
Support Adebabay Media Project አደባባይ ሚዲያን ለመርዳት
Donation protected
አደባባይ ሚዲያ በኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ዜናዎችን፣ ሐታዎች፣ን ዘገባዎችን እና ጥናቶችን በላቀ ጥራት እና በብዙ ባለሙያዎች ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ማቅረብን ተልእኮው ያደረገ ለትርፍ ያልተቋቋመ (Nonprofit) ድርጅት ነው። በዚህ ዘመን መልካም ሕብረተሰብ ለመፍጠር ሚድያ ወሳኝ ሚና አለው። አደባባይ ሚድያ በወገንተኝነት ላይ የተመሠረተ፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት እውቀት እና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ የሆነ አማራጭ ሚድያ ሆኖ የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ (nonprofit organization) የሚድያ ተቋም ነው።
ግባችን ሀገራችንና ሕዝቦቿን የሚጠቅም ሁሉን አቀፍ፣ ሚዛናዊ መረጃና «የነጠረ እውነታ» ማቅረብ፣ በሀገራችን ስለሚደረገው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ» ኢኮኖሚያዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ለማንም ያልወገነ መረጃ በተለያየ መንገድ ማቅረብ ነው። ሥራ ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ነጻ የሕብተረሰብ በይነ-መረብ (internet) ወይም የማኅበረሰብ ትስስር መገናኛ መንገዶችን (Social Media) በመጠቀም የተለያዩ ዝግጅቶችን ስናቀርብ ቆይተናል። ይሁን እንጂ በፌስቡክ እና በዩ-ቲዩብ ብቻ ተወስኖ መረጃዎች ማስተላለፍ በቂ ካለመሆኑም በላይ አገልግሎታችንን ማስፋትና በበቂ የሰው ኃይል ማጠናከር አስፈላጊ ነው።
“የሁላችንም ስለሆነች ኢትዮጵያ በአደባባይ እንዘግባለን” የሚል መሪ መርህ ይዘን በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ለሌሎችም የዓለም ማኅበረሰብ ለመድረስ ዘመኑ የሚፈቅደው መገናኛ ዘዴዎችን ሁሉ ለመጠቀም የገንዘብ አቅም ውሱንነት አለብን። በሀገራችን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ተመልካቾቻችን በሳተላይት ቴሌቭዥንዝግጅታችንን ለማድረስ ዓላማችንን የተረዳችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ በጎ ሕሊና ያላችሁ ወገኖቻችን ሁሉ የቻላችሁን ያህል አስተዋጽዖ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
አደባባይ ሚዲያ፣ የሁላችን ስለሆነች ኢትዮጵያ።
(+1)
Email: [email redacted]/[email redacted]
www.adebabay.com
በሁሉም ማኅበራዊ ድረ ገጾች
@AdebabayMedia ቢሉ ያገኙናል።
Organizer
Ephrem Eshete Ephrem
Organizer
New Braunfels, TX