Main fundraiser photo

Honoring Teshome's Courageous Fight

Donation protected

Dear Friends and Family, With heavy hearts, we share the passing of our beloved Teshome Desta after a courageous battle with cancer. He leaves behind his loving wife, Zemenaye, and their three young children (ages 3, 4, and 11). Though he is no longer with us, his love and legacy continue through them.

 As Zemenaye faces the immense challenge of raising their children alone, she needs our support now more than ever. The road ahead is difficult, but together, we can help provide stability and comfort for their family.

 Please consider donating and sharing—every act of kindness makes a difference. Thank you for your love, generosity, and support.

ሰላም ወዳጆች፣ ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ?
ወንድማችን ተሾመ ደስታ በአሜሪካን ሀገር ቨርጂኒያ ግዛት ይኖር የነበረ ሲሆን ላለፈው አንድ አመት ተኩል ያህል ጊዜ ደረጃ 4 የጨጓራ ካንሰር ሲሰቃይ ቆይቶ እ.አ.አ.የካቲት 27፣ 2025 ከዚህ ዓልም በሞት ተለይቷል።

ወንድማችን ተሾመ 3 ህፃናት ልጆቹን (የ3፣ የ4 እና የ11 ዓመት) እና በቅርቡ ከኢትዮጲያ የመጣች ባለቤቱን ትቶ በህይወት የተለየን ሲሆን ለቤተሰቡም ብቸኛው መጋቢና ገቢ አምጪ ነበር። በመሆኑ የእሱ ህልፈት ቤተሰቡን ከባድ ሐዘን ላይ ከመጣሉም ባሻገር ለከፍተኛ ጭንቀት እና ችግር ዳርጓቸዋል።

ለጊዜው በቅርብ ያለን ጓደኞቹ ከቤተሰቡ ጎን በመቆም የተቻለንን እያደረግን እንገኛለን። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ቤተሰቡ ያለ ምንም የገቢ ምንጭ ባዶ ሜዳ ላይ ስለቀረ፤ ይህን ችግር በጥቂቱም ቢሆን ለመቅረፍ እና አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ለማለት ጎፈንድሚ ተከፍቷል::

ተሾመ ገና በመስሪያ ዘመኑ፤ እና ብዙ እቅዶች የነበሩት ወጣት ነበር። ጅማሬው የወደፊቱን ተስፋ የሚያሳይ የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ቅሪት ለልጆቹ ሳይተው ክፉ ሞት ቀድሞታል::

የተሾመ ባለቤት ዘመናይ ልጆቻቸውን ብቻዋን ለማሳደግ ከባድ የሆነ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ስለሆነም በዚህ ከባድ የሀዘን እና በጣም ፈታኝ ወቅት የእኛን ድጋፍ በእጅጉ ትሻለች። ስለሆነም እባክዎን የበኩልዎን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ በህፃና ልጆቹ እና በፈጣሪ ስም እንማፀናለን። ይህንን መልክት ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ እንድታደርሱ ስንል በትህትና እንጠይቃል። ማንኛውም ያክል የበጎ አድራጎት ለውጥ ያመጣል። ለፍቅራችሁ፣ ለልግስናችሁ እና ለድጋፋችሁ ክልብ እናመሰግናለን።
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Zemenay Yilma
    Organizer
    Burke, VA

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee