
የስቱዲዮ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ
Donation protected
ሼር ማድረግም ከእገዛ አንዱ ነውበመላው ዓለም ለምትገኙ ለተከበራችሁ ሙስሊም እህት እና ወንድሞቼ
ይህን ፖስት ያደረኩት ትንሺ ልቤ ስላዘነ እና ስለከፋኝ ነው አውፍ በሉኝ
ፋቲህ ሪከርድስ ብዬ በጀመርኩት የስቱዲዮ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ጀምሬ በማቆሜ አንዳንድ ሰዎች የተሳካ የመሰላቸው እና ዳጎስ ያለ ገንዘብ የሰበሰብኩ የመሰላቸውም ብዙ ሰዎች አሉ.እውነታው ተስፋ መቁረጥ ሳልፈልግ ትንሽ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሆነብኝ ይህን የቪድዮ እና ኦዲዮ ስቱዲዮ ፕሮዳክሽን ከፍቼ ወደ ስራ ለመግባት 12,000,000 ሚልየን ብር አጠቃላይ ያስፈልገኝ ነበር
የጠየቁት !እንስራ ስራ ልስራ ልጥቀም እኔም ምንዳው ከአላህ ላግኘው እንጂ ወላሂ የዱንያን ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት አይደለም
ካሜራዎች ዘመናዊ የቁርዓን የሀዲስ የአናሺድ የመንዙማዎች የቅጂ መሳሪያዎች ማይኮች ላፕቶፕ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች ሌሎች ያልጠቀስኩዋቸው ማቴሪያሎችን ለመግዛት ሂሳብ ሰርተን የመጣልን 12ሚልየን ብር ነበር
በነበረኝ የሁለት ቀን የቲክቶክ የላይቭ ቆይታ ላይ 100,000 መቶ ሺህ የኢትዮ ብርም ሰብስቤ ነበር በሰበሰብኩትም ገንዘብ የ6ወር የስቱዲዮ ክራይ 1 ላብቶፕ ገዝቼም ነበር አሁን ላይ እቃዎቹን ገዝቼ አሙዋልቼ ስቱዲዮውን ለመክፈት ከባድ ዳገት ሆኖብኛል ራሴን አጋልጬ ፊት ለፊት የመጣሁ ለዑመቱ የሚጠቅም ስራ ከፍ ባሉ ስራዎች ለመከሰት ነበር ቢሳካ ጥቅሙ የኔ ብቻ አልነበረም!
ማንም ሰው ላይ አልፈርድም ግን! ማድረግ ይቻል ነበርኮ!!!
ብቻ አልሀምዱሊላህ ይሁን ለበጎ ነው አላህ የተሻሉ መንገዶችን ከፋችን ነው ብዬ ለግዜው ተስፋዬን መለስ አድርጌ አዲስ ነገር እየጠበኩኝ ነው ለምንድነው ግን በቁም ማንረዳዳው?ስንሞት ብቻ ነው ውድ የምንሆነው?ካበቃለት ካለፈ ቡኅላ ነው ምንተጋገዘው
አላህ የሰጠኝ ሙስሊም እህትና ወንድሞቼ እያላችሁ የሌላ እምነት ተከታይ ሰው መቼም ሊያግዘኝ እኔም እገዛውን ልጠይቀው አልችልም
መቼም ሞት አይቀርም !!! አላህ ሀያታችንን ያርዝመው እንጂ ወላሂ ወተላሂ ወቢላሂ እኔ ከሞትኩ ቡኃላ ምንምን አይነት የገንዘብ እርዳታን አልፈልግም ዱዓችሁን ቢሆን እንጂ !
ሀስቡነ አላሁ ወኒዕመል ወኪል (ወላሁ አዕለም )
Organizer
Ibrahim ahmed wazir
Organizer
Seattle, WA