
በ2017 ዓ.ም የአቅምዎን በመለገስ አንድ ልጅ ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄድ ያድርጉ!
Tax deductible
“ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።” ምሳ ፲፱፥፲፯
በአሜሪካን ሀገር በቨርጂኒያ ግዛት የተቋቋመው የቅዱስ ዮሐንስ በጎ አድራጎት ማኅበራችን በሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ የኑሮ ችግር ውስጥ ወድቀው የሚገኙ ወገኖቻችንን አቅም በፈቀደ መጠን ለመርዳት የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ማኅበር ነው!
በዚህም መሠረት ማኅበሩ :-
1ኛ- ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና አሳዳጊ የሌላቸውን 25 (ሃያ አምስት) ህጻናት፣
2ኛ- በHIV AIDS ( ኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ) ወላጆቻቸውን ያጡ እና እነርሱም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ 15 አስራ አምስት ህጻናት በድምሩ 40 ( አርባ) ሕጻናትን የዕለት ምግባቸውን የዓመት ልብሳቸውን በመግዛትና ሙሉ ወጪአቸውን በመሸፈን በቋሚነት ያሳድጋል።
በተጨማሪም 80 (ሰማኒያ) ለሚሆኑ አረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መኖሪያ ቤት በመገንባት የውሃ ጉድጓድ በማስቆፈር የዓመት ቀለብ በመግዛት ማኅበሩ ለወገኖቹ አጋርነቱን በመግለጽ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል።
የበጎ አድራጎት ማኅበራችን በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደግሞ አቅም በፈቀደ መልኩ የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር ከ50 -100 ለሚሆኑ ሕጻናት ልብስ ፣ ጫማ ፣ የትምህርት ቁሳቁስ በመግዛትና ተጨማሪ ድጋፍ በመስጠት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ በመሆኑ እርስዎን የወገኖችዎን ችግር በመገንዘብና አቅምዎ የፈቀደውን በማድረግ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዴታዎን እንዲወጡ በድሆች ወገኖቻችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
"መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤" ዕብ 13፥ 16
Organizer
Tilahun Abebe
Organizer
Lorton, VA
Kidus Yohannes Charity Group
Beneficiary