የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ) የአቅማችንን በመለገስ እናግዝ!

የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ)  የአቅማችንን በመለገስ እናግዝ! campaign photo, 1 of 4የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ)  የአቅማችንን በመለገስ እናግዝ! campaign photo, 1 of 4
የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ)  የአቅማችንን በመለገስ እናግዝ! campaign photo, 2 of 4

  • l
7 donors
Fundraiser’s main image
0% complete

$1,363 raised of 

‌

የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ) የአቅማችንን በመለገስ እናግዝ!

የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ) የአቅማችንን በመለገስ እናግዝ!

0% complete

$1,363 raised of 

7 donations
Donation protected
ወንድምን ማንሳት የወንድም ሀላፊነት ነው

ከጥቂት አመታት በፊት በኢቫንጀሊካል ቲቪ ይተላለፍ የነበረው ብዙ ዘማሪያን የወጡበት እጅግ ተወዳጁ የዜማ ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዳለ ወርቁ (ዳሽ) አቀራረቡ ማራኪ ቀለም ያለው ሆስት፤ እርጋታው ተመልካችን የሚስብ፣ የራሱን ለዛ የተላበሰ እንደነበር ሁላችንም እናስታውሳለን።

የፈጠራ አካሄዶቹ የሚተላለፉትን የዝማሬ ፕሮግራሞች ተወዳጅ እንዲሆኑ አድርጓቸው ነበር። በስቱዲዮ የመዝሙር አምልኮ ደረጃና በፕሮግራሙ ይዘት በደምብ ታስቦበት የሚያሰናዳ ፕሮግራም ያዘጋጅ ነበር። በዚህም ብዙዎች ዛሬ አብዝተን የምናዳምጣቸው ወጣት ዘማሪያን እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል።

እንዳለ (ዳሽ) የሚጋብዛቸው ዘማሪያን በፀጋ ከምንወዳቸው አንስቶ ማንም እስከ የማያውቃቸው አዳዲስ ዘማሪያን ድረስ የተውጣጡ ናቸው። በተለይ በየቤቱ የተደበቁ ዘማሪያን ጌታ በሰጣቸው ፀጋ ሲገለጡ ''የት ነበሩ እስከዛሬ?'' ብለናል። የፕሮግራሙ ይዘት አምልኮን፣ ምስክርነትን፣ የአገልግሎት ተሞክሮን ማካፈልን፣ ምክርንና ኢንተርቪዎችን ያዘሉ ነበሩ።

የዛ ተወዳጅ ፕሮግራም አዘጋጅ ወንድማችን ዳሽ አሁን ያለበት ሁኔታ ጥሩ አይደለም። ለብዙዎቻችን በረከት የነበረ ልጅ አሁን ላይ እንኳን ፕሮግራም ለመስራት ይቅርና በግልም በብዙ አይነት ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ ይገኛል።

አሁን ላይ ይሄንን ወንድማችንን ለማገዝ እና ተወዳጅ ፕሮግራሙንም እንዲጀምር ለማድረግ በተለያዩ አገልጋዮች አማካኝነት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። ይህ የጎፈንድሚ አካውንትም ወንድማችንን ለማገዝ በእርሱ ፍቃድ የተከፈተ ነው። ወንድምን ማንሳት የወንድም ሀላፊነት ነውና፣ ለደከመ ቀኝን መስጠት የክርስቲያን ግዴታ ነውና ሁላችንም ቅዱሳን የአቅማችንን በመለገስ ከወንድማችን ጎን እንድንቆም አደራ እንላለን።
Donate

‌
‌‌
‌
‌‌
‌
‌‌
‌
‌‌
‌
‌‌

Organizer

Muluneh Taye
Organizer
Alameda, CA
  • Other
  • Donation protected

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee