The Anointed Word Of God Church

  • A
10 donors
0% complete

$2,100 raised of $200K

The Anointed Word Of God Church

የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን

የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን በፓስተር ሚካኤል ወንድሙ ከተተከለች በኢትዮዽያ ሁለት አስርት ዓመታትን በዋሽንግተን ዲሲ ደግሞ 13 ዓመታት አስቆጥራለች:: ቤተክርስቲያናችን ራዕይዋ የሆነውን ፍጹም የሚሆን ሠውን በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት በማነፅ ለማቅረብ የተመሰረተች ሲሆን በዚሁ አገልግሎትም በኢትዮዽያ ከ2500 በላይ ምዕመንን በአምስት አጥቢያዎች በማገልገል ላይ ትገኛለች:: ምዕመኖቻችንም የእግዚአብሔር ቤት እንዲሰፋ እና ቅዱስ ቃሉም እንዲሰበክ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል በማድረግም ላይ ይገኛሉ::

አዲስ አበባ በሚገኘው ህንፃችን ሁሉን ያሟላ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን:: ሆኖም ግን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አጥቢያችን ለእሁድ እና ሃሙስ ብቻ በተገደበ ሰዓት ኪራይ ያለን በመሆኑ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የመኪና ማቆሚያ፣ የህፃናት ማቆያ፣ የታዳጊና ወጣቶች የመማሪያ እና የመጫወቻ ስፍራ ባለመኖሩ ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያናችን ለመምጣት እኛም ለማገልገል ተግዳሮት ሆኖብናል:: እንዲሁም ቤተክርስቲያናችን ላቀደቻቸው እና አሁንም ለማህበረሰቡ እየሰጠች ያለውን አገልግሎት አግዷታል::

የእግዚአብሔርን መንግስት እና ማህበረሰባችንን ለማገልገል እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ያለገደብ የሚያገለግልበትን እና የሚገለገልበትን ሥፍራ ለማዘጋጀት ይህንን የገንዘብ ማሰባሰቢያ አዘጋጅተናል:: ዓላማችንም ሁሉን ያሟላ የማምለኪያ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የማስተማሪያ እና ለማህበረሰቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ቤተክርስቲያንን መግዛት ነው::

በአዲሱ በምንገዛው ወይንም  በምንገነባው የማምለኪያ ስፍራችን ዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ፆታ፣ ሳይለይ ለማህበረሰባችን አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል::
ቦታው የህጻናት ማቆያንም ያካትታል::

ቤተክርስቲያናችን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ ትኩረትን በመስጠት ዓላማን ነድፋ ተነስታለች:: ልጆቻችን እግዚአብሔርን በማወቅ በፍቅር ታዘው እንዲኖሩ፣ እነርሱንም የሚመስሉ ጏደኞች እና ቤተሰብ እንዲያፈሩ በምንገዛው ወይንም  በምንገነባው የማምለኪያ ስፍራ ወጣቶች ትልቅ ስፍራ አላቸው::
እንዲሁም በተለያዩ ሱሶች የተሳቡብንን ልጆች መንከባከቢያና መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆንን ቤት አብረን እንገንባ::

የቻላችሁትን ሁሉ በገንዘብ በማገዝ በዚህ GoFundMe አጋርነታችሁን አሳዩን:: በማህበራዊ ገጾቻችሁ በማጋራት ሌሎችንም ሰዎች የዚህ በጎ አላማ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጋብዙዋቸው::

የጌታን ቤት ከኛ ጋር ለመስራት ተባባሪያችን ስለሆናችሁ እግዚአብሔር እናንተን እና የእናንተ የሆነውን በጌታ በኢየሱስ ስም  ይባርክ!


The Anointed Word of God Church, an evangelical Ethiopian community church, boasts a history spanning over two decades in Ethiopia and 13 years in the Washington D.C. area. Planted by our pastor, Pastor Michael, with a vision to present the perfect man to Christ, rooted in the scripture "Whom we preach, warning every man, and teaching every man in all wisdom; that we may present every man perfect in Christ Jesus" (Colossians 1:28), our dedicated members have played a pivotal role in our flourishing community.

In Ethiopia, our church has expanded to a congregation of 2500 and now calls a building with full facilities its own. However, here in the DMV area, where we are connected to approximately 250,000 members of the Ethiopian community, our local church is in immediate need of a dedicated space to continue serving and expanding our community outreach. The strength of our church lies not only in our shared faith but also in the strong cultural bonds that unite our community members.

Operating primarily in our native language, Amharic, we strive to meet the diverse needs of our community, catering to children, young adults, the elderly, and the entire congregation. Recognizing the pressing need for a dedicated worship space to better serve our community, we are launching a fundraising initiative. Our goal is to secure the necessary funds to purchase our own church facility. Your support is crucial in creating a lasting space for worship, fellowship, and community outreach.

We invite you to join us on this journey, contributing to the growth and development of the Anointed Word of God Church. Together, let's work towards establishing a permanent home for our congregation and fulfilling our mission of serving the community.


Organizer

Michael Woldeyohanes
Organizer
Washington D.C., DC
A
Anointed Word of God International Church
Beneficiary
  • Faith
  • Donation protected

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe