- H
- A
ጁ/ሌፍትናንት ግርማ ቢሆን ለሀገሩና ለወገኑ ባለው ከፍተኛ ፍቅር በቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባል በመሆን ሰራዊቱን ከተቀላቀለ ጀምሮ አስፈላጊወን ትምህርትና ስልጠና በሚገባ ፈፅሞ በተመደበበተ የ 201 ስኳድሮን P-203 ተብላ በምትጠራ የጦር መርከብ ላይ ተመድቦ የተሰጠውን ግዳጅና ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት ላይ በነበረበት የቀይ ባህር የግዳጅ ቀጠና በደረሰበት ጉዳት የቀኝ እግሩን በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳቱ በዚህም የተነሳ የቀኝ እግሩን በመቆረጡ በህክምና ቦርድ ከባህር ኃይሉ በክብር ከተሰናበተ በኃላ በነበረው ከፍተኛ የትምህርት ፍላጎቱ ትምህርቱን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመቀጠል ከአዋሳ ዩኒቨርስቲ በ Educational Leadership በማስትሬት ዲግሪ ከተመረቀ በኋላ በዝዋይ የሆላንድ የእርሻ ካምፖኒ ለአካባቢው ነዋሪዎች በከፈተው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በርዕሰ መምህርነት (በዳይሬክተርነት) በማገልግል ቤተሰብ መስርቶ ኑሮውን በተሟላ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ጋር በመዋደድና በመከባበር ለዓመታት እየኖረ በነበረባት የዝዋይ ከተማ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ምክንያት በማድረግ በተነሳው ማንነትን የተመረኮዘ ጥቃት በኢትዮጵያዊነቱና በኦርቶዶክሳዊ አማኝነቱ ጉዳት ሊያደርሱበት ከመጡት ጥቃት አድራሾች በአስተማራቸው ተማሪዎች ታዳጊነት የእሱና የቤተሰቡ ሕይወት ቢተርፍም ከላይ በተመለከተው ሁናቴ ቤቱና ንብረቱን በእሳት በማቃጠል ስላወደሙበት ከነቤተሰቡ በመጠለያ ይገኛል፤ ይህ ትሁትና ፅኑ የውድ ሀገሩ ባለውለታ የሆነ ወንድማችን የዛሬ አራት ዓመት የልብ ቀዶ ጥገና ህክምናም የአደረገ መሆኑን ተረድተናል ወንድማችን ግርማ በእግዚአብሔር ተፅናንቶ በእኛ በወገኖቹ አለንልህ ባይነት ወደ ቀደመው ኑሮው እናቋቁመው ዘንድ የተቻለንን ሁሉ በመርዳት የወገን አለኝታነታችንን በመወጣት የበረከቱ ተሳታፊዎች እንሆን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን::
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

