አርቲስት ስዩም ተፈራ /ጋሽ ስዩም/ ትላንት በ EBS ምርጡ ገበታ የተሰኘ ፕሮግራም ላይ ቀርበው መታመማቸውን የስራ አጋራቸው ሲናገር ብዙዎች አይታችኋል።
ጋሽ ስዩም ወደ ውጪ ሄደው መታከም እንዳለባቸው ባልደረባቸው ሲናገር እሳቸው አንገታቸው ደፍተው እንባ ሲያቀሩ በማየታቸው ብዙዎች ልባቸው እጅግ አዝኗል። ጎ ፈንድ ሚ ክፈቱልን ከጎናቸው መቆም እንፈልጋለንም ባላችሁት መሰረት ይህንን ጎ ፈንድ ሚ ከፍተናል።
:
የተወደዳችሁ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራውያን ሁሉ በምንችለው ከእኚህ አንጋፋ የጥበብ ሰው ጎን እንድንቆም ፍቅራችንንም በዚህ አጋጣሚ እንድንገልፅላቸው በአክብሮት እንጠይቃለን።
Organizer
Mimi Tesfaye (Organizer)
Organizer
Folcroft, PA

