$14,003 raised
·70 donations

Support Our Mother in Her Cancer Battle
Donation protected
በጌታ የተወደዳችሁ ወገኖች፣
የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ!
አባታችን ወ/ዊ ደሳለኝ ደምሴና እናታችን ወ/ ሮ ደስታ በዳዳ ከልጅነት እድሜአቸው ጀምሮ በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ላይ የቆዩና አሁንም እያገለገሉ የሚገኙ የወንጌል አገልጋዮች ናቸው። ብዙ ዘርፍ ካለው አገልግሎታቸውም መካከል በቤተ ክርስቲያን ተከላ፤ የወጣት አገልግሎቶችን በማደራጀትና በመምራት፤ በወንጌላውያን ክርስቲያኖች ኅብረት (EVASU) በተባባሪ አገልጋይነት እና የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትን አገልጋዮች በማሠልጠንና በማስተማር አገልግለዋል። ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ "ደወል የወንጌል አገልግሎት" የተባለ አገልግሎትን በመመሥረትና በመምራት የወንጌል ማድረስና ቤተ ክርስትያን ተከላ፣ መሪዎችና አገልጋዮችን በማሠልጠንና በማስተማር አገልግሎት ላይ ይገኛሉ ።
በአሁኑ ጊዜ እናታችን ወ/ሮ ደስታ በዳዳ ባጋጠማት የጤና እክል ምክንያት በህንድ አገር ህክምና እየተከታተለች ትገኛለች። ምንም አንኳን ነገሩ ከእቅማችን በላይ ቢሆንም እግዚአብሔርን በመተማመን ህክምናውን አስጀምረናል። ህክምናው ወደ ህንድ አገር መመላለስንም የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል።
ይህንን ሁኔታ የሰማችሁ ከአባታችንና ከእናታችን ጋር ያገለገላችሁ ወንድሞችና እህቶች "ሌዊ ርስቱ እግዚአብሔር ነው (ዘዳ 18:2 ) በምንችለው መጠን የፍቅር መግለጫችንን በማበርከት አብረናችሁ እንሆናለን" ብላችሁ ስለ አበረታታችሁኝ ይህን Account ከፍቻለሁ።
ከወላጆቻችን ጋር አብራችሁ ያገለገላችሁም ሆነ የተገለገላችሁ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር በፍቅር ያነሣሣችሁ ሁሉ በፍቅር ሥጦታችሁና በጸሎታችሁ አብራችሁን እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ።
ሁላችሁንም ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ! እላለሁ።
ባንቺአምላክ ደሳለኝ ደምሴ (ሰሜን አሜሪካ)
Evangelist Desalegn and his wife Desta are serving Jesus Christ in many-fold ministry fields.
Now Desta is seriously sick and is admitted in New Delhi hospital, India. We need your prayers and financial support to help cover Desta's medical expenses.
[Banchiamlak Desalegn Demissie is organizing this fundraising]
Donations
Organizer
Banchamlak Demissie
Organizer
Raleigh, NC