ESAT Satellite Support Fund

ከመስጠትዎ በፊት ሁለት ማሳሰቢያዎች፤
1) ቲፕ (Tip) ከሚለው መስመር "Other" የሚለውን በመምረጥና በቲፑ ሳጥን ውስጥ "0.00" በማስገባት የእርዳታዎን ገንዘብ ብቻ መክፈል ይችላሉ
2) በ ፔይፓል (PayPal) መክፈል ካልፈለጉ፤ እሱን Step አልፈው በ Credit ና Debit ካርድ መስጠት ይችላሉ

The Ethiopian Satellite TV and Radio is a truly grassroots nonprofit media outlet supported by thousands of subscribing contributors and over 64 support groups in major cities around the globe,  ESAT broadcasts in Amharic, Afaan Oromo, Sidama and Tigrigna languages.

We call upon our supporters and anyone who believes in press freedom to donate to ESAT to boost its capacity in realizing our common dream for a free and prosperous Ethiopia. For the last Ten years, ESAT has been the main source of information to millions of Ethiopians all over the world with you're help we will continue to do so. 

Together, we shall prevail! Long Live Ethiopia and people's!

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) በሀገራችን የነበረው ወደር የለሽ የሚዲያ አፈና የወለደው፣ የአፈና ስርዓትን ከሀገራችን ለማስወገድ የነፃነት ትግል እንዲቀጣጠል ፈር የቀደደ፣ የትግል ሂደቱ ሲቀጣጠልም ትግሉ መስመር ይዞ እንዲሄድና እንቅስቃሴዎቹ እንዲተሳሰሩ የተጋ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የለውጥ ጅማሮ ከታየ በኋላም የለውጡ ሂደት ያለመደናቀፍ እንዲቀጥል በከፍተኛ ሀገራዊ ሀላፊነት ስሜት የሰራ፣ የሀይማኖት ድርጅቶች ሀይማኖታዊ ድፍረት ሲያጋጥማቸውም ከድምፃችን ይሰማ የሙስሊሙ የሀይማኖት ነፃነት ትግል እስከ ዋልድባ የመሬት ዘረፋ የነበረውን የጉልበተኛ አገዛዝ ፅዩፍ ተግባራት ያጋለጠ፣ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ አቅም ካልገደበው በስተቀር ለሁሉም
ኢትዮጵያዊ አይንና ጆሮ ሆኖ በቅንነት ሀገር ያገለገለ ሚዲያ ነው።

በሀገራችን የለውጥ ሂደት ከመጣ በኋላም በየጊዜው የሚከሰቱ ሁከቶችና ግጭቶች ወደባሰ ሀገራዊ ጥፋት እንዳያድጉ ሁሉም በሚመሰክረው መልኩ እጅግ ሀላፊነት በተሞላው ሁኔታ ተንቀሳቅሷል፤ አሁንም እየሰራ ይገኛል። ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሆኖ በአለም ከተከሰተ በኋላም ህዝባችን ስለበሽታው ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኝ በተከታታይ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ያከናወነው ተግባር መጠነ ሰፊ ነው።

ይህ በሁሉም መስክ ለሀገራችን ኢትዮጵያ አስፈላጊ የሆነው ኢሳት ለሀገራችን እስካሁን አስፈላጊ የነበረውን ያህል ወይም ከዚያም በበለጠ በቀጣዩ ጊዜ እጅግ አስፈላጊ ነው። ሀገራችን አሁን ካለችበት ምስቅልቅል እንድትሻገር እንደ ኢሳት ያለ ስለሀገርና ህዝብ ህልውና ብቻ እየተጋ በሀላፊነት የሚሰራ ሚዲያ አስፈላጊ ብቻም ሳይሆን የህልውናም ጉዳይ ነው። 

ስለሆነም ኢሳት እስከዛሬ የዘለቀውና ማስመዝገብ የቻላቸውን ውጤቶች ያስመዘገበው በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉአቀፍ ድጋፍ መሆኑ ይታወቃል። የኢሳት ስራዎች ቀጥለው ለሀገርና ለህዝብ ከትናንቱም የበለጠ ማከናወን ይችል ዘንድ የእርስዎ ድጋፍ እጅጉን አስፈላጊ ነውና ኢሳትን በሚችሉት የገንዘብ መጠን ይደግፉ። ኢሳት ትናንትን የተሻገረውና ነገም የሚቀጥለው የኢሳትን አስፈላጊነት በተረዱ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ነውና በተሻለ አቅምና ተደራሽነት ህዝባችንን እንድናገለግል ዛሬም ኢሳትን እንዲደግፉ ጥሪያችንን እናቀርብልዎታለን።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር

በኢሳት ቦርድ አለም አቀፍ ድጋፍ ማስተባበሪያ

Donations

 See top
 • Addisu Alene 
  • $100 
  • 1 mo
 • tessema getachew 
  • $300 
  • 1 mo
 • Teshome Wordofa 
  • $50 
  • 1 mo
 • Biru Gebremeskel  
  • $20 
  • 1 mo
 • Anonymous 
  • $50 
  • 1 mo
See all

Organizer

ESAT Global 
Organizer
Alexandria, VA
ESAT 
Registered nonprofit
Donations are typically 100% tax deductible in the US.
Learn more
 • #1 fundraising platform

  More people start fundraisers on GoFundMe than on any other platform. Learn more

 • GoFundMe Guarantee

  In the rare case something isn’t right, we will work with you to determine if misuse occurred. Learn more

 • Expert advice, 24/7

  Contact us with your questions and we’ll answer, day or night. Learn more