
Help Tigist Fiseha
Donation protected
በአሜሪካን ምድር ጠፍታ ከስድስት ዓመታት በኃላ የተገኘችው ትግስት … አሁንም እንዳትጠፋ ቤተሰቦቿ ሰግተዋል !
ትግስት ፋስሃ ገ/ማርያም (ናንሽ) ትባላለች፡፡ ጎንደር ከታማ ነው ተወልዳ ያደገችው፡፡ ጎንደር ቀበሌ አንድ አምባጅኔ ሰፈር እኔ ሳውቃት በትምህርቷ ታታሪ ጎበዝ ጭዋ ልጅ ሆና ነው፡፡ ጉብዝናዋ ቀጥሎም በጎንደር ዩንቨርስቲ የሊንጉስቲክ የዲግሪ ተማሪ እንድትሆን አብቅቷታል፡፡ ነገር ግን ልትመረቅ ስትል የአዕምሮ ህመም (መተት ተብሎ) ትምህርቷን አቋረጠች ፡፡ ለፍተው ያሳደጓት እናትና አባት በየጸበል ቦታ ይዘው በመንከራተት ፈጣሪ ፈቅዶ ወደ ቀደሞ ጤንነቷ ተመለሰች፡፡ ከተሻላት በኃላም አልቦዘነችም ቤተሰብ ለማገዝና ራሷን ለመቀየረ ስራ በጎሃ ሆቴል ጀመረች፡፡ የማኔጀመንት ዲግሪዋን ከአልፋ ዩንቨርስቲ ስትከታተል ቆይታ ልትመረቅ ስትል የአሜሪካን የዲቪ ሎተሪ ደረሳት፡፡ ጥረ 7 ቀን 2004 ዓ.ም ከ12 ዓመት በፊት ወደ አሜሪካ ምድርም አቀናች፡፡ ዲሲ ከደረሰች በኋላ እሰከ 2007 ዓ.ም ስራ በመስራት ቤተሰቦቿን በመደገፍ ቆይታለች፡፡
ይሁን እንጂ ከ2007 ዓ.ም በኃላ እስከ 2009 ዓ.ም ድረሰ አልፎ አልፎ ስልክ በመደውል ቤተሰቦቿን ከማግኘት ውጭ እየራቀች ነበር፡፡ ክፍተቱ ሰፍቶ ከ2009 ዓ.ም በኃላ ግን ያለችበትን የሚያውቅ የበላትን ጅብ አየሁ የሚል ጠፋ፡፡ ቤተሰብ ተጨበነቀ ወጣ ወረደ… ለስድስት አመታት እናት እንባ አነቡ… በቀን ጨለመባቸው…. አባት በሃዘን አንገታቸውን ደፉ…. ቤተሰብ በሰለጠነ አለም አንድ ልጁን ፈልጎ ለማግኘት ተሳነው፡፡
ከስድስት ዓመታት በኃላ 2015 ዓ.ም ነሐሴ 14 ቀን በቨርጂኒያ ውድስታክ ከተማ መገኘቷ ለቤተሰብ ተነገረው፡፡ በሞት ስላልተቀደሙ ቤተሰብ ፈጣሪን አመሰገኑ ፡፡ ትግስት ስትገኝ ከሰውነት ተራ ወጥታ በሸልተር (መጠለያ) ውስጥ በአንድ ደግ ኤርትራዊ ድጋፍ ቁማ ነበር፡፡ ይህንን የሰሙ ቤሰቦች የሚያግዛቸው ሰው ሲፈልጉ ልበ ብርሃን የሆነውን አማኑኤን ማናዬ ( የሰፈሯን ልጅ) አስቸገሩ፡፡ ከዓመታት መንከራተት መጨነቅ ብቸኝነት በኃላ አይዞሽ የሚላት በርቀትም ቢሆን ሰው ተገኘ፡፡ የመኖሪያ ፍቃድ ዶክመንት ሆነ ፓስፖርት ስለጠፋባት ወደ ሃገሯ ተመልሰ በቤተሰቦች ድጋፍ ከህመሟ እንዳታገግም መውጫ በሩን ቆለፈባት፡፡ ጊዜ ጊዜን እየወለደ ቀናት ወደ ወራት እየተሸጋገሩ ሂዶ የጤናዋ ጉዳይም አሳሳቢ ደረጃ ደረሰ፡፡
ወደ ቨርጂኒያ ሃሪሰንበርግ ከተማ አቀናች እዚያም ከመጠለያ (ሸልተር) ይልቅ የከተማው ጉዳናዎች ተቀበሏት፡፡ ከሰውነት ተራ እየመጣች መጣች እሰይ ተገኘች ያለው ቤተሰብ ለቅሶው እንዴት ከዚህ የሲኦል ኑሮ ትግስትን መታደግ ነበር፡፡
ከወራት በፊት እናቷ ጎንደር በሄድኩበት አገኙኝ … ለአመታት ያፈሰሱትን እምባ ዋጥ አድርገው ማተቤን ያዙት … ብርሃን አሉኝ … ለነፍስ ይሆንሃል ልጄን ለሃገሯ ምድር አብቃልኝ… ስሜቱ እጅግ ከባድ ነበር… ከራሴ ጋር ቃልገባሁ በቻልኩት ሁሉ የእኝህን እናት ፈገግታ ለአንደ ቀን እንኳን ልመልስ፡፡
እናም ትግስትን ካለችበት ሰቆቃ አላቆ ለማምጣት ሚያግዙኝን አሰባሰብኩ በአዲስ አበባ የጎንደር ጎሃ አብሮ አደግ ማህበር አመራሮችን /ጌትሽ ገብረሚካኤል፣ ነፃነት ሁሴን ፣ ቆንጂት ተስፉሁን፣ ይርጋ ገብረ መድን/ ከጎንደር ደግሞ /ጓደኞቸን ሰሎሞን አስርደውና ደጀኑ ንጉሴን/ መረጥኩ፡፡
አሜሪካን ሃገር ከልጅነቷ ጀምሬ የማውቃትን ልበ ቀናዋን ሂወት ታደሰን (የልብ ህሙማን ህፃናትን እና መሰል እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቀድማ የምትደርሰውን መረጥኩ፡፡ እርሷም አላሳፈረችኝ … ቀጠልኩ አማኑኤል ማናየ (ዶክመንቷን በማስተካከል እያገዛት ያለ)፣ ሂደጎ ነጋሽ (ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል)፣ ነፃነት ገዳሙ (አሁን ወደላቸወበት የፀበል ቦታ እንድትገባ ያገዛትና እየደገፋት ያለ) ቀሲሰ ንጋቱ አበበ ፣ጀጃው፣ አዎት፣ ህሩይ ሌሎችንም ስም ያልጠቀስኳቸው አብረወን ሆኑ፡፡
አሁን ላይ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ ገዳም Saint Arsema Ethiopian Orthodox Monastery 2239 Bachmans Valley Rd, Manchester, MD 21102 በነፃነት ገዳሙ እርዳታ ገብታ ትገኛለች፡፡ ነገር ግን የሚያስፈልጋት መጠለያ፣ አልባሳትና ምግብ ሲሆን በፀበል ቦታው ሆኖ የሚያግዛት ሰው ትፈልጋለች፡፡ ይሁን እንጂ ሰው የላትም፣ ገንዘብ የላትም ፣ጤና የላትም፡፡ እናም የእናንተን በጎነት ትፈልጋለች፡፡ አይዞሽ አለንልሽ በማለት ያቅማችሁን በገንዘብ በመደገፍ፣ በሞያ በማማከርና በመሳሰሉት ከጎኗ እንድትቆሙ በፈጣሪ ስም ቤተሰቦቿ ይጠይቃሉ፡፡ ዶክምንቷ ተስተካክሎ ውደ ሃገር ቤት መጥታ የቤተሰቦቿን አይን እንድታይ አግዙን ይላሉ፡፡
ላለፉት ስድስት ዓመታት በምን አይነት የሂወት ውጥንቅጥ ውስጥ እንዳለፈች እርሷና ፈጣሪ ብቻ ነው የሚውቁት ስትናገር ግን እንዲህ ትላለች
• ልጆችእንደነበሯት እና ተቀምታ ለማደጎ እንደተሰጠ
• በሆኑ ሰዎች ታግታ እንደነበር
• የአሜሪካን ዜግነት ተፈትና እንደነበር
• የሚከታተሏት ሰዎች እንዳሉ በዚህም ከቦታ ቦታ እንደምትንከራተት ደጋግማ ትናገራለች፡፡
ትግስትን ለመርዳት የምትፈልጉ donate እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፡፡ የእህቷ ስልክ +25118519315 ማንኛውንም ጥያቴ ተመቀበል፡፡ (ዋትስ አፕ ፣ቴሌግራምና ቀጥታም) መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
ብርሃን ሲሳይ ነኝ እግዚአብሄር ያክብርልኝ ስላገዛችኋት፡፡
Organizer
Amanuel Wubneh
Organizer
Visalia, CA