
Help Masresha get life saving Bone Marrow Transplant
Donation protected
Help Masresha Shumye Get Life-Saving Bone Marrow Transplant
Story:
Hello everyone,
My name is Masresha Shumye, (a.k.a Mimi) and I am reaching out for your help. I have been battling blood cancer for some time now. Despite trying every possible treatment in Ethiopia, including chemotherapy, my condition has not improved.
In fact, the disease is progressing, causing painful swellings and even loss of vision. My doctors have now told me that my best chance for recovery is to get a bone marrow transplant abroad.
Unfortunately, I have exhausted all my savings on treatments and can no longer afford the costs of this critical procedure.
I am humbly, in God's name, asking for your support. Any amount you can donate will bring me one step closer to getting the treatment I need to restore my health and sustain my life and live together with you. If you are unable to donate, please consider sharing my story with others and remember me in your daily prayer.
Thank you so much for your kindness and generosity.
Good bless you all.
Sincerely,
Masresha Shumye
--------------------------------------------------------------------------------
ሰላም ለሁላችሁ፣
ማስረሻ ሹምዬ እባላለሁ ። ላለፉት ጥቂት አመታት በደም ካንሰር ተይዤ ባለ በሌለ ጉልበትና ፅናት ህይወትን መጋፈጥ እጣ ፈንታዬ ሆኗል። ኬሞቴራፒን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዓይነት ህክምናዎች ብሞክርም ህመሜ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበኝ ሄዷል። አሁን አሁን በሽታው ይዘቱን እየቀየረ የሚያሰቃዩ እብጠቶችን በመፍጠር የአይን ብርሃኔን እስከ መከልከል ደርሷል ።
ሀኪሞቼ አሁን ለማገገም ያለኝ የመጨረሻ አማራጭ ወደ ውጭ አገር ተጉዞ የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ማድረግ እንደሆነ ነግረውኛል። እንደ አለመታደል ሆኖ የነበረኝን ሃብትና ጥሪት በሙሉ በሃገር ዉስጥ ሕክምና አሟጥጬ የተጠቀምሁ በመሆኑ እና ለዚህ ህክምና የተጠየቅሁት ወጪ ከፍተኛ ስለሆነ የእናንተን እርዳታ መጠየቅ ግድ ሆኖብኛል።
ስለሆነም በደግነት የምትለግሱት ማንኛውም መጠን ጤንነቴን ለመመለስ የሚያስፈልገኝን ህክምና ለማግኘት በአንድ እርምጃ ያቀርበኛል እና የምትችሉትን በመለገስ ታግዙኝ ዘንድ በፈጣሪ ስም እጠይቃችኋለሁ። ታሪኬን ለሌሎች በማካፈልም የጥሪዬ ተባባሪ እንድትሆኑልኝ እማፀናለሁ። በተጨማሪም ለጸሎት በቆማችሁ ጊዜ እኔን እንድታስቡኝ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።
ስለ ደግነታችሁ እና ልግስናችሁ ፈጣሪ ምላሹን ይሰጣችሁ።
አስተባባሪ፡ አባቴነህ ዓለሙ
ማሳሰቢያ፡
- የጎፈንድሚ ቲፑን ዜሮ ማድረግ ከፈለጉ Enter custom tip የሚለውን በመጫን Tip amount የሚለው ባዶ ቦታ ላይ ዜሮ ያስገቡ::
- ድጋፈዎን በዜል/Zelle በኩል መለገስ ከፈለጉ አስተባባሪውን አባቴነህ ዓለሙን ማነጋገር ይችላሉ::
ከሰላምታ ጋር
ማስረሻ ሹምዬ
Organiser
Abateneh Alemu
Organiser
Boston, MA