Main fundraiser photo

London Debre Semayat Medhanealem And St. Gabriel EOTC

"ሕንፃው ግን ለእግዚአብሔር ለእምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው" ፩ዜ መ ፳፱÷፩

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።

ልዑል እግዚአብሔር ድንቅ ነገርን አደረገልን፤ እርሱን የምናመልክበት በስሙ ተሰብስበን የምናወድስበት የምንቀድስበት ቤት ሰጠን ። እንደሚታወቀው ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (ሣልሳዊ) በዩናይትድ ኪንግደም (ሎንዶን) ከተማ በስደት በኖሩበት ወቅት እ/ኢ/አ በ1994 የሎንዶን ስደተኛ ደብረ ሰማያት መድኃኔዓለም እና አምላክ ወሰብዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን አቋቁመው ለምዕመናን አገልግሎት ይሰጡ ነበር ።

የብፁዕነታቸውን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ ተከትሎ ታቦተ ሕግጋቱ በሎንዶን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የኪዳን ፀሎት እና ወርኃዊ የቅዳሴ አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ፤ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አገልግሎቱ እንዲቀጥል በሰጡት መመሪያ መሠረት በአሁኑ ወቅት የዘወትር አገልግሎት የሚሰጥበትን ሕንፃ ቤተክርስቲያን ተከራይተን ዘወትር ቅዳሜ፣ የመድኃኔዓለም፣ የቅዱስ ገብርኤል እና በአበይት በዓላት መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የእግዚአብሔር አምላክ ፈቃዱ ሆኖ በአሁኑ ሰዓት የራሳችን ቤተመቅደስ የሚሆን ህንፃ ቤተክርስቲያን በጨረታ ተወዳድረን ያሸነፍን ሲሆን፤ የመጀመሪያ ቅድሚያ ክፍያ 35 ፐርሰንት በአጭር ጊዜ ውስጥ መክፈል ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ቤተክርስቲያኑን በቀጥታ ለእኛ አምልኮ አመቺ እንዲሆን አድርጎ ለመስራትና በራሳችን ዲዛይን የውስጡን ገጽታ በመከፋፈል መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማህሌት በማዘጋጀት የኦርቶዶክስ ቀኖና በሚፈቅደው የተለያዩ መንፈሳዊ ስርዓት እንዲፈፀምበት የውስጡን ስራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር የተጠቀሰውን ቅድሚያ ክፍያ እና የውስጥ ስራዎችን ለመስራት በአሁኑ ወቅት በቂ የገንዘብ አቅም ስሌለውና የገንዘብ ድጋፍ ስለሚያስፈልገው፤ የእግዚአብሔር በረከት ባደረባችሁ የቸሩ መድኃኔዓልም ልጆች በሆናችሁ ሙሉ በሙሉ በመተማመን፤ ዘመኑ በሚፈቅደው ቴክኖሎጂ በጎፈንድሚ እሱ በልባችሁ ያሳያችሁንና የፈቀደላችሁን እርዳታ ለማድረግ እጃችሁን እንድትዘረጉ ይህን ጥሪ እናቀርባለን።

በፀሎት፣ በእውቀት፣ በሀሳብ፣ በጉልበት፣ በገንዘብና ማቴሪያ በማቅረብ በዚህ መንፈሳዊ በረከት በሚያሰጥ ትሩፋት እንድትሳተፉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።

"በመካከላቹ አድር ዘንድ መቅደስ ይስሩልኝ" ። ዘጸፈት ፪፭÷፰

እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያንችንን ይጠብቅ ።
የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጽ/ቤት
የብፁዕ አባታችን በረከታቸው አይለየን ።


"The work is great, for the palace is not for man, but for the LORD God." (1 Chronicles 29:1)

In the name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, one God—Amen.

Our Most High has performed wondrous works for us; He has granted us a sacred place where we may worship, adore, and honor Him.

In 1994, during the time our beloved shepherd, His Grace Abune Gorgorios (Salsawi), was in exile in London, the churches of Debre Semayat Medhane Alem and Amlak Wesebe Gabriel Church was founded to minister to the faithful.

After the earthly departure of His Grace Abune Gorgorios, the Ark of the Covenant was moved to Debre Genet Holy Trinity Church, where it continued to bless the faithful through morning prayers and monthly Mass. Later, under the wise guidance of His Grace Abune Yakob, Archbishop of the UK and Ireland, the ministry moved into a new church building, where Mass is celebrated every Saturday, as well as on monthly and annual feast days.

In accordance with God's will, our future church building has been secured through a competitive bidding process. An initial deposit of 35% must be paid within a short period, and essential work must be completed to ready the sanctuary for worship. In response, we have prepared and shared an interior design proposal for the building.

For the celebration of the liturgy, the sanctification of the space, the hymnody, and the execution of various spiritual programs—and in light of the financial challenges presented by the advance deposit and the necessary internal work—we, the humble and faithful children of God, trust that you will not forsake us. We humbly seek your support through prayer, knowledge, insight, funds, and materials, and we gratefully rely on the financial assistance provided via GoFundMe.

"And let them make me a sanctuary, that I may dwell among them."
(Exodus 25:8)

May God Almighty protect our church.

The Parch Admin Council
May the blessing of His Grace Abune Gorgorios be with us.

Medhanealem EOTC London is organising this fundraiser under the auspices of the Diocese of United Kingdom & Ireland, on behalf of the London Debre Semayat Medhanealem And St. Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Medhanealem EOTC London
    Organizer
    England
    London Debre Semayat Medhanealem And St. Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
    Beneficiary

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe