Raising Money for Girma Bihon

  • H
  • A
40 donors
0% complete

$5,420 raised of $20K

Raising Money for Girma Bihon





 

 
ጁ/ሌፍትናንት ግርማ ቢሆን ማን ነው?




ጁ/ሌፍትናንት ግርማ ቢሆን ለሀገሩና ለወገኑ ባለው ከፍተኛ ፍቅር በቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባል በመሆን ሰራዊቱን ከተቀላቀለ ጀምሮ አስፈላጊወን ትምህርትና ስልጠና በሚገባ ፈፅሞ በተመደበበተ የ 201 ስኳድሮን P-203 ተብላ በምትጠራ የጦር መርከብ ላይ ተመድቦ የተሰጠውን ግዳጅና ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት ላይ በነበረበት የቀይ ባህር የግዳጅ ቀጠና በደረሰበት  ጉዳት የቀኝ እግሩን በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳቱ በዚህም የተነሳ የቀኝ እግሩን በመቆረጡ በህክምና ቦርድ ከባህር ኃይሉ በክብር ከተሰናበተ በኃላ በነበረው ከፍተኛ የትምህርት ፍላጎቱ ትምህርቱን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመቀጠል ከአዋሳ ዩኒቨርስቲ በ Educational Leadership በማስትሬት  ዲግሪ ከተመረቀ በኋላ በዝዋይ የሆላንድ የእርሻ  ካምፖኒ ለአካባቢው ነዋሪዎች በከፈተው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በርዕሰ መምህርነት (በዳይሬክተርነት) በማገልግል ቤተሰብ መስርቶ ኑሮውን በተሟላ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ጋር በመዋደድና በመከባበር ለዓመታት እየኖረ በነበረባት የዝዋይ ከተማ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ምክንያት በማድረግ በተነሳው ማንነትን የተመረኮዘ ጥቃት በኢትዮጵያዊነቱና በኦርቶዶክሳዊ አማኝነቱ ጉዳት ሊያደርሱበት ከመጡት ጥቃት አድራሾች በአስተማራቸው ተማሪዎች ታዳጊነት የእሱና የቤተሰቡ ሕይወት ቢተርፍም ከላይ በተመለከተው ሁናቴ ቤቱና ንብረቱን በእሳት በማቃጠል ስላወደሙበት ከነቤተሰቡ በመጠለያ ይገኛል፤ ይህ ትሁትና ፅኑ የውድ ሀገሩ ባለውለታ የሆነ ወንድማችን የዛሬ አራት ዓመት የልብ ቀዶ ጥገና ህክምናም የአደረገ መሆኑን ተረድተናል ወንድማችን ግርማ በእግዚአብሔር ተፅናንቶ በእኛ በወገኖቹ አለንልህ ባይነት ወደ ቀደመው ኑሮው እናቋቁመው  ዘንድ የተቻለንን ሁሉ በመርዳት የወገን አለኝታነታችንን በመወጣት የበረከቱ ተሳታፊዎች እንሆን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን::

                                   

                                                              ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
 
 

Organizer

Zecarias Zewdie
Organizer
Chino, CA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee