Help Kindova Get Hawariat Hospital Critical Medical Items

  • M
  • H
  • Y
23 donors
0% complete

€8,904 raised of €8.4K

Help Kindova Get Hawariat Hospital Critical Medical Items

Donation protected
ይህ የገቢ ማሰባሳቢያ "ኧሰት የበጎ አድራጎት ድርጅት" ምስረታ ሂደት ላይ የተሳተፉ የምሁር አክሊል ወረዳ ተወላጆች የተዘጋጀ ሲሆን ዓላማው በወረዳው ብቸኛው ሆስፒታል ወደሆነው የሐዋርያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በእጅጉ ተፈላጊ የሆኑ የህክምና መሣሪያዎች እንዲጓጓዙና ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነው እንዲተከሉ ለማድረግ ከሚያስፈልገው ወጪ ውስጥ ከፊሉን ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን፣ ድጋፉ ለ"ኪንዶቫ ሂዩማኒቴርያን ኦርጋናይዜሽን" ይላካል።

የህክምና መሣሪያዎቹ ከጥቂት ወራት በፊት የወረዳው ተወላጅና ባሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ በሆነችው ባር አጅየት ዘይዳ ግዛው ዋና አስተባባሪነት፣ በወረዳው የአስተዳደርና የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ ሰጪነትና "ኪንዶቫ ሂዩማኒቴርያን ኦርጋናይዜሽን" በሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጠያቂነት ”ፓርትነርስ ፎር ሄልዝ” ከተባለ የህክምና የበጎ አድራጎት ተቋም ለሐዋርያት 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል የተበረከቱ ናቸው። ቁሳቁሱ ድምር ዋጋቸው 350,000 (ሦስት መቶ ሐምሳ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ሲሆን በ40 ፊት ኮንቴይነር ተሰብስበው ወደ ሆስፒታሉ ለመጓጓዝ ተዘጋጅተዋል።

ቁሳቁሶቹ በወረዳችን ለነፍሰ ጡር እናቶች፣ ለህጻናትና ለአረጋውያን ጨምሮ ለብዙ ተወላጆች ከጤና እክል ፋታ ለመስጠት ብሎም ነፍስ ለማዳን የሚያገለግሉ ሲሆን ጠቅለል ያለው ይዘታቸው የሚከተለው የኪንዶቫ ተቋም ገጽ ላይ ቀርቧል:-


ዋጋቸው 300, 000 የአሜሪካን ዶላር ከሚያወጡ ዘላቂ አገልግሎት ከሚሰጡና በመጠን ከፍ ካሉ እቃዎች በተጨማሪም ኮንቴይነሩ የሚኖረው ክፍት ቦታ ግምታቸው 50,000 የአሜሪካን ዶላር በሚያወጡ አላቂ የህክምና ቁሳቁስ ይሞላል።

ይህንን ድጋፍ በማድረግ የወገኖቻችንን ሕይወት እንታደግ፤ ለብዙዎች በህክምና እጦት ተባብሶ አስከፊ ደረጃ የሚደርስ የጤና እክልም እናስቀር። በተጨማሪም ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚመሰረተው የ"ኧሰት የበጎ አድራጎት ድርጅት" ከጅምሩ የአካባቢውን ተወላጆች በአባልነት፣ በበጎ ፈቃደኝነትና በተለያየ ደረጃ ላቅ ባለ ተሳትፎ አካቶ ማህበረሰቡ በየዘርፉ ያሉበት ችግሮች እንዲቃለሉ ለማድረግ የጀመረውን ራዕይ እንዲያስፈጽም እናግዝ።

እኔ፣ ዮናስ ሰይፉ ሟነንዳ ድጋፍ እየተደረገለት ያለው ሆስፒታል የሚገኙበት ምሁር አክሊል ውስጥ ያደግኩና ትምህርቴን የተከታተልኩ ስሆን፣ ለኪንዶቫ ሂዩማኒተርያን ኦርጋናይዜሽን የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻውን የማስተባብር በጎ ፈቃደኛ ነኝ። የተሰበሰበውን ገቢ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ወደሚገኘው የኪንዶቫ ሂዩማኒተርያን ኦርጋናይዜሽን የባንክ ሒሳብ ደብተር በቀጥታ የባንክ ትራንስፈር ገቢ አደርጋለሁ፤ ገቢውን ወደዚሁ ባንክ ሒሳብ ደብተር የምልከውም እኔው ራሴ ነኝ።

የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ትልቅ ልዩነት የሚያመጣ ስለሆነ ከወዲሁ በማህበረሰቡ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን።

This fundraiser is organized by members of the Mihur Akli Woreda who are participating in the founding of a local NGO called "Esset Charity Organization". It is aimed at covering part of the costs for transportation and installation of much-needed medical supplies to the only hospital in the Woreda, the Hawariat Primary Hospital, and will be sent to Kindova Humanitarian Organization.

The medical equipments were donated a few months ago by the charity organization “Partners for Health” under the coordination of Bar Ajiet Zayda Gizaw, a fellow member of the community currently living in the United States, with the support of the woreda's administration and medical professionals through the request of a humanitarian organization called “Kindova Humanitarian Organization”. The total value of the medical supplies is 350,000 (three hundred and fifty thousand) USD and they are collected in a 40-feet container and readied for transportation to the hospital.

The supplies will be used to provide emergency and basic health care and will save lives and ensure the wellbeing of many residents of our Woreda, including pregnant women, children and the elderly. The following link contains a summary of the medical supplies on the website of Kindova.


In addition to large, durable medical equipment and devices costing 300,000 USD, the open space in the container will be filled with consumable medical accessories, with an additional cost estimated at 50,000 USD.

Let's contribute to saving the lives of people in the area and prevent serious health issues which could be exacerbated by the lack of sufficient medical care. Let’s also help the Esset Charity Organization, which will be founded in a few days time, in mobilizing members of the community to solve the society's problems in many sectors through active membership, volunteerism, and various levels of participation.

I, Yonas Seifu Muanenda, grew up and went to school in the Mihur Aklil Woreda where the hopital being supported is located, and I am a volunteering in this fundraising campaign on behalf of the Kindova Humanitarian Organization. The funds raised will be transferred to the Kindova Humanitarian Organization's bank account in the United States of America using direct bank transfer, and I will be the one who will send the funds to this bank account.

Your contribution to this cause will make a big difference, and we offer our heartfelt gratitude to you in advance on behalf of the community.

Organizer

Yonas Seifu Muanenda
Organizer
Pisa, TC
  • Medical
  • Donation protected

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee