Main fundraiser photo

“ኑ! የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ”፡፡ ነህምያ 2:20

Tax deductible
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

“ኑ! የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ”፡፡ መጽሐፈ ነህምያ 2:20

ታቦተ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ታቦተ ቅድስት ሥላሴ ፍጹም በሆነ የልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ወደከተማችን ሒውስተን በሚያዚያ ወር 2007 (April 2015) በመምጣታቸው ምክንያት የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ እና የቅድስት ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተመስርቶ ታቦታቱም ላለፉት 4 ዓመታት ከተማችንን፣ ሕዝባችንንና አገልጋይ ካህናትን እየባረኩን ይገኛሉ። ይህም ታብተ ጽዮንን በክብር በመቀበሉ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤቱን ሁሉ እንደባረከ በተጻፈው መሰረት ነው።(2 ሳሙ 6: 11)።  ታቦተ ጽዮን በድንኳን ተቀምጣ ስትባርክ እንድኖረች ሁሉ እኛም ታቦታቱን በድንኳኑ አንጻር በኪራይ ቤት በማስቀመጥ መንፈሳዊ አገልግሎታችንን  በመስጠት ላይ እንገኛለን።

 ይሁን እንጂ ታቦታቱ አሁን ያሉበት ቦታ ኪራይ ከመሆኑ ባሻገር ለቤተክርስቲያን አመቺ አይደለም።  ልበአምላክ ዳዊት “እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፥ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በመጋረጆች ውስጥ እንደ ተቀመጠ አያልሁ። (2 ሳሙኤል 6: 11) ብሎ ታቦተ ጽዮን የምታድርበት መቅደስ ለመስራት እንደተነሳ ሁሉ በአጥቢያው የምንገኝ ምዕመናን ለታቦታቱ ማደሪያ የሚሆንና የምንባረክብት ቦታ በመግዛት (8231 McGee Ln., Houston, TX 77071) ፣ ቦታውንም በሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ በማስባረክ፣ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑን ለመስራት በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ይህም “በመካከላችሁም አድር ዘንድ መቅደሴን ሥሩልኝ" (ዘጸ 25:8 ) እያለ የሚጣራውን የፈጣሪያችንን ቃል ለመፈጸም የሚደረግ ጥረት ነው። ስለዚህ ለዚህ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታ የሚሆን የገንዘብ፤ የቁሳቁስ፤ የሙያ ድጋፍ በማድረግ ይህንን የእግዚአብሔር ቤት አብረን እንድንሰራ እንዲሁም በሃሳብና በጸሎት እንድታግዙን ስንል መንፈሳዊ ጥሪያችንን በቅድስት ሥላሴ፣ በቅድስት ድንግል ማርያምና በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም እናስተላልፋለን፡፡

  ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ 


Want to join me in making a difference? I'm raising money to benefit Holy Trinity and Saint Mary Ethiopian Orthodox TEWAHEDO Church, and any donation will help make an impact. Thanks in advance for your contribution to this cause that means so much to me.

Organizer

Endale Abebe
Organizer
Houston, TX
Holy Trinity and Saint Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe