- H
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች በሙሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ።
እንደሚታወቀው የሁላችን መምህረ ወንጌል ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) በተለመደው የአገልግሎት ጉዞ ከኢትዮጵያ ውጭ ባለበት በድንገት ታሞ ጥቂት ቀናት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ያስቀመጠውን ሳያነሳ፣ ያቀደውን ሳይቋጭ፣ በድንገት ወደ ፈጣሪው በመጠራቱ ሁላችንም በጥልቅ ሀዘን ውስጥ መሆናችን ይታወቃል።
አሁን ልናሳስባችሁ የፈለግነው መምህር ዘላለም ወንድሙ በዓለም ሁሉ እየተዘዋወረ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያስተማረ ታማኝ አገልጋይ ወደ ጌታው ደስታ በክብር መግባቱን እያመንን በምድር ለምንቆየው ስሙን የምንዘክርበት የመታሰቢያ ሀውልት ለማሰራት በተጨማሪም የድሆች አባት ነበርና ሥራውን ለማስቀጠል እንዲቻል ገንዘብ ለማሰባሰብ Go Fund me በመክፈት ለበጎ አሳቢዎች ዕድሉ ተመቻችቷል። ሁላችሁም ከዚህ በረከት እንድትሳተፉ ዕድሜውን ሙሉ ባገለገለው በእግዚአብሔር ስም በአክብሮት እንጠይቃለን ። የአገልጋዩን ወልደ ሰማዕትን ነፍስ እግዚአብሔር በክብር ያሳርፍልን። አሜን።
[Organized by DSK Mariam EOTC, 1350 Buchanan St NW, Washington, DC 20011]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ஜ۩۞۩ஜ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
The Ethiopian Orthodox Church recently lost a beloved preacher, Deacon Zelalem Wondimu, who dedicated his life to serving God, helping others, and supporting important ministry work in Ethiopia.
To honor his legacy and continue the mission he cared so deeply about, we have created this fundraiser. If you are able, please consider donating and share the link with others. Every contribution helps keep his legacy and impact alive. Thank you for your prayers and support.
[Organized by DSK Mariam EOTC, 1350 Buchanan St NW, Washington, DC 20011]



