10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ!

10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ! video thumbnail, 1 of 710ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ! video thumbnail, 1 of 7
10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ! campaign photo, 2 of 7

Tana Haik Alumni Network’s fund provides student stipends, hygiene, and college grants

  • T
  • S
  • D
10 donors
10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ! campaign photo, 4 of 7
10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ! campaign photo, 5 of 7
10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ! campaign photo, 6 of 7
Fundraiser’s main image
0% complete

$2,300 raised of $7K

10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ!

10ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ!

0% complete

$2,300 raised of $7K

10 donations
Tax deductible
የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ በላቀ የትምህርት ውጤታቸውና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታቸው የተመረጡ ታዳጊ ተማሪዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ፣ ሴት ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ የሚያበረታታና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችም እገዛ የሚያደርግ ፕሮግራም ነው።

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ባካሄዳቸው ዘጠኝ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብሮች፡ ከቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች እና ደጋፊዎች በተደረገ ድጋፍ፦
  • ከ269 በላይ ተማሪዎችን በየወሩ በወጪ ደግፏል። ከ3000 በላይ ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ወርሃዊ ንጽህና መጠበቂያ በየወሩ አቅርቧል።
  • ከ45 በላይ ዓይነስውራን ተማሪዎችን የሚያግዙ ድምፅ መቅጃዎችን አቅርቧል። ወደ ዩንቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የዝግጅት ወጪን ሸፍኗል።
  • ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ክበብ ጋር በመተባበር የሮቦቲክስ እና ቴክኖሎጂ ስልጠና ከ40 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች አሰጥቷል።
  • ከ684,500 ብር በላይ በጀት በመያዝ ICT እና ሮቦቲክስ ላብራቶሪን የማጠናከር ስራ አስጀምሯል።
  • የኮምፒውተር ላብራቶሪዎችን የኔትወርክና ኤሌክትሪክ ዝርጋታ በባለሙያ አሥሰርቷል።
  • ለሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ሥራ የገንዘብና የማማከር ድጋፍ አድርጓል።
  • እንዲሁም የመምህራን ማረፊያ ክፍል እድሳት እና አዲስ ሎከሮችን አዘጋጅቷል።
  • የቤተመጽሐፍት ወንበሮች ድጋፍና የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) አቅርቧል።

በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የመጽሐፍ ማሰባሰብና የፅዳት ዘመቻዎችን አስተባብሯል። ሁሉም ሥራዎች የተሳኩት ግን ይህን በጎ ዓላማ ሰምተው በደገፉ ብዙ የተባበሩ እጆች እንደሆነ እናምናለን።
ባለፉት ዙሮች በነበረው ተሳትፎ ከቀድሞ ተማሪዎች በተጨማሪ ሁሉም በጎ አሳቢ ኢትዮጵያውያንና ጉዳዩን ከወዳጆቻቸው የሰሙ የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር መሳተፋቸውን አይተናል። በመጪው የ2019 ዓ/ም የትምህርት ዓመትም የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት ይህን በጎ ሥራ ለማስቀጠል ከዚህ በታች ያለውን ዕቅድ አውጥቶ በየዓመቱ የሚያደርገውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምሯል። እንዲሳተፉና ለወዳጆችዎም እንዲያጋሩ ድጋፍ በሚደረግላቸው ተማሪዎች ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።

በዚህ ለ10ኛ ጊዜ በሚደረገው “የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ” ድጋፍ የሚከተሉትን 5 ዕቅዶች ለማከናወን ታስቧል፦
1- በትምህርት ውጤትና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ 40 ተማሪዎችን በወጪ ማገዝ። ይህም ማለት ለእያንዳንዳቸው ከመስከረም እስከ ሰኔ በወር 1000 ብር መደጎም። ለዚህ ተግባር የሚያስፈልገው ወጪ፦ 10 ወር × 40 ተማሪዎች × 1000ብር=400,000 ብር ይሆናል።

2- እገዛ ለሚያስፈልጋቸው 1000 ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) ለአንድ ዓመት ማቅረብ። ለዚህ ተግባር የሚያስፈልገው ወጪ 600,000 ብር ይሆናል።

3-ለ5 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ መግዛት። ለዚህ ተግባር የሚያስፈልገው ወጪ 35,000 ብር ይሆናል።

4-ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚገቡ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረጊያና እና ለጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ህክምና መጠባበቂያ በጀት ማቅረብ። ለዚህ ተግባር የታቀደው የብር መጠን 150,000 ብር ይሆናል።

5- የህብረቱን ስራዎች ባህር ዳር ላይ ለሚሰራ ጸሐፊ የዓመት ደሞዝ ማቅረብ። ለዚህ የሚያስፈልገው ወጪከመስከረም እስከ ነሐሴ 4000 ብር ×12 ወር= 48,000 ብር ይሆናል።

በድምሩ 1,233,000 ብር የሚገመት ወጪ በማድረግ እነዚህን ሥራዎች ለማሳካት ታቅዷል፡፡

እስካሁን ባለፉት 9 ዙሮች የነበረው የተማሪዎች እገዛ የተሳካው ይህን በጎ ሥራ የሰሙና የወደዱ ሁሉ ባደረጉት ያላሰለሰ የገንዘብ፣ የሃሳብ እንዲሁም የጉልበት ድጋፍ ነው፡፡ በመሆኑም የዚህን ዓመት አስረኛ ዙር በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ጥሪ ስናቀርብ ድጋፋችሁ እንደማይለየን በመተማመን ነው። (ከዚህ በፊት በጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ የታገዙና ዩንቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎችን አስተያየት በYouTube ገፃችን ለማየት ይህንን ይጫኑ)

ከሀገር ውጪ ድጋፍ ለማድረግ በዓመታዊው የGofundme ዘመቻ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት ድረ ገፅን (www.tanahaikbdr.com) ይመልከቱ ወይም አባል ለመሆን እንዲሁም ጥያቄና አስተያየት በዚህ tanagraduates@ጂሜይል.com ይላኩልን፡፡

ላልሰሙ ወዳጆችዎም መረጃውን ያጋሩልን፡፡ ስለሚያደርጉት ትብብር ሁሉ በታዳጊ ተማሪዎቹ ስም እናመሰግናለን፡፡


የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት



About Tana Haik Alumni Network & it's Scholarship Programs In the year 2012, a few former-students who lived in Ethiopia and abroad volunteered to work together for the cause of giving back to their former school, Tana Haik and the community. They established the alumni group with a vision: “Together, we can make a difference to bring a bright future for students in our community!”. It was launched by supporting the school through providing furniture and Internet service to the Library, and organizing donation of books. In just a few years, alumni from all over the world shared the vision and expanded dimension of the support to students and the school. Currently, there are alumni members from various batches and non-alumni volunteers participating in annual fundraisers and campaigns to support current 'Tana Haik High School' students.

The support to students is provided annually in 4 formats:

1. Tana Family Scholarship (TFS)
A total of 40 students are selected annually based on academic performance & socio-economic status. And these students are given a monthly stipend or financial support throughout the academic year. The stipend is mainly used by students for study & living costs.

2. Sanitary Napkins to Female Students
Female students are provided free sanitary napkins at the school throughout the academic year. Currently the annual number of students supported has reached 1000.

3. Special Support to Disabled Students
Currently special voice recorders are provided annually to sight Impaired students.

4. Financial Support to Students Joining College. Selected number of students who newly join college are provided with one time financial support. The grant helps students with initial costs required to join college.

Please share with others, thank you for you support.

Tana Haik Alumni Network is organized by the following former students and volunteers of Tana Haik

Solomon Nurga – Atlanta, USA
Dejenie Tarekegn – Maryland, USA
Tenager Bekalu – Helsinki, Finland
Geta Mehariw –Portland, USA
Solomon Kibret – California, USA
Meseret Ejigu – Addis Ababa, Ethiopia
Sileshi Minayehu – Bahir Dar, Ethiopia
Behailu Yirga – Bahir Dar, Ethiopia
Mastewal Alemu – Bahir Dar, Ethiopia
Eden Metaferia – Stockholm, Sweden
Bekalu Metalign – Addis Ababa, Ethiopia
Rahel Wondie – Addis Ababa, Ethiopia
Minwyelet Getinet – Grande Prairie, Canada
Lake Endalew – Virginia , USA
Tewodros Tesera – Maryland, USA
Yonatan Gossaye – London, UK
Misganaw Birhan – Turku, Finland
Henok Hailemariam– Maryland, USA

[ *ከላይ ያለው ቪዲዮ ከአራት አመት በፊት የተሠራ ነው፣ ስለ ህብረቱ ስራዎች አጭር መረጃ ለመስጠት አጋራናችሁ *]

Donate

Organizer

Tana Haik Almuni Network
Organizer
Silver Spring, MD
T
Tana Haik Alumni Network Inc
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe