Main fundraiser photo

“በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም”

Tax deductible


          በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

                                      “ራእይ ሲታደስ”

                    ትኩረት ለኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ።
               
               ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ራእይ ይሰጠዋል።
                                     
                                    ለእኔም እንደዚሁ።

ራእይ ሁለት ዓይነት ምሪት አለው። እነዚህም በማወቅና ባለማወቅ ሲሆኑ የእኔ ሁለቱንም የያዘ ነው ማለት እችላለሁ።
ይኽም በአለማወቅ፣ (በወላጆች ምሪት) በሕፃንነት ወደገዳም መወሰድና በጉባኤ ቤት በሊቃውንት እግር ሥር ማደግ ፣
በማወቅ፣ (በራስ ምሪት) መንፈሳዊ ጥበብን ከሥጋዊ ጥበብ ጋር ለማጣጣም ወደ ከተማ መግባትና ከዚያም በቤተ ክርስቲያኒቷ አማካኝነት ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አውሮፓ መዝለቅ ነበር።
በአውሮፓ በትምህርት ሳለሁ ማኅበረ ክርስቲያኑ በመንፈሳዊ ሕይወት ተደራጅቶ እንዲጓዝ የሚያመለክት ራእይ ተቀብያለሁ። ይህም የሰው ልጅ ከልደቱ አንስቶ ያለውን የሕይወት ጉዞውንና ዘመኑን፣ ሕፃንነቱን፣ ወጣትነቱን፣ ጎልማሳነቱን፣ ሽምግልናውን በአጠቃላይ የመነሻ መድረሻውን ሂደት የሚያመለክትና በሦስት ደረጃ የተከፈለ ነው።
በአንደኛ ደረጃ የተጠቀሰው ራእይ፤ “እምነት፤ ተስፋ፤ ፍቅር” የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስን ቃል መሠረት ያደረገ ሲሆን ይኽም ታላቅ ካቴድራል እንደሚሠራና የቤተ ክርስቲያን ተረካቢ የሆኑ ተተኪ ትውልድ “የፍቅር ኅብረት” በሚል ስያሜ ወጣቶችን የሚያደራጅ ነው።
በሁለተኛ ደረጃ፤ “ልጅህን በሚሄድበት ቦታ ምራው” “ሕፃናት ወደእኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው” የሚለውን ቅዱስ ቃል መሠረት ያደረገ ነው።
ስለሆነም ለወላጆች ተብሎ በተሰጠው ምክር፣ ሕፃናት መንፈሳዊ እንክብካቤ እየተደረገላቸው በጥበብና በመልካም ምግባር እንዲያድጉ “በተስፋ ለሕፃናት” በሚል ስያሜ ሕፃናትን የሚያሰባስብ ነው።
ሦስተኛው፤ የተፈጥሮ ሕግጋትን፣ (ልደትና ሞትን) ሂደቱን ያካተተ ምሪት ነው። ይኽም በዘመኑና በጊዜው ሁሉም የሚለወጥ መሆኑን ያመለክታል። ወጣት ሆኖ የሚቀር የለም፤ በተራው ወላጅ ይሆናል፤ አዲሱ ያረጃል፤ ሁሉም ያልፋል። ወላጆች በወጣትነታቸው ጊዜ ያካበቱትን የአገልግሎት ልምድ በስፋት በመቀጠልና በማዳበር የወላጆች መዘምራን፣ የወላጅ አገልጋዮች፣ በሚል የአገልግሎት ዘርፍ በመሳተፍ “በእምነት ኅብረት” ጥላ ሥር እንዲደራጁ ማድረግ ሲሆን በተጓዳኙም በእርጅና ወራት አረጋውያን የሚረዱበት፣ የሚጦሩበትና የሚሸኙበት፣ መረዳጃ ማህበራዊ አገልግሎትን ይመሰርታል።
ይህ ራእይ፣ መቼና በየት ቦታና ሥፍራ እንደሚደረግ የታወቀ አልነበረም። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የሰጠውን ራእይ በፈለገው ጊዜና ቦታ በፈቃዱ መፈጸሙ የማይቀር ነው። በመሆኑም፣ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነውና የማይቻለውን እንዲቻል አድርጎ አሜሪካን በ1991 ዓ.ም ገባሁ። በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሃያና ሠላሳ በሚሆኑ ምዕመናን አገልግሎቴን ጀመርኩ።
በተሰጠኝ ራእይ መሠረት ወጣቱን የሚያሰባስብ “የፍቅር ኅብረት” ተመሠረተ። የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ተቋቋመ።ለአምልኮ መገልገያ የሚሆን ቡካነን መንገድ ላይ ያለው ሕንጻ ተገዛ። ቤተክርስቲያኒቷም ርእሰ አድባራት (ካቴድራል) የሚል ስያሜ ተሰጣት። ወላጆች የሚያገለግሉበትና የሚዘምሩበት “በእምነት ኅብረት” በሚል ስያሜ ተደራጁ። ለሕፃናትና በዚህ ሀገር ለተወለዱ የቅዳሴ አገልግሎት በእንግሊዘኛ መሰጠት ተጀመረ። ሕጻናቱም “በተስፋ ለሕፃናት” በሚል ስያሜ ተደራጁ።
ከላይ የተጠቀሱትን ራእዮች በበለጠ ለማስፋፋትና ለማደራጀት ብሎም ተግባራዊ ለማድረግ የተሟላ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የሕንፃ ግንባታ ተጀመረ። የተጀመረውም የግንባታ ሥራ በድንገት ተቋረጠ። ይባስ ብሎም በብዙ ድካምና ውጣ ውረድ ከአቋቋምነው ቤተ ክርስቲያናችን በአመፅ ተገፍተን እንድንወጣ ተደረገ።
በዚህ ባልተጠበቀ ድርጊት እጅግ የአዘንን ቢሆንም ሁሉንም ነገር በትዕግሥትና በጸሎት ኃይል በመጠበቅ መንፈሳዊ አገልግሎታችንን ለመቀጠል ችለናል።
“ከአንዱ ሥፍራ ሲያሳድዷችሁ ወደ ሌላ ሥፍራ ሂዱ” በአለው መለኮታዊ ቃል መሠረት በዝርወት መንፈሳዊ አገልግሎታችንን በማከናወን ላይ እንገኛለን። በደረሰብን በደል ተስፋ ሳንቆርጥ በአሁኑ ወቅት ራእያችንን ሰንቀን በአዲስ መልክ ወደ ላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ በበለጠ ተነሳስተን ጥረት እያደረግን ነው።
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥ ታላቅ ደብር ለማነጽና በተጓዳኙም ለመላው የኅብረተሰቡ ክፍል፣ ዘርፈ ብዙ የሆነ ማኅበራዊ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማዕከል ለመገንባት ተነስተናል። አመቺ የሆነ ቦታ በማፈላለግ ላይ እንገኛለን።
ለዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ከጎናችን በመሰለፍ ይህንን ታላቅ ራእይ ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የገንዘብ እርዳታ እንድታደርጉልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። እንዲሁም በችሎታችሁና በሙያችሁ እንድትደግፉንና በጸሎትም እንድታስቡን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
እግዚአብሔር የሰጠውን ራእይ በራሱ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚያደርገው እምነታችን የጸና ነው።

“መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በኔ ላይ ትኖራለች፤
አሁንም እጄን አበርታ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሣዬ

In the Name of the Father, the Son and the Holy Spirit, Amen

Renewal of Faith, Hope, and Love The Ethiopian Orthodox Church has one of the richest histories of mankind! It has a vivid heritage that has persisted to this day, from the Ethiopian eunuch that received the gospel from Phillip to the Church’s role in the pivotal battle of Adwa against Italian expansion, to its rapid growth here in the United States and throughout the whole world. But the Church, as a whole, has recently fallen on hard times. Instead of spreading the teachings of Christ and the Gospels, there has been internal conflict and much grief as the church has struggled to stay focused on its message. Which is why DSK Mariam wants to create a new beginning for all of us, young and old. With your help, we can build a church that preaches Christ’s teachings of love, forgiveness, and mercy. We can become a forwardlooking church that remembers and teaches the ancient Orthodox tradition, but we can also create a church that will help its believers navigate modern-day issues.
Let us remember and celebrate the church’s history and its teachings, but l also let us avoid the mistakes of the past, and instead focus on the present needs of this generation of believers. To accomplish this, we will expand Sunday School program, provide service opportunities for members, and create programs that help ALL of our members. Every contribution that you make, no matter how little, makes a huge difference! Every dollar brings us closer to having a church that can help all of its members and bring all believers closer to God.  Let us create a church where people are free to worship and where future generations can learn and understand the tradition that God gave us. Let us create a church where the current (and new generations) of Christians can learn to be confident in their belief in Christ and the message of the Gospels! Amen

“መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በኔ ላይ ትኖራለች፤ አሁንም እጄን አበርታ”
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Dskdmariam Church
    Organizer
    Washington D.C., DC
    Ethiopian Orthodox Tewahdo Church Gedame Tekle Haimanot Bible Association
    Beneficiary
    • Faith

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe