Tesfa Neda support ( ተጋግዘን ጉራጌን ለአለም እናስተዋውቅ)

በመጥፋት ላይ ያለውን የጉራጌ ህዝብ ማንነትና ፣ ባህል ፣ ቋንቋ እናሣድግ ❗ እናስተዋውቅ❗
ከተሞቻችንን እናሣድግ ❗ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንትን እንሳብ❗

ተስፋ ነዳ እባላለሁ።በሙያዬ ደራሲና ዳይሬክተር ነኝ። የቤቶች ሲትኮምን ፣ ትንሿ ፓርላማ ሲትኮምን ፣ አራዳ ሲትኮምን ፣ ናዳ ቴአትርን የፃፍኩ ሲሆን ሌሎች የዶክመንታሪ ፊልሞችን ና ማስታወቂያዎችን ፅፌ ዳይሬክት አድርጊያለሁ። 


በዚሁ ስራ ላይ ሳለሁ በጉራጌ ላይ መሠረቱን ያረገ ሚድያ አለመኖሩን ሣይ ና የቆየው የጉራጌ ህዝብ ማንነትና ባህል እየተሸረሸረ መሆኑን ስረዳ "ለአካባቢዬ ምንድነው መስራት ያለብኝ?" ብዬ ካሠብኩ በኋላ የዛሬ ሶስት አመት የቤቶች ድራማ ተዋንያንን ወደ ዞናችን በመውሰድ ትልቅ የመስቀል በአል የቲቪ ፕሮግራም አቅርቢያለሁ። 

በመቀጠልም ከወራት በፊት እንደ አዲስ ስራዎችን በማዋቀር የዞናችንን ከተማዎች በዶክመንታሪ ፊልም የማሣየት ሀሣብ ይዤ በመነሣት የጉንችሬ ና የእምድብር ከተማን ሰርቻለሁ።

ስራዎቼን ለመመልከት ይሄን ሊንክ ይጫኑ
https://www.youtube.com/channel/UCLllNUL5gBerQDZQ6U0AbSQ

በመቀጠልም በጉራጌ ህዝብ ዘንድ የሚጠቀስ የታሪክ አሻራ ያኖሩ ሠዎችን ታሪክ ቀርፀን ማስቀመጥ አለብን በሚል መነሻ ከአርቲስት ደሣለኝ መርሻ ጀምሬ የተለያዩ ሠዎችን ኢንተርቪው አድርጌ ለህዝብ አቅርብያለሁ። የጉራጌ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ ሲነሣም ጉዳዩን ለአለም ለማሣየት እንዲያስችል ወደ ገጠሩ ገብቼ የሀገር ሽማግሌዎችንና ወጣቶችን በመጠየቅ ይሄንንም ከከተማ ምሁራን አስተያየት ጋር በማሠናሠል አቅርብያለሁ። በቅርቡም የተከበረውን የጉራጌ ህዝብ የአንድነት ና የእርቅ ክብረበአል የሆነውን "ፈቸት ኬርታ" ከሀሣብ ጥንስሱ ጀምሮ ተከታትዬ ለህዝብ ማቅረቤ ይታወቃል። ከዚ ጎን ለጎንም ከአለምአቀፍ የጉራ ማህበር ጋር በመተባበር በአብዛኛዎቹ የጉራጌ አካባቢዎች በመዞር የሠራሁት "ጎጎት" ዶክመንታሪ ፊልም ተጠቃሽ ነው። እነዚህ ስራዎች በህዝብ ና በመንግስት ላይ የፈጠሩት ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ፍርዱን ለህዝብ መተው እመርጣለሁ።

ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ ተቀዛቅዞ የቆየውን የጉራጊኛ ሙዚቃ በማነቃቃት አዳዲስ ሙዚቃዎች ለማቅረብ ና ክሊፕም ለመስራት ጥረት አድርጌ ስራዎቹ በህዝብ ተወዳጅነት አትርፈዋል። አርቲስቶቹም ተነቃቅተው በአዲስ ሀይል ለስራ ተነስተዋል።

የስራዬ መዳረሻ የራሴ ትልቅ ሚድያ ማቋቋም ሲሆን በየዘርፉም ሰፋ ያሉ ስራዎችን ለመስራት አስባለሁ። እነዚህን ሁሉ ስራዎች ስሰራ የቆየውት በአብዛኛው በራሴ ወጪ የተቀረውን ደግሞ በጥቂት ሰዎች የግል አስተዋፅኦ ነው። ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ መሠረት በሌለው መልኩ የአንድ ህዝብ ሚድያ ሆኖ መቀጠል ከባድ በመሆኑ የህዝብ እርዳታ ና ትብብር እፈልጋለሁ። ተባብረን ከሰራን የማንቀይረው ታሪክ አይኖርም ብዬ አምናለሁ። ያን ማድረግ ካልቻልን ግን ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየው የጉራጌ ማንነት እንዳይጠፋ እሰጋለሁ።

በዚህ አመት ውስጥ ልሰራ ካቀድኳቸው ስራዎች መሀከል ከስር የተገለፁት ሶስት ስራዎች ዋነኞቹ ናቸው።

1ኛ እማት ጉራጌ የሞባይል አፕሊኬሽን

⭐ የጉራጌ ባህሎች

✅ በዚህ ምርጫ ስር የጉራጌ ባህሎች ይዘረዘራሉ። ማብራርያ ና  በባህሎቹ ላይ የተሠሩ ጥናታዊ ፅሁፎችን ያገኛሉ።

✅ በተናጠል የእያንዳንዱን ባህል አከዋወን የሚያሣዩ አጫጭርና ረጃጅም ዶክመንታሪ ፊልሞች ያገኛሉ።

⭐ የጉራጌ ከተሞች

✅ በሁሉም የጉራጌ ከተሞች ላይ በተናጠል የተሠሩ ዶክመንታሪ ፊልሞችን ያገኙበታል።

✅ ስለ ከተሞቹ ነባራዊ ሁኔታ ፣ መልካዓ ምድር ፣ የቱሪስት ና የኢንቨስትመንት አማራጮች የተብራራ የፅሁፍ መግለጫ ያገኛሉ።

✅ ከአፕሊኬሽኑ ሳይወጡ የከተማውን አስተዳደር ወይም የመረጡትን ቢሮ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።

⭐ የቱሪዝም መዳረሻዎች

✅ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚያሣዩ ዶክመንታሪዎች

✅ በቱሪዝም መዳረሻዎቹ አቅራቢያ ያሉ ሎጅና ሪዞርቶች

✅ ሊሣተፉባቸው የሚችሉ አመታዊ ፌስቲቫሎች

2ኛ - "የጉራጌ መንገድ ስራ ድርጅት ከየት እስከ የት?" ዶክመንታሪ ፊልም

በኢትዮጵያ ውስጥ ከተቋቋሙ ሀገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ ተጠቃሽ የሆነው የጉራጌ መንገድ ስራዎች ድርጅት ብዙ ልማትን የሠራ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ታሪኩን በዶክመንታሪ ፊልም መስራት ከጀመርኩ ወራት ተቆጥረዋል። በእናንተ እገዛ በቅርቡ ይጠናቀቃል።

3ኛ "ጉራጌ ና መርካቶ"

መርካቶ ለጉራጌ ምን ማለት እንደሆነ መቼም አጠያያቂ አይደለም። ይህ ዶክመንታሪም ጉራጌ የመርካቶን ምድር ከረገጠበት ጊዜ አንስቶ በሴራ እስከ ተገፋበት እእከ አሁኑ ዘመን ድረስ ያለውን ታሪክ ያሣያል።

እነዚህን ስራዎች በአግባቡ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ በመሆኑ የእናንተን እገዛና ድጋፍ እጠይቃለሁ። በስራዎቼ የምትተማመኑ ወዳጆቼ የምትችሉትን በማበርከት የ ዩቱዩብ ቻናላችን የክብር አባል ይሁኑ።


አመሠግናለሁ
ተስፋ ነዳ
ደራሲና ዳይሬክተር
ስልክ 0924410897
Facebook : Tesfa G Neda
Email :   [email redacted]
#እማት_ጉራጌ

Donations

 See top
 • LUNDAT BIZA 
  • $50 
  • 2 hrs
 • birhanu shikur 
  • $200 
  • 7 hrs
 • Marigeta Moshe  
  • $90 
  • 7 d
 • Fasika Gebremichael  
  • $50 
  • 11 d
 • Berhanu Kereta 
  • $50 
  • 11 d
See all

Organizer

Mikias Getachew 
Organizer
Alexandria, VA
 • #1 fundraising platform

  People have raised more money on GoFundMe than anywhere else. Learn more

 • GoFundMe Guarantee

  In the rare case that something isn’t right, we will refund your donation. Learn more

 • Expert advice, 24/7

  Contact us with your questions and we’ll answer, day or night. Learn more