
Let Bobicho Mission Center Shine for Generations
Donation protected
Let’s make Bobicho Mission Center shine for generations
Dear, brothers and sisters,
As you know, Bobicho is a historic place and symbolizes the light-creating and life-giving impact of the gospel of Jesus Christ in what used to be a spiritually and socio-culturally dark part of Ethiopia. Bobicho is also a historic mission site. For example, it had the first Bible school and the first junior secondary school in the region. For the first time, 150 young men who committed themselves to the full-time evangelistic ministry were sent from Bobicho. Among those young men were Ababa Kedamo Mechato and Ababa Eyoel Fuge. Abba Gole, from Bobicho, was the first President of the Ethiopian Kale-Heywet Church.
About nine years ago, a decision was taken by the South Shewa regional office of the Ethiopian Kale-Heywet Church to build a Memorial Center in Bobicho. The Center is designed to house a ministerial training center, an archive collection room, a museum, prayer hall, guest accommodation, a meeting hall, and offices.
When completed, the Center will:
1. enable the church to archive and preserve its own history and traditions: stories, symbols, and traditions that stand as testimony to the origin, identity, and role of the Church, as represented by SIM and the Kale-Heywet Church;
2. help young people to understand about the transforming power of the gospel, be inspired by the stories told through the center, and commit themselves to the truth of the gospel;
3. serve as a ministerial training center, which will equip existing and prospective ministers for biblically founded and contextually relevant pastoral and leadership ministry;
4. serve as a Center for prayer and fellowship.
Over the past years, brother and sisters in Addis Ababa and around the Southern Shewa region have been doing their best to support the project with fundraising. Now, those of us who live abroad have organized ourselves at the global level and in 6 regions (South Africa, United Kingdom, Mainland Europe, Canada, USA, and Australasia) to raise funds for the completion of the project. The progress and results thus far have been encouraging. We would like to encourage you all to participate in this important cause and play your part. As Nehemiah said: ‘The God of heaven will make us prosper, and we His servants will arise and build…’ (Neh 2:20 ESV).
God bless you!
The Global Team
የቦቢቾን የወንጌል ታሪክ ለማደስና ለትውልድ ለማስተላለፍ ድርሻዎን ይወጡ
የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች፣
ሁላችንም እንደምናውቀው ቦቢቾ በመንፈሳዊና ማኅበራዊ ጨለማ ውስጥ በነበረው ህዝባችን መካከል ለፈነጠቀውና ለተቀጣጠለው የክርስቶስ ወንጌል ብርሃን መነሻም መገለጫም የሆነች ስፍራ ናት። በተጨማሪም፣ ቦቢቾ ታሪካዊ የሚሺን ማዕከል ናት። ለምሳሌም፣ በክልሉ የመጀመሪያዎቹ መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤትና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት አገልግሎት መስጠት የጀመሩት በቦቢቾ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሙሉ ጊዜያቸውን ለወንጌል አገልግሎት የሰጡት አንድ መቶ አምሳ ወጣት ወንዶች ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተላኩትም ከዚሁ ከቦቢቾ ነበር። ከእነዚህ ወጣት ወንዶች መካከል እነ አባባ ኬዳሞ ሜቻቶና አባባ እዩኤል ፉጌ ይገኙበታል። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የነበሩት አባ ጎሌ ኑነሞ የወጡትም ከዚሁ ከቦቢቾ የወንጌል ማዕከል ነው።
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ገደማ፣ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የደቡብ ሸዋ ቀጠና ጽሕፈት ቤት በቦቢቾ የእምነት አባቶችና እናቶች መታሰቢያ ማዕከል ለማሠራት ውሳኔ አስተላለፈ። ማዕከሉ በውስጡ የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማዕከል፣ የታሪካዊ መዛግብትና ቅርሶች መስቀመጫ ክፍል፣ ሙዚየም፣ የጸሎት አዳራሽና ክፍሎች፣ የእንግዶች ማረፊያ ክፍሎች፣ እንዲሁም መሰብሰቢያ አዳራሾችና ቢሮዎች እንዲኖሩት ተደርጎ የተቀረጸ ነው።
የግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅም ማዕከሉ፣
1. የቤተክርስቲያንን ታሪክ፣ ቅርስና ወግ ተንከባክቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ያስችላል። እነዚያ ታሪኮች፣ወጎችና ቅርሳዊ ምልክቶች የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊና ታሪካዊ እሴቶች ለማስቀጠል ከማገልገላቸውም በላይ በደቡቡ የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አካባቢዎች የቤተክርስቲያንን መነሻ፣ ማንነትና ሚና የሚያሳዩ ቋሚ ማስረጃዎች ሆነው ይቀጥላሉ።
2. ወጣቱ ትውልድ ሕይወት ስጪና ሕይወት ቀያሪ ስለሆነው የወንጌሉ ኃይል ሙሉ መረዳት እንዲኖረው፣ በአስደማሚ ታሪኮቹ እንዲነቃቃና እንዲነሳሳ፣ እንዲሁም ራሱን ለወንጌል እውነት እንዲያስገዛ ያግዛል።
3. ነባርና ተተኪ አገልጋዮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትና ማህበራዊ ፋይዳ ባለው አኳኋን ለመሪነትና መጋቢነት አገልግሎት የታጠቁና የበቁ እንዲሆኑ የሚያዘጋጅ የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።
4. የጸሎትና የጋራ አምልኮ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።
ባለፉት ዓመታት፣ በአገር ቤት በተለይም በአዲስ አበባና በደቡብ ሸዋ አካባቢዎች የሚገኙ ወገኖች ይህንን ፕሮጄክት በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በቴክኒክ አቅም በፈቀደ መጠን ሲደግፉ ቆይተዋል። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ፣ በውጭ አገራት የምንኖር ወገኖች ራሳችንን በዓለም አቀፍ ደረጃና በስድስት አህጉር-ተኮር ክልሎች በማደራጀት ለፕሮጄክቱ ማስጨረሻ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመሰብሰብ በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን። ክልሎቹም፦ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ክንግደም፣ አውሮፓ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስና አውስትራልኤዥያ (አውስትራልያና ኒውዚላንድ) ናቸው።
የእስካሁኑ እንቅስቃሴያችን እጅግ አበረታችና ውጤታማ ሊባል የሚችል ነው።ሁላችሁም ለዚህ በጣም አስፈላጊ ለሆነው ፕሮጀክት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር ጥሪያችንን እና ቀርባለን። ነህምያ እንዳለው፣ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሠራለን…” (ነህ 2፥20)።
የአለም አቀፉ ኮሚቴ
ማሳሰቢያ !!! ስጦታ በሚያደርጉበት ጊዜ ጎ-ፈንድ-ሚ የሚጠይቅዎትን ተጨማሪ ችሮታ (ቲፕ) መክፈል አይኖርብዎትም። ተጨማሪ ችሮታው (ቲፕ) ወደ ፕሮጀክቱ አካውንት ገቢ አይሆንም። ቲፕ ሳይጨምሩ ስጦታውን ለመስጠት የሚከተለውን ያድርጉ፤ ‘TIP’ ከሚለው መስመር ‘OTHER’ የሚለውን ከመረጡ በኋላ በቲፑ ሳጥን ውስጥ ዜሮ (0.0) ከሞሉ በኋላ የስጦታውን ገንዘብ በእርዳታው ቦታ ብቻ ይሙሉ።
Co-organizers (3)
Wondmagegn Tafesse
Organizer
Uppsala
Estifanos Biru Shargie
Co-organizer
Desta Heliso
Co-organizer