Main fundraiser photo

Helping Atsede's medical bill

Donation protected
የሴቶች ግፍ በካሜላትና በአፀደ ይብቃ!!
*************************************
ኣሁን የማካፍላቹ እውነተኛ ታሪክ ያልተለመደና ኣሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ ከታች የምታይዋት ኣፀደ ንጉሴ ትባላለች:: ተወልዳ ያደገችው በአዲግራት ከተማ 02 ቀበሌ እንዳባ ጎበዝ(ሐዱሽ ዓዲ) የሚባል ሰፈር እዛ ተወልዳ ያደገች ወጣት ናት:: ከ 1ኛ አሰከ 12ኛ ከፍል በአዲግራት ከተማ ጨርሳ ከዛ ወደ አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገባች:: በዛኔ በደረሰባት የጤና ችግር ትምህርትዋን አቋርጣ ወደ አገርዋ ተመለሰች:: ጤናዋ ከተሻላት በኃላ እህትዋን ለመጠየቅ ወደ ጅግጅጋ ሄደች::ከዛ ታላቅ እህትዋን ተቀብላ ትንሽ ስራ እንድትጀምረ አገዘቻት:: ትንሽ ከሰራች በኃላ ወደ ትዳር አለም ገባች:: አግብታም የአንድ የ 5 ዓመት ወንድ ልጅ እናት ናት:: ግን እንደዚህ ሁኖ እያለ የዚች እናት ባለቤት (ባልዋ) ልጁን አቅፋ ባሳደገችለት፥ በአዲግራት ከተማ ስራዋን ጨርሳ ወደ እናትዋ ቤት ስትገባ በእናትዋ ግቢ በሚገኝ ጓሮ ተደብቆ ቆይቶ( ተጠርጣሪ ባለቤትዋ ካሕሳይ ተክለሃማኖት) በ 3 ሊትር አሲድ ከጭንቅላትዋ ጀምሮ መላው ሰውነቷ እንደትቃጠል አስቦ አፈሰሰላት:: ሆኖም ግን የእግዚአብሄር ፍቃድ ሁኖ ፊትዋን:አይንዋን እና አንድ አንድ የሰውነት ክፍልዋ ጉዳት አድርሶ ሌላውነ የሰወነተ ክፈልዋ ግነ በልብሷ በመቃጠል ጩሀ ጎረቤት በመርዳት ህይወቷን ልትተርፍ ችላለች:: ይሁን እንጂ ይህ የደረሰባት አደጋ ለመዳን በምትታከምበት ጊዜ የሚረዳት ወላጅ ሆነ ደሀና የሆነ ቤተ ሰብ ሰለሌላት ወዳጆችዋን አና ጓደኞችዋን ባለን አቅም አህታችን እናድናት:: አሁን የምትገኝበት በመቀሌ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል(BURN UNIT) ትገኛለች:: እህታችን የቻልነውን ያህል አንድናግዛት ማገዝ ያልቻልን ደግሞ ሼር በማድረግ እንተባበራት::
ይህ የሴቶች ግፍ ደግሞ በካሜላትና በአፀደ ይብቃ!! ፍትሕ ለእህታችን ኣፀደ!
please ....... share ....share ..... share
ምንጭ አህትዋ ፀጋ ንጉሴ
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Alem Brhanemeskel
    Organizer
    Portland, OR

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee