Main fundraiser photo

Amhara Satellite Radio and Television (ASRAT)

Donation protected
ለድምፅ-አልባው ሕዝባችን ዘላቂ፣ ተዓማኒና ተደማጭ ድምፅ እንሁን።

የአማራ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን (አሥራት ሚድያ) በቁርጥ ቀን የአማራ ልጆችና በአማራ ወዳጆች ኢትዮጵያውያን ከተመሠረተ ጀምሮ ድምፅ-አልባ ለሆነው ሰፊ የአማራ ሕዝብና ለሌሎች ወንድም ኢትዮጵያውያን ድምፅ ሆኖ ቆይቷል። የአማራን ሕዝብ፤ ሀገሩ ኢትዮጵያ ከሌሎች ወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነትና በሰላም የሚኖርባት እንድትሆን ከአንድ በአማራ ሕዝብ ከተቋቋመ የብዙኃን መገናኛ ተቋም የሚጠበቀውን ድርሻ ለመወጣት አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ሰርቷል። በአጭር ጊዜ የአገልግሎት ዘመኑ፤ አድሎአዊ አሠራሮችን፤ የንጹኃን ጭፍጨፋዎችን፤ ሕገወጥ መፈናቀሎችን፤ የንጹሃን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አረመኔያዊ ግድያዎች፣ ማሰቃየቶችንና ጠለፋዎችን፤ በስልጣን አላግባብ መጠቀምን፤ በአጠቃላይም ብልሹ አስተዳደርን ሲዘግብና ሲያጋልጥ፤ እንዲሁም ገንቢ ትችቶችንና ጥቆማዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። በዚህም በሀገራችን እየደረሱ ካሉ ዘግናኝ ችግሮች የባሱ ምስቅልቅሎች እንዳይከሰቱ መከላከሉን እንረዳለን። በዚህም በሀገር ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በመከላከል ኃላፊነት ከሚሰማው አንድ የብዙኃን መገናኛ የሚጠበቀውን ድርሻ መወጣቱን እናምናለን።

ተቋሙ እነዚህን ተግባራት ለመፈጸም ይበቃ ዘንድ፤ በበጎ ፈቃድና በቂ ባልሆነ ክፍያ ላገለገሉና እያገለገሉ ላሉ የተቋሙ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ላሉ ደጋፊዎቻችን በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በተጨማሪም፤ በቅን ልቦና ስንሳሳት የምንታረምበትን ሃሳብ ለሰጣችሁን፣ መልካም ስንሠራ ላበረታታችሁንና ድካም ሲሰማን አቅም ለሆናችሁን ሁሉ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን።

አሥራት ሚድያ በደረሰበት የፋይናንስ አቅም ማነስ ምክንያት ዕዳዎቹን ሊከፍል ካለመቻሉም በላይ፤ በዋሽንግተን ዲሲ የነበረውን ስቱዲዮ ለመዝጋት እንደተገደደ ይታወሳል። በዚህም፤ ለፖለቲካዊ ጫና ተጋላጭ ሆኗል። ፖለቲካዊ ጫናዎቹ ከሚገለጹባቸው መንገዶች መካከል፤ የባለሥልጣናትን አስተያየት ጠይቆ መልስ መከልከል (ቀጥሎም "ሚዛናዊ ዝግጅቶች ባለማቅረብ" መከሰስ)፣ ጋዜጠኞችን ማሰርና ማንገላታት በሂደቱም ሌሎች ጋዜጠኞችን በማሸማቀቅ ዕለታዊ ተግባራቸውን እንዳይከውኑ ማድረግና የመሳሰሉ ናቸው።

ሆኖም፤ ሕገ-መንግሥታዊና መዋቅራዊ በደል ለሚደርስበት ሕዝባችን እንዲሁም ተመሳሳይ በደል ለሚፈጸምባቸው ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ሐቀኛ ድምፅ አለመሆን ለኅሊና ወቀሳ የሚዳርግ ድርጊት መሆኑ ከግምት ሲገባ፤ አሥራት ሚድያን መዝጋት አማራጭ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም።

ስለሆነም፤ አሥራት ሚድያን ከሚደርስበት ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ጫና ለመከላከል፤ እንዲሁም የአማራን ሕዝብ ዘላቂና ፍትሐዊ ጥቅሞች ለማስከበር በሚደረገው ትግል ተቋሙ ያሉበትን ዕዳዎችና የሰራተኞቹን ደመወዝ ከፍሎ ወሳኝ ሚናውን በሀገርቤትና በውጭ እየተወጣ ይቀጥል ዘንድ አሥራት ሚድያን አቅምዎ በሚፈቅደው መጠን እንዲደግፉ የማክበር ጥሪያችንን እናቀርብልዎታለን። ጥሪያችንን ችላ እንደማይሉም ተስፋ እናደርጋለን።

ለዘላቂው፤ https://asratmediahouse.org ላይ ከሚገኙት ዘዴዎች በአንዱ ወርኃዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥያቄአችንን እናቀርባለን።

ድር ቢያብር፤ አንበሳ ያስር!
የአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፤
ነሐሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት።
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    ASRAT MEDIA HOUSE
    Organizer
    Seattle, WA

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee