- Y
- F

የሙዚቀኛ ምህረተአብን ህይወት እንታደግ
0% complete
$14,740 raised of $15K
215 donations
ወንድማችን ሙዚቀኛ ምህረትአብ ታዬ እጅግ የተባረከ ፣ትሁት ፣ የተረጋጋ ፣ አመለሸጋ ልጅ ሲሆን ለብዙ ዘማሪያን ሙዚቃን የተጫወተ፣ ረዘም ላለ ጊዜያት በሙዚቃው ዘርፍ ያገለገለ ወንድማችን ነው። የመጋቢ አገኘሁ ይደግ፤ የመጋቢ ታምራት ሐይሌ፣ የዘማሪ ወርቅነህ አላሮ፣ የዘማሪ ቴዲ ታደሰ እና ሌሎች በርካታ አልበሞች ላይ ሰርቷል። ብዙዎች የሚያውቁት የዘማሪት መስከረም ጌቱ "አይዞህ" ስራም የእርሱ ነው። ወንድማችን ከዚህ ስራ በኋላ ብዙ ዘማሪያን ለስራ ቢፈልጉትም ባጋጠመው ከባድ ህመም ምክንያት እንደበፊቱ መስራት አልቻለም።
ወንድማችን ምሬ ላለፉት ሰባት አመታት በጉሮሮ ካንሰር እየተሰቃየ ያለ ሲሆን ቤተሰቦቹም ሀገር ውስጥ ባሉ የተለያዩ ሆስፒታሎች ሲያሳክሙት ቢቆዩም ነገር ግን ከጊዜ ወደጊዜ የጤንነቱ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቶ አሁን ላይ ፈፅሞ መናገር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ብዙዎች ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ሁኔታውን አይተው ወደ ህዝብ እናድርስና ገንዘብ ሰብስበን ውጪ ሃገር እንድትታከም እናድርግ ቢሉትም ሰው ማስቸገር አልፈልግም ብሎ እስከዛሬ ድረስ ሳይታከም ቆይቶ አሁን ግን ህመሙ እየጸና በመሆኑ ውጪ ሄዶ መታከም ስላለበት በወዳጆቹ ሙዚቀኞችና ዘማሪያን ግፊት እንዲሁም በእርሱ ፈቃደኝነት ቅዱሳንን በማስተባበር ወንድማችንን ለማሳከም እንቅስቃሴ ጀምረናል።
ሙዚቀኛ ምህረትአብ ብዙዎችን የጠቀመ ስራን የሰራ ሲሆነ በአሁን ሰአት የሁላችም እርዳታና እገዛ የሚፈልግበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። አይዞህ በሚል ዝማሬ ከመስከረም ጋር እንዳፅናኑን እኛም የአቅማችንን በመለገስ ወንድማችንን ከዚህ ስቃይ እንድንገላግለው እንዲሁም ወደሚወደው አገልግሎቱ እንድንመልሰው አደራ ጭምር እንላለን። ከስር ባለው የወላጅ እናቱ የባንክ አካውንት የወንድማችንን ህይወት እንታደገው ዘንድ ጥሪ እናደርጋለን ።
