Main fundraiser photo

Urgent Life-Saving Call for Meseret Fentabil

Donation protected
አስቸኳይ የሕይወት አድን ጥሪ ለመሰረት ፈንታቢል፡ የልጆች እናት ሕይወት አድን ህክምና ትፈልጋለች

መሰረት ፈንታቢል በባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ እና የሶስት ልጆች እናት ስትሆን፣ በትህትናዋ እና በደግነቷ የምትታወቅ እና ለተቸገሩ ሰዎች የአቅሟን ሁሉ ለማድረግ ግንባር ቀደም የሆነች መልካም ሴት ናት፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት ለሕይወት አስጊ የሆኑ ከባድ የጤና ችግሮችን ስትታገል ቆይታለች፡፡ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው በ2015 ዓ.ም. የ70 ዓመቱ አባቷ ኩላሊታቸውን ለግሰዋት ንቅለ ተከላ ተደርጎላት ነበር፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ንቅለ ተከላው አልተሳካም። በዚህም ምክንያት ሌላ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ የግድ ያስፈልጋታል፡፡ አሁን በየጊዜው የኩላሊት እጥበት እያደረገች ትገኛለች።

ነገር ግን ከዚህም በላይ የሚያሰጋው ሥር በሰደደ ተጓዳኝ የልብ በሽታ (Chronic rheumatic valvular heart disease) እየተሰቃየች መሆኑ በሃኪሞች መረጋገጡ ነው። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና ቡድን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ከመደረጉ በፊት የልብ ህመሟ መታከም አለበት ብሏል፡፡ እንደሚታወቀው እንዲህ አይነት የነፍስ አድን የቀዶ ጥገና ህክምና በኢትዮጵያ ውስጥ ሊደረግ ስለማይችል በውጭ ሃገር ማለትም በሕንድ ወይም በታይላንድ መደረግ ይኖርበታል። አጠቃላይ የህክምናው ወጭ ከ50,000 ዶላር በላይ የሚገመት ሲሆን ይህም ለመሰረት እና ቤተሰቧ ከአቅማቸው በላይ ነው።

መሰረት ሕይወቷን ለማዳን የሚያስፈልጋትን ህክምና እንድታገኝ በዓለም ዙሪያ ያሉ ደጋግ ሰዎች እንዲረዷት እና ሕይወቷን እንዲታደጓት በፈጣሪ ስም ትጠይቃለች! እያንዳንዱ መዋጮ ለልጆቿ እና ለቤተሰቧ እንድትኖር እድል በመስጠት ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።

ስለ ልግስናችሁ፣ ስለ ደግነታችሁ እና ስለ ጸሎታችሁ አስቀድመን በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን! ለድጋፋችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

አስተባባሪ ኮሚቴው

Urgent Life-Saving Call for Meseret Fentabil: A Mother in Need of Life-Saving Treatment

Meseret Fentabil, a loving wife and mother of three from Bahir Dar, Ethiopia, is known for her humility and kindness, and she is always the first to lend a hand when someone is in need. Sadly, for the past six years, she has been battling life-threatening severe health issues. Both of her kidneys had failed. She underwent a kidney transplant in 2022, with her 70-year-old father as the donor. Unfortunately, the transplant was unsuccessful.

Before another transplant can be attempted, doctors discovered Meseret suffers from chronic rheumatic valvular heart disease. The medical team at St. Paul’s Hospital in Ethiopia has determined that the heart condition must be treated first, before attempting another kidney transplant, while she continues her dialysis. Unfortunately, this life-saving surgery cannot be performed in Ethiopia and must be done abroad, in India or Thailand. The total cost of the treatment is estimated at over $50,000, far beyond what Meseret and her family can afford.

Meseret humbly asks individuals around the world to help her receive the treatment she needs to save her life. Every contribution counts in giving her a chance to live and be there for her children and family.

We thank you for your prayers, generosity, and kindness. May God bless you for your kind support!

The Organizing Committee
Donate

Donations 

  • Seble Tekle Ferede
    • $20
    • 1 mo
  • haieleysus yizengaw
    • $100
    • 4 mos
  • Anonymous
    • $15
    • 5 mos
  • Tariku Sherif
    • $100
    • 5 mos
  • Anonymous
    • $20
    • 5 mos
Donate

Co-organizers (2)

Desalegn Mengistie
Organizer
Milpitas, CA
Firehiwot Tessema
Co-organizer

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee