
የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እድሳት ገቢ ማሰባሰቢያ - ምእራፍ አንድ
Donation protected
የግሸን ደብረ-ከርቤ ቅ/ማ/ቤተክርስቲያን እድሳት - ምእራፍ አንድ
ግሸን ደብረ ከርቤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የተቀመጠበት ታላቅ መንፈሳዊ ታሪክ ያለበት መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በዚህ መንፈሳዊና ታሪካዊ ቦታ ላይ የእግዚአብሔር አብ፤ የእመቤታችን ቅድስት ማርያም፤ የቅዱስ ሚካኤል፤ የቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ኡራኤል አብያተ ክርስቲያናት ይገኙበታል፡፡
የእመቤታችን ቤተክርስቲያን አንድ መቶ አመት የሞላዉ ሲሆን በጊዜ ሂደት ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያት በደረሰበት ጉዳት ማለትም የግድግዳ መሰነጣጠቅ፣ የተሸካሚ ምሰሶዎች መጉበጥ፣የድንጋይ ደረጃዎች መጎዳት፣ የወለል ንጣፍ፣ የኮርኒስ፣ በርና መስኮት መጎዳት ፣በተለያየ ጊዜ የተደረጉ የጥገናና እድሳት ሰራዎች የቅርሱን መሰረታዊ ገጽታ መቀየር የመሳሰሉት ችግሮች ጊዜ የማይሰጡና አፋጣኝ ጥገና የሚያስፈልጋችዉ በመሆኑ ይህ ገቢ ማሰባሰቢያ ተዘጋጅቷል።
ስለዚህ ሁላችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ተረባርባችሁ ለዚህ ለተቀደሰ ተግባር የአቅማችሁን እንድትወጡ ቤተክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
Organizer
Mahibere Teklehaimanot
Organizer
Silver Spring, MD