
በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው እገዛ እናድርግ!
Donation protected
ሰሞኑን በጎጃም ግንደወይን በምትባል ከተማ ላይ ያልታሰበ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ሰዎች ጥረው ግረው ያፈሩት ሀብት በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ወድሞባቸዋል:: በእዚህ የእሳት ቃጠሎ የተለያዩ የንግድ ሱቆች የወደሙ ሲሆን ከ30 ሚልየን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰ ተገልጿል:: ይህን ያህል ገንዘብ መልሶ ማግኘትና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መልሶ ማቋቋም ከወረዳዋ ህዝብ አንፃር ግዜ የሚወስድ እንደሆነ ይታወቃል::
ስለዚህም እኔ ሄኖክ አበበ ከአሁን በፊት የGofundme አካውንት ከፍቼ እርዳታ ሰብስቤ ባላውቅም አቅሜ በፈቀደው መንገድ ግን ለተለያዩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በተለያየ ግዜ እርዳታ ሳደርግ ነበር:: ዛሬ ግን የትውልድ መንደሬ ላይ የደረሰው ጉዳይ ስላሳዘነኝና ጉዳቱ የደረሰባቸው ሰዎች ብዙ ተስፋ ያላቸው በመሆኑና ብዙዎቹ ደግሞ ያላቸው ጠቅላላ ሀብት በመውደሙ እንደገና ለመቋቋም ከባድ ስለሚሆንባቸው ይሄንን በማሰብ ይህን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ከፍቻለሁ::
የምትሰጡት የእርዳታ ገንዘብ በግልፅነት ለተጎጂዎች እንዲደርስ እንደማደርግና ለዚህም ማረጋገጫ እዚሁ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በግልፅ እንደምለጥፍና እንደማሳውቅ ቃል እገባለሁ:: ለወንድሞቻችን እጃችንን እንዘርጋላቸው::
Organizer
Henok Abebe
Organizer
Hyattsville, MD