አሥራትን በመደገፍ የህዝብ ድምጽ ይሁኑ/ SUPPORT ASRAT MEDIA

የአሥራት ተደራሽነት እንዲቀጥልና የታፈነው የአማራ ሕዝብ ድምፅ እንዲሰማ አሥራትን ያግዙ!

ውድ የአማራ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን /አሥራት ቤተሰቦች! እነሆ በእናንተ እገዛ አሥራት ከአንድ አመት በላይ ሆነው። ባለፈው አንድ አመት አሥራት በእናንተ እገዛ ከአጣዬና ከሚሴ እስከ ወልቃይትና ራያ በአማራው ላይ የተቃጠውን ጥቃት ለማጋለጥ ሰርቷል። በመተከል፣ በሸዋ፣ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባና በዙሪያው ባሉት ከተሞች አማራው ላይ የተፈፀሙትን በደሎች አደባባይ አውጥቷል።  በየዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቻችን ላይ የተፈፀሙትን ዘግናኝ ወንጀሎች አጋልጧል። በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአማራ አደረጃጀቶችም ድምፅ ለመሆን ጥሯል። ለታገቱ አማራ ተማሪዎች ድምፅ በመሆን እየሰራ ነው። በየከተሞቹ የተደረጉ ሰልፎችንና ሌሎች የአማራ ሕዝብ አቋሞችን በማድረስ ቀዳሚ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

አሥራት ጠንካራና ደካማ ጎኖቹን በመገምገምና በማስተካከል የአማራን ድምፅ በተገቢው መንገድ ለማሰማት ጥረት ማድረጉን ቀጥሏል። በቅርቡም በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኙ አማራዎች ጠቅላላ ጉባኤና የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አቋቁሟል። በቀጣይም የሚስተካከሉትን በማስተካከል፣ መጠናከር  ያለባቸውን በማስቀጠል ይሰራል። ይሁንና አሥራት ለአማራ ሕዝብ ድምፅ ሆኖ እና ጠንክሮ ለመቀጠል የእናንተን እገዛ በእጅጉ ይፈልጋል። ከቴሌቪዥን ስርጭቱ ባሻገር የራዲዮ ስርጭት በመጀመር ለሕዝብ ተደራሽ ለመሆን አቅዷል። በተለይ በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ እንዲሁም ምርጫ ይደረግበታል በተባለ ወቅት የአማራ ሕዝብ የተጣራና ጠቃሚ መረጃ ያገኝ ዘንድ በርትቶ ለመስራት  እገዛችሁን ይፈልጋል።

እናመሰግናለን!

አሥራት ቦርድ

Donations ()

 • Ermiyas Aytenfisu 
  • $100 
  • 53 mins
 • A M 
  • $30 
  • 2 d
 • DMV Amhara Community. United we stand divided we fall. የዲሲና አካባቢው የአማራ ማህበር.  
  • $2,150 
  • 3 d
 • Berhanu Getachew 
  • $30 
  • 3 d
 • Anonymous 
  • $200 
  • 3 d
See all

Organizer

ASRAT MEDIA HOUSE 
Organizer
Seattle, WA
 • #1 fundraising platform

  People have raised more money on GoFundMe than anywhere else. Learn more

 • GoFundMe Guarantee

  In the rare case that something isn’t right, we will refund your donation. Learn more

 • Expert advice, 24/7

  Contact us with your questions and we’ll answer, day or night. Learn more