
Support Hayat St. Michael & Washa Abune Hara Dengel Church
Donation protected
A Sacred Discovery, A Community in Need
In the heart of Hayat Shore, a remarkable discovery has brought spiritual significance to the community: the Ark (ፅላት), revealed through a monk's visionary dream from Etisa Teklehaimanot Monastery. Unearthed near the Gewasa River, alongside ancient monk caves, the Arks now reside in the humble "መቃኞ ቤተክርስቲያን" (Meqagno Bete Kirstian), established on February 23, 2015 (Gregorian Calendar).
Debreselam Kidus Michael & Abune Hara Dengel Church is a beacon of faith and healing, drawing pilgrims seeking spiritual solace and physical well-being. However, the church faces a critical challenge: it's situated on a tiny plot of land, hindering its ability to serve the growing community.
Our Urgent Plea for Support
We are reaching out to you for help to expand and develop this sacred space. To achieve this, we need to purchase land from neighboring farmers. Your generous donations will enable us to build:
- A Proper Church Building: The current "መቃኞ ቤተክርስቲያን" is a small, inadequate structure. We urgently need to build a larger, traditional oval church to accommodate the increasing number of worshippers.
- A Guest House for Pilgrims: Many travel long distances seeking healing through the church's spiritual water. A guest house will provide them with much-needed accommodation.
- Priests' Dormitory: Our dedicated priests need a safe and comfortable place to rest, as they conduct frequent overnight services.
- Educational Facilities: We are committed to training future priests through "አብነት እና ሰንበት ትምህርት ቤት" (Abnet and Sunday School). Currently, children learn under trees. Your support will help us build proper classrooms.
- Modernized Spiritual Water Bathing Center: We want to provide a hygienic and safe environment for those seeking healing through the spiritual water.
Every Donation Makes a Difference
Your contribution, no matter the size, will directly impact the lives of countless individuals seeking spiritual and physical healing. Together, we can transform this sacred site into a thriving center of faith and community.
Please Donate and Share
Help us build a sanctuary for Debreselam Kidus Michael & Abune Hara Dengel Church. Share this campaign with your friends and family, and let's work together to make a lasting difference.
Thank you for your generosity and compassion.
የአያት ሾሬ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ዋሻ አቡነ ሐራ ቤተክርስቲያን አመሰራረት ለየት ያለ ትዝታ ያለው ነው፡፡ በገዋሳ ወንዝ ዳርቻ ላይ እረኞች የሚውሉበት ዋሻዎች ያሉ ሲሆን በነዚህ ዋሻዎች ውስጥ ለብዙ ዘመናት ተቀብረው የቆዩ ጽላቶች እንዳሉ በራዕይ የተገለጸላቸው የደብረ ጽላልሽ ኢትሳ ተክለሃይማኖት ገዳም መነኩሴ በራዕያቸው መሰረት ቦታው ላይ መጥተው ታቦታቱን አውጥተው በየካቲት 16፣ 2007 ዓም መቃኞ ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ታቦታቱ ገብተዋል፡፡ በመነኮሳት ከረጅም ዘመናት በፊት ከቋጥኝ ተፈልፍለው የተሰሩ የመነኮሳት ባእቶችም ቦታው ላይ ተገኝተዋል፡፡
የአያት ሾሬ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ዋሻ አቡነ ሐራ ድንግል ቤተክርስቲያን የእናንተን እርዳታ ይፈልጋል፡፡ በአሁን ሰአት ቤተክርስቲያኑ አንድ ደብር ሊሟላለት የሚገባ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የሚያስችል በቂ መሬት የሌለው እንዲሁም በዙሪያው ያሉ አርሶአደሮች በመጠነኛ ዋጋ ለመሸጥ ፍላጎት ቢኖራቸውም በገንዘብ ችግር ምክንያት ለመግዛት አልተቻለም፡፡ በመሆኑም በእናንተ እርዳታ መሬት ከአርሶአደሮች ላይ በመግዛት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መሰረተ ልማቶች ማልማት ለነገ የማይባል ግዴታችን ነው፡፡
- የአቡነ ሐራ ድንግል ጽላቱ ያለበት መቃኞ ቤተክርስቲያን ግማሽ ዋሻ እና ግማሽ በቆርቆሮ የተሰራ እንደመሆኑ በየጊዜው ከሚመጣው ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር እና ከጻድቁ ክብር ጋር የማይሄድ እንዲሁም ወንዝ ዳር እንደመሆኑ በክረምት ሁሌም የጎርፍ ስጋት ያለበት በመሆኑ በእናንተ እርዳታ ከእናንተ ጋር ሆነን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ኀራ ድንግል የአባቶቻችንን ትውፊት ያማከለ ክብ ቤተክርስቲያን መገንባት ያስፈልጋል፡፡
- ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን የጻድቁን እምነት ተቀብተው እና በጸበላቸው ተጠምቀው ከተለያየ ደዌ ለመዳን እንዲሁም ከዲያብሎስ እስራት ለመፈታት በደብሩ ለአንድም ሆነ ለሁለት ሰባት ለመጠለል እና ለመዳን የሚመጡ ሲሆን ቦታው ወንዝ ዳር እንደመሆኑ ለአውሬ የመጋለጥ አደጋ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ መጠለያ ባለመኖሩ ለተለያዩ በዝርዝር ለመግለጽ የሚያዳግቱ ችግሮች እንዳይጋለጡ ደረጃውን የጠበቀ የጸበልተኞች መጠለያ መስራት ከእኛ የአቡነ ሐራ ወዳጆች ይጠበቃል፡፡
- በደብሩ የካህናት ማደሪያ ባለመኖሩ ካህናት ለዘውትር የለሊት መንፈሳዊ አገልግሎት ግርማ ለሊቱን እና ድምጸ አራዊትን ተጋፍጠው ከቤታቸው ሔደው እያገለገሉ ያለ ሲሆን ይህም አገልግሎቱን እያስተጓጎለ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሁላችንም የአቡነ ሐራ ወዳጆች ለነዚህ የኛን ሃጢያት ለማስተረይ ዘውትር ለሚተጉ የነብሳችን አባቶች ደረጃውን የጠበቀ የካህናት ማደሪያ መስራት ይጠበቅብናል፡፡
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ አደጋዎችን ተቋቁማ ለዘመናት የቆየችው አንድም በእግዚአብሄር ጸጋ እና ጥበቃ ሲሆን ሁለተኛው አባቶች ባስቀመጡልን ጥበብ መሰረት ተተኪ ካህናት በአብነት እና ሰንበት ትምህርት ቤት እየተማሩ እየበቁ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል፡፡ በዚህ ደብር ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎችም አንድም በምግባር ልጆቻቸውን ለማሳደግ እንዲሁም ተተኪ በማፍራት ክርስቲያናዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ልጆቻቸውን የሚልኩ ሲሆን ለዚሁ አላማ የሚውል መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት ልጆች በየዛፍ ስር እየተማሩ በመሆኑ የሚመጡትን ልጆች በሙሉ ለማስተናገድ እንዲሁም ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ተቸግረናል፡፡ በመሆኑም ደረጃውን የጠበቀ የአብነት እና ሰንበት ትምህርት ቤት መስራት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው፡፡
- በቅርቡ ጸጋ የበዛላቸው ምዕመናን የከርሰ ምድር ጸበል አስቆፍረው ያወጡ ሲሆን ወረፋ እና ግፊያን ለማስወገድ ደረጃውን የጠበቀ መጠመቂያ እና ጸሎት ማድረሻ ስዕል ቤት በመገንባት ከዚህም በላይ ቁጥር ያለው ሰው ወደ ቦታው መጥቶ እንዲድን ማስቻል ከእኛ የኦርቶዶክስ ልጆች የሚጠበቅ ምግባር ነው፡፡
የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ
መልአከ ታቦር መምህር እያሱ ሲሳይ
ስልክ: +251912247338
የህንፃ ኮሚቴ ሰብሳቢ
መምህር ፍሰሃፅዮን ክፍሌ
ስልክ: +251911803389
የህንፃ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ
አቶ ተስፋዬ ንጉሴ
ስልክ: +251910028900
Organizer and beneficiary
Abraham Zerihun
Organizer
Los Angeles, CA

Yinges Yigzaw
Beneficiary