is impossible for him to cover most of his medical expenses. He is very grateful for prayers and continuous support in the past. And because of this enormous medical and personal financial needs,  his family and friends have delegated his daughter Weineshet Tadesse Muluneh and brother Yohannes Adamsu who resides in Toronto, Canada to mobilize all Ethiopians around the world to raise funds for him. This is an opportunity for you to stand with the Ethiopian Patriot  Col. Tadesse Muluneh and show him you care.

Therefore, we are kindly asking you to come alongside and do all you can to help our dear brother. All the money raised on GoFundMe is going toward his medical expenses. We will keep you updated the progress as well as the next steps.  

There are many people behind this great cause, and it's impossible to list them all here. The family would like to thank the Former Ethiopian Air Force members for coordinating this fund raising with Col. Tadesse Muluneh’s family. 

We are open to engage and accept your constructive and creative input towards this cause. For more information please contact us at tadessemuluneh288@gmail.com

God Bless Ethiopia

Weineshet Tadesse Muluneh

Yohannes Adamsu
+ Read More
ጀግኖቻችንን በሕይወት እያሉ ልናከብራቸው፤ ሲቸገሩም ልንደግፋቸው ይገባናል። ስለዚህ ይህን ለኢትዮጵያ አገራችን ከወጣትነቱ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መስዋዕትነት ሲከፍል የኖረ የጀግኖች ጀግና የሆነ ወገናችንን ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን በዚህ ወቅት ካልደረስንለት ውድቀቱ የእኛ የወገኖቹ እንጂ የእርሱ አይደለም። እባክወትን share ያድርጉ፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!
+ Read More

$17,500 of $50,000 goal

Raised by 179 people in 5 months
Your share could be bringing in donations. Sign in to track your impact.
   Connect
We will never post without your permission.
In the future, we'll let you know if your sharing brings in any donations.
We weren't able to connect your Facebook account. Please try again later.
AG
$500
ASHEBIR GEBRE
22 days ago
HT
$100
Haimanot Taddess
1 month ago
AA
$195
Amare Admasu
1 month ago
AM
$30
Asheber Menker
1 month ago
$50
Mesfin Ayele
1 month ago
TZ
$85
Teketel Zewdie
1 month ago
SH
$50
Saba Haile
1 month ago
$50
Hiwot Demssie
1 month ago
$50
Anonymous
1 month ago
GS
$50
Getachew Sheferaw
1 month ago
or
Use My Email Address
By continuing, you agree with the GoFundMe
terms and privacy policy
There's an issue with this Campaign Organizer's account. Our team has contacted them with the solution! Please ask them to sign in to GoFundMe and check their account. Return to Campaign

Are you ready for the next step?
Even a $5 donation can help!
Donate Now Not now
Connect on Facebook to keep track of how many donations your share brings.
We will never post on Facebook without your permission.