የአሰቦት ደብረ ራማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ከመፍረስ እንታደገው

  • R
  • b
139 donors
0% complete

$7,776 raised of $20K CAD

የአሰቦት ደብረ ራማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ከመፍረስ እንታደገው

Donation protected

ኦርቶዶክሳዊ ቁጭት የወለደው ተጋድሎ!

................ ........... ..............................

ስለ እመብርሃን #Share በማድረግ ይተባበሩ።


አምና በ2016 ዓ.ም በምዕራብ ሐረርጌ በሚኤሶ ወረዳ የሚገኘው የአሰቦት ደብረ ራማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ልጆች በስራ ፣በትምህርትና በተለያየ ምክንያት በተለያየ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ የአሰቦት ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በሚያዚያ ወር ከያሉበት ተጠራርተው ካሳደጋቸው ደብር ደብረ ይድራስ ከተሙ።


ሲገናኙ የተፈጠረው ስሜት የደስታም የጥልቅ ሀዘንም ነበር። በመገናኘታቸው ቢደሰቱም ጥቂት ኦርቶዶክሳውያን እና ብዙ አሕዛብ በሚኖሩባት ከተማ አብሮ አደግ ጓደኞቻቸው፣ የሰንበት ትምህርት ቤት እህትና ወንድሞቻቸው በጋብቻና በተለያየ የኑሮ ውጣ ውረድ ምክንያት ከሃይማኖት ወጥተው (ወደ አሕዛብ ቤተእምነት ተቀላቅለው)አገኟቸው።

አስተውሉ ኦርቶዶክሳውያን ያሉት ምእመናን በቁጥር እጅግ ጥቂት ቢሆኑም ከእነርሱ ውስጥም ደግሞ ወደ አእዛብ እምነት የሚጨመሩት ቁጥር እየጨመረ መጣ


ይህ እጅግ ልብ የሚሰብር ነበር። አስተማሪ በማጣት ትላንት በቤተመቅደሱ ሲያገለግሉ የነበሩ ወጣቶች ዛሬ በሌላ በረት ገብተዋል። ይህንን ማየት እጅግ ከባድ ሕመም ነበር


እናም በወቅቱ እነዚህ ወጣቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው አሰቡ። በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት በማኅበራቸው ማኅበረ ጊዮርጊስ አማካኝነት ከደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት በጋራ በመሆን እነዚህ ተግባራት በፍጥነት ለመጀመር ቃል ገቡ:-


1ኛ መፍትሔ ያሉትን ሕጻናትና ወጣቶች ለመጠበቅ ዞሮ ከወላጆቻቸው ጋር በመነጋገር ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት በማምጣት በደብሩ ያሉ ዲያቆናት እንዲያስተምሯቸው ማድረግ። ከኑሯቸው ጋር እየታገሉ ጥቂት ወንድሞች የሰንበት ትምህርት አገልግሎቱን ለማስቀጠል ቢሞክሩም ማስቀጠል አስቸጋሪ ነበር።ነገር ግን አሁን የፈተናው ክብደት በማስዳት ዋጋ በመክፈል ማስተማር እንዲጀምሩ ማድረግ። ይህም ወዲያውኑ ተጀመረ።


2ኛ የመጡት ልጆች የመማሪያ አዳራሽ ስለሌላቸው በፍጥነት አዲስ አዳራሽ መገንባት።

አሁን ተሰባስበው የሚማሩት በዛፍ ስር ነው


3ኛ ሊፈርስ የተቃረበውን ህንጻ ቤተመቅደስ ማደስ።

ዕለት ዕለት ለኪዳን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሚገኙ እናትና አባቶች አያድሱት ነገር አቅም አጠራቸው በቁጥርም ጥቂት ናቸውና። አሁን ከአሁን በላያችን ላይ ፈረሰ እያሉ እየተጨነቁ ስለሆነ ቶሎ በማደስ ብርታት መሆን። የዚህ ተግባር (ማደስ) ትልቁ አላማ ከባድ ቢሆንም ለእናትና አባቶች ትልቅ መነቃቃት መፍጠር ነው።

የመረሳት፣የመተው ስሜት ውስጥ የነበሩ ምእመናን

የእድሳቱን መጀመር ካዩ በሗላ የደስታ እንባ ሲያነቡ መመልከት ተችሏል የማይቻል የመሰላቸው ሆኖ ሊያዩት ነው።


4ኛ በአማረኛ እና በኦሮምኛ በሁለቱም ቋንቋ የሚያስተምር መምህር መቅጠር።


ወጣቶቹ ሳይውል ሳያድር ጊዜ የማይሰጥ ነውና ካላቸው ላይ ቀንሰው ሳይሆን ያላቸውን በመስጠት ወዲያውኑ ስራውን ጀምረዋል። አሁን ላይ ግን አቅም አንሷቸዋልና አብሮነታችንን እናሳያቸው በእውነት።


❤ ከላይ ለተጠቀሱት ለነዚህ ተግባራት የሚውል ለአዳራሽ ግንባታና ለቤተ ክርስቲያን እድሳት የገንዘብ ድጋፍ አነሰ በዛ ሳትሉ አቅም በፈቀደ ሁሉ እንድታግዙ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።


❤በሁለቱም ቋንቋ ለሚያስተምር መምህር ወርኃዊ ክፍያ መቻል የምትፈልጉ ማኅበራትና ምእመናንም ድጋፍ አድርጉ።


ድጋፍ ለማድረግ


1000639112725 CBE ማኅበረ ጊዮርጊስ


ለበለጠ መረጃ:- +251960792516


❤ የደብሩ አባቶች ካህናትን ጥሪ ከታች Video ይመልከቱ


=======================


#Share በማድረግ በቅዱስ ጊዮርጊስ ይተባበሩ!!


...........

Organizer

Yishak Shitaye
Organizer
Brooks, AB

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee