- F
- M
- E
EMS እስካሁን ተጉዟል ለመቀጠል ደግሞ ድጋፋችሁን ይሻል!
EMS በከፍተኛ መሠናክል፣ በጥቂት የፋይናንስ አቅምና እጅግ ፈታኝ በሆነ ጉዞ አመታትን ተሻግሯል። በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ውስጥ በሚዲያ ዘርፍ የነበረንን ሚና ለሃገራዊ ሃላፊነትና ፕሮፌሽናሊዝም ለማዋል በከፍተኛ ፍላጎት እና ተስፋ ተነስተን እየሰራን ቆይተናል።
ህዝባችን በገጠመው የህልውና ስጋት ፣ በሀገሪቱ የተንሰራፋው የጦርነት ፣ የመፈናቀል እና ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የህዝብን ችግር እንድናስቀድም ፣ ባለን ትንሽ አቅም በብዙ መስዋዕትነት እንድንደክም ቢያበረታንም ፤ የአቅም ውስንነት ግን በሚፈለገው መጠን ሊያራምደን አልቻለም።
ያለፉትን ሁለት አመታት ያለተጨማሪ ገቢ ማሰባሰቢያ ያለውን አቅም አሟጦ ያገለገላችሁ የናንተው ድምፅ የሆነው EMS ድጋፋችሁን ይሻል።
ለግፉአን ድምፅ የሆነ ኢትዮጵያዊነትን እኩልነትን፣እና ፍትሐዊነትን የሚያቀነቅን ሃገራዊ ሚዲያ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።
ለፍትህ እንቆማለን! ዕውነትን እንዘግባለን!
የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ (EMS)
Organizer
C
Corporation for Public Media Inc
Beneficiary


