
Support Mengistu's Fight for Life
Donation protected
የ4 ጨቅላ ልጆች አባት የሆነው መ/ር መንግስቱ መግሶ በመምህርነት ሙያ በቅንነትና ታማኝነት አገርን እያገለገሉ ባሉበት በድንገት ሁለቱም ኩላሊቶቹ ሥራ በማቆማቸው በከባድ ህመም ውስጥ ሆኖ ከእግዚአብሔር በታች የእናንተን ደጋግ ኢት/ያዊያንን እጅ እየተጠባበቀ አልጋ ላይ ይገኛል::የእርሶ ጥቂት ድጋፍ የመ/ር መንግስቱ መግሶን ህይወት ሊያተርፍ ይችላል!!
የወንድማችንን መ/ር መንግስቱ መጊሶ ህይወት ለመታደግ አገር ቤት ባሉ ጥቂት ወገኖች መልካምነትና ተነሳሽነት የተጀመረው እጅግ አድካሚና እልህ አስጨራሽ የገንዘብ ማሰባሰብ ህደት አሁንም እንደቀጠለ ነው!!
ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ድካምና ውጣውረድ የተሰበሰበው ገንዘብ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር ብቻ በመሆኑና ለመ/ር መንግስቱ መግሶ የኩላሊት ንቅለተከላ ከተጠየቀው ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ገደማ የጎደለ በመሆኑ ይህንን ጉድለት በመሙላት የወንድማችንን ህይወት ለማዳን ዛሬ በይፋ gofundme ከፍተናል!! በተለያየ ምክንያት ኢት/ያ ባለው በመ/ር መንግስቱ መጊሶ አካውንት በቀጥታ ገንዝብ ማስገባት ያልቻላችሁና ያልተመቻችሁ በሰሜን አሜሪካ: በአውሮፓና አረብ አገሮች ውስጥ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን ወገኖች እባካችሁ ከ10 እና 20 ዶላር ጀምራችሁ በgofundme እንድትረዱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን:: የመ/ር መንግስቱ መግሶ አካውንት ቁጥር CBE፦ 1000150452407
ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና። ምሳሌ 22:9
Organizer
Tamene Tessema
Organizer
Dallas, TX