- A

Support Henock's Life-Saving Kidney Transplant
0% complete
$39,207 raised of $40K
225 donations
በአስቸኳይ የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገውን የሄኖክ ደሊልን ህይወት ለማትረፍ ይርዱን::
ውድ ወዳጆቻችንን እና ሩህሩህ ልብ ያላችሁ ደጋጎች በሙሉ በአሁኑ ወቅት ተወዳጅ የትዳር አጋር፣ አባት እና ጓደኛ የሆነው ሄኖክ ደሊል በህይወት ለመቆየት ከባድ ትግል እያደረገ ይገኛል፡፡ የሄኖክ ኩላሊቶች ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆሙ በመሆናቸው በአስቸኳይ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል፡፡ ያለዚህ ቀዶ ህክምና የጤና ሁኔታው በባሰ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይሄዳል፡፡
ይህ አመት ሄኖክ እና መላው ቤተሰቡ ለመሸከም የሚከብድ ከባድ ፈተና እና ዱብ እዳን ለመጋፈጥ የተገደዱበት አመት ነው፡፡ በሰኔ 2017 ዓ.ም ቤተሰቡ ልብ በሚሰብር ድንገተኛ አደጋ የ5 ዓመት ወንድ ልጁን ተነጥቋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም በቀጠለው የጤናው መታወክ ምክንያት ሄኖክ ወደ ስራ ገበታው መመለስ አልቻለም፡፡ ቤተሰቡ ያን ከባድ ሀዘን መሸከሙን እንደቀጠለ አሁን ደግሞ ሄኖክ ለህይወቱ እጅግ አስጊ የሆነ የጤና ችግር ጋር እየታገለ ይገኛል፡፡
የኩላሊት ንቅለ ተከላውን ሂደት ወደሚጀምርበት ኢትዮጵያ ጉዞ ከማድረጉ በፊት ሄኖክ በአሜሪካ ከሐኪሙ ጋር አስፈላጊውን የህክምና ምርመራዎች እና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምናዎችን አድርጓል፡፡
ነገር ግን በቴነሲ ግዛት ውስጥ ያለው የንቅለ ተከላ ጥበቃ ተራ እጅግ በጣም ረጅም ነው - ቢያንስ 10 ዓመታት። ሄኖክ ይህን ያህል ጊዜ መጠበቅ አይችልም። በዚህም ምክንያት ኩላሊቷን በልግስና ከምትሰጠዉ እህቱ ጋር በመሆን የንቅለ ተከላውን ሂደት ለማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል። ሁሉም ዝግጅቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ወደ ህንድ ለንቅለ ተከላው ይጓዛሉ.
ለሄኖክ ኩላሊት የምትለግሰው እህቱ ስትሆን የእርሷ ኩላሊት ከሄኖክ አካለዊ ሁኔታ ጋር ተስማሚ መሆኑ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡ ሄኖክ በህይወት ለመትረፍ ያለው ሁነኛ አማራጭ በህንድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ሲሆን በህንድ የሚደረግለት ይህ ህክምና በተሻለ መልኩ በፍጥነት እና በወጪ ረገድም ከሌሎች ቦታዎች ዝቅ ባለ ወጪ መከናወን የሚችል ህክምና ነው፡፡ነገር ግን በዚህ አማራጭ ለህክምናው፣ ለጉዞው እና ለቀዶ ጥገናው በኋላ ያሉ ወጪዎች እጅግ ከፍተኛ በቤበተሰቡ አቅም መሸፈን የማይችሉ ናቸው፡፡
በመሆኑም ለሄኖክ በህይወት ለመትረፍ ወሳኝ በሆነው በዚህ ጊዜ የእናንተን ርህራሄ እና ድጋፍ ከምንም በላይ እንሻለን፡፡ አቅማችሁ በፈቀደው መጠን ሁሉ የምታደርጉት ማናቸውም የገንዘብ አስተዋጽዖ ሄኖክ በህይወት እንዲቆይ፣ እንዲፈወስ እና ከቤተሰቡ ጋር ቀሪ ህይወቱን እንዲያሳልፍ ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡ ለጋስነታችሁ በእውነትም አንድ ለመትረፍ ትገል ላይ ያላችን ህይወት የሚያድን መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡
ሄኖክ እና ቤተሰቡን በጸሎታችሁ እንድታስቡን እንጠይቃለን፡፡ በዚህ እጅግ ጭንቅ በሆነ ጊዜ ከሄኖክ ጎን በመቆማችሁ ከልብ እናመስግናለን፡፡
ለድጋፋችሁ ታላቅ ምስጋናን እናቀርባለን፡፡
Dear friends and compassionate supporters,
We are reaching out for help on behalf of Henock Delill, a loving husband, father, and friend who is now fighting for his life. Henock’s kidneys have completely failed, and he urgently needs a kidney transplant. Without this surgery, his condition will continue to worsen.
This year has already brought unimaginable pain to Henock and his family. In June 2025, they suffered the tragic loss of their 5-year-old son in a heartbreaking accident. Since then, due to ongoing health issues, Henock has been unable to return to work. As the family continues to grieve this devastating loss, he is now facing a life-threatening medical battle.
Before traveling to Ethiopia to begin the transplant process, Henock completed all necessary evaluations and primary treatments with his doctor in the United States. but the transplant waiting list in Tennessee is extremely long — at least 10 years. Henock cannot wait that long. Because of this, he is now in Ethiopia, completing the medical steps needed for the transplant process with his sister, who is generously donating her kidney. Once all preparations are complete, they will travel to India for the transplant.
His sister, who is a matching donor, is donating her kidney to save his life. His best chance for survival is to undergo the transplant in India, where the procedure can be completed more quickly and at an affordable cost. However, even with this option, the medical, travel, and post-surgery expenses are overwhelming.
We are asking for your kindness and support during this critical time. Any amount you can contribute will help give Henock the chance to live, heal, and remain with his family. Your generosity can truly save a life.
Please keep Henock and his family in your prayers. Thank you for standing with them during their darkest moment.

