Main fundraiser photo

ምዕራብ ጎንደር የኢ\ኦ\ተ\ቤ\ክ ሀገረ ስብከት ገቢ ማሰባሰቢያ

Donation protected
ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዮሐንስ መልእክት

የምዕራብ ጎንደር ታሪካዊነት ባጭሩ

ታላቁ አፄ ቴዎድሮስ የተወለዱበት፥ አፄ ዮሐንስ መተማ ላይ የተሠውበት፣ ታላቁን ገዳም ማኅበረ ሥላሴን ጨምሮ ስድስት የአንድነት ገዳማት የሚገኙበት ፥ ከሦስት መቶ በላይ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙበት፥ በአሐዝ መግለጥ ባልችልም በግምት በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይሚኖርበት፥ ታሪካዊ ሀገረ ስብከት ነው። ከላይ እንደ ገለጽኩት ከነዚህ ከአራቱ ሀገረ ስብከቶች ሁለቱ ማዕከላዊ ጎንደርና ምዕራብ ጎንደር የሚመራው በእኔ በወንድማችሁ በአባ ዮሐንስ ነው።

የምዕራብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ግንባታዎች

1/ ሊቀ ጳጳሱ የሚኖሩበት መንበረ ጵጵስና፥

2/ ሀገረ ስብከቱ የሚገለገልባቸው ባለ 18 ክፍል ቢሮዎች፥

3/ አንድ ሽህ ሕዝብ ለማስተናገድ የሚችል ሁለገብ አዳራሽ። እነዚህን በቅደም ተከተል አቅደን በመሥራት ላይ እንገኛለን። መንበረ ጵጵስናውና የቢሮዎቹ ግማሽ ማለትም ዘጠኙ ክፍሎች ጣራቸው ቆርቆሮ ለብሷል።

ግንባታዎቹን ለመጨረስ ያጋጠመን ፈተና

አሁን በኢትዮጵያ ወቅቱ የክረምት መግቢያ ዋዜማው ላይ ነው። በመሆኑም በሮችና መስኮቶች ካልተዘጉ አውሎ ነፋስ ቆርቆሮውን ይገለብጥብናል ብለን ታላቅ ሥጋት ላይ ነን። አያድርገው እንጂ ይህ ከሆን ልፋታችን ሁሉ ከንቱ ይሆንብናል። በክርስቶስ ወንድሞችና እኅቶች! እየሠራን ያለነው የእግዚአብሔርን ሥራ ነውና ፥ በዚህ ወቅት የምትችሉትን ያህል እርዳታ ብታደርጉልን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን አስቀድመን እናቀርባለን። በክርስቶስ ወንድማችሁ የሆንኩት፦

አባ ዮሐንስ፥ የምዕራብ ጎንደርና የማዕከላዊ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ

የምዕራብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የባንክ ሂሣብ ቍጥር

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዳ ውኃ ቅርንጫፍ= 1000293156976

የሊቀ ጳጳሱ ስልክ ቍጥር 0901220190

We are raising money for supporting the Western Gondar Ethiopian Orthodox Church Diocese to finish the construction they started for the Diocese School and Archbishop office. Please take a look at the Video. The collected money is transferred through Mekane Birhan St Gebriel EOTC in Seattle to the Western Gondar EOTC Diocese. Any donation you make will help make an impact. 
This fundraising money covers the construction of a hall, school, and the office of the Archbishop. 
The money will be wired from Mekane Birhan Saint Gabriel account directly to the West Gondar ETOC Diocese commercial Bank of Ethiopia Account opened for this project.
One transfer is done the reciept willl be shared on this gofundme link.
Thank you and God bless you for your contribution to this cause.
May the blessing of the Archbishop of the Diocese, Abune Yohannes,  be with us.

The committees working on these fundraising are Dagem Tadesse, Meseret Tesfaye, Gashaw Andargie, Issayas Demoze, Bemnet Tesfaye, Tsega Desta and Girmachew Tefera Mekonnen.

If you prefer to transfer using  Zelle - 2064763591
Name - Mekane Birhan St Gebriel EOTC

Donate

Donations 

    Donate

    Organizer and beneficiary

    Issayas Demoze
    Organizer
    Seattle, WA
    Dagem Yalew
    Beneficiary

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee