
“ድረሱልን፣ አጥምቁን እና ወደ ቀደመችው ሃይማኖታችን መልሱን”
Donation protected
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“ድረሱልን፣ አጥምቁን እና ወደ ቀደመችው ሃይማኖታችን መልሱን”
የቅድስት ቤተ ክርስቲያናን ተቀዳሚ ተልዕኮ ቅዱስ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ በማዳረስ የሰው ልጅን ለእግዚአብሔር መንግሥት ማብቃት ነው፡፡ በሀገራችን ጠረፋማው ክፍል የሚኖሩ ወገኖችን በማስተማር፣ ማጥመቅ እና ማጽናት ረገድ የተሠራው ሥራ በእጅጉ ውስን ነው።
“ድረሱልን፣ አጥምቁን እና ወደ ቀደመችው ሃይማኖታችን መልሱን” እያሉ የሚጣሩ ነፍሳት ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡ የቅድመ ጥምቀት የሃይማኖት ትምህርት ለማስተማር፣ ለማጥመቅ፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራንን ለማሰልጠን፣ መጽሐፍትን ለመተርጎም እና መምህራንን ለመቅጠር በአጠቃላይ ክርስትናን በጠረፋማ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የሁላችንንም ተሳትፎ እና ድጋፍ ይጠይቃል፡፡
ስለሆነም ይህን መንፈሳዊ ተልእኮ እንዲደግፉ በልዑል እግዚአብሔር ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ማኀበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል