Main fundraiser photo

Moges Tadese-Ethiopian National Team Soccer Player

Donation protected
እኛ የሰው ልጆች በሰው ልጅ የመኖር የጉዞ መስመር ሂደት ውስጥ ከፊት ለፊታችን ያለዕረፍት እየቆጠሩ ወደ እኛ በሚመጡት በእያንዳንዳቸው ሰከንዶች ውስጥ የሚመጣውን ፤ የሚፈጠረውንና የሚገጥመንን አንዳንችም ነገር ፈፅሞ አናውቅም ።

ብዙዎች በሰከንዶች ውስጥ ሚሊዮን ብሮችን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ያገኛሉ ።
ሚሊዮኖች በሰከንዶች ውስጥ በመራብ ፤ በመጠማት ፤ በጦርነትና በአደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ድንገት ያጣሉ ።
ብዙዎች ደግሞ በቀላል መንገድ ጤናቸውን ማግኘት እየቻሉ ቀላሉን መንገድ የቱ እንደሆነ የሚያሳያቸው አጥተው ጤንነታቸውን አጥተው ይኖራሉ ።

መቼም ይሄንን ሁሉ ማለት የፈለኩበትን ምክንያት ለምን እንደሆነ ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁኝ ።
ይሄ የኑሮ ጭንቀታችንን ፤ ድብርታችንን ብዙ ችግራችንን ይዘን የምንደበቅበት የምንወደው የእግር ኳሱ ወይም የስፖርቱ ዓለም መቼም የማይወስደን የማያደርሰን ጥግ የለም ።
ዛሬ ደግሞ የሁላችንንም እርዳታ ወደ ሚፈልገው እግር ኳስ ተጨዋቹ ወንድማችን ሞገስ ታደሰ ጋር ይዞን መጥቷል ።

በብዙ ሰዎች የማህበራዊ ድህረ-ገፅ መስኮቶች ላይ እንደተፃፈው በተለምዶ 6 ኪሎ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ሰፈር አካባቢ ተወልዶ ያደገው ወጣቱ ሞገስ ታደሰ ለቅ/ጊዮርጊስ ፤ ሲዳማ ቡና ፤ አዳማ ከነማ ፤ መብራት ኃይልና ለወልዲያ ክለቦች እንዲሁም ለኢትዮዮጵያ ብ/ቡድን በመጫወት የእግር ኳስ ህይወቱን ያሳለፈ ሲሆን በአንድ መልካም ባልሆነች ቀን ከሜዳ ውጪ በደረሰበት ድንገተኛ ከባጃጅ ላይ የመውደቅ አደጋ መነሻነት ምክንያት በአሁን ሰዓት ጤንነቱን አጥቶ በከባድ ህመም ውስጥ ሆኖ በቤቱ ከተቀመጠ ሰንብቷል ።

አሁን ያለበትም የጤንነቱ ሁኔታ በእጅጉ ከባድና አስቸጋሪ ስለሆነባቸው የብዙዎችን እርዳታ እንደሚፈልግ እሱ ቤተሰቦቹና ለእሱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ተናግረዋል ።
ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ በአሁን ሰዓት በወላጅ እናቱ በወ/ሮ ሰርካለም አለባቸው ቦጋለ ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ የባንክ የሂሳብ ቁጥርም ገንዘብ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴና ጥረት እየተደረገለት ነው ።

በዚህ በምንወደው እግር ኳስ ውስጥ ትላንት በፍጥነት ሲሮጥ ያወቅነውንና የተመለከትነው ሞገስ ታደሰ ዛሬ በቅፅበቶች ለመንቀሳቀስ እንኳን ከብዶታል ።
በፍጥነት እየሮጠ እየልቡ የሚያዘው ሰውነቱ ዛሬ ድካም ተሰምቶታል ። 
በአጠቃላይ ዛሬ ላይ ነገሮች ሁሉ በድንገት ለሞገስ ከባድ ሆነውበታል ።

ሁኔታዎች ሁሉ ድንገት ሳያስበው የተለወጡበትና ጤንነቱን ያጣው ወንድማችንን ዛሬ ላይ ጤንነቱን መልሶ ለማግኘት ሲል የወገኑን እርዳታ ጠይቋል ።
የሁላችንንም አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልገውን ወንድማችንን በመርዳት ኢትዮጵያዊነታችንን እናሳይ ።
ከሁላችንም የምትገኘው ትንሿ ነገር መጨረሻ ላይ ለእሱ ትልቅ ዋጋና ብርታት ትሰጠዋለች ። ይህ ጥሪ ሁሉንም የሚመለከት ቢሆንም እግር ኳስን ለሚወዱ ተጫውተው ያሳለፊ እንዲሁም በአሁን ሰአት በፕሪሜይሪሊጉ እና ሱፐር ሊግ የሚጫወቱ ተጨዋቾቻችን ሞገስ ካለበት ችግር እና የጤና እክል የማውጣት ሀላፊነት ይኖርብናል ። ይህን መልክት ሼር በማድረግ ለስፓርት ወዳዱ ማህበረሰብ እንድታደርሱልንም ጭምር መልእክታችንን እናስተላልፋለን። 
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Bizuneh Worku
    Organizer
    SeaTac, WA

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee