Main fundraiser photo

Dire Dawa Basketball Club

Donation protected
ቡድናችንን ከመፍረስ አድኑት!

Ethiopian Men's Basketball Premier League started last week & Team Dire Dawa Men's Basketball lost two games in a row. One away game with Adama Kenema Men's Basketball Team & one with Wolkitae Kenema Men's Basketball Club@ home court i.e DIRE. And it's very tough & sad indeed. Yet, I salute to my boys for showing them what basketball skill is all about - the dribbles, cross-over etc. and most importantly playing a big game like this without having meals both before & after the game, not adequate sport apparel, salary & budgets. Your love for the game & bravery is immeasurable & amazing.

To all Dire Dawa Basketball fans both here & there, I am literally begging you to help your brothers who are competing in this Ethiopian Basketball Premier League.

Thanks in advance for your support.

————————————————————————

ወጣቶችን መርዳት እራስን መርዳት ነው!!

የኢትዮጲያ ቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ከተጀመረ ድሬ ዳዋ ቅርጫት ኳስ ቡድን ሁለት ጨዋታዎችን አድርጎ ሁለቱንም በተከታታይ ተሸንፏል፡፡ በምንም መልኩ መሸነፍ ይመራል፡፡

ግን ለእኔ ከቡድኑ ሽንፈት በላይ መራራው ነገር - በፕሪሚየር ሊጉ እየተወዳደሩ ካሉት 13 ምናምን የክልል ከተሞችና ክለቦች ውስጥ የድሬ ዳዋ ቅርጫት ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ያለምንም ደሞዝ፣ ጥቅማ ጥቅም፣ ተገቢ የስፖርት ትጥቅ፣ ኧረ በጣም የሚገርመው ከጨዋታ በፊትም ሆነ በኀላ ምግብ እእንኳን የሌላቸው መሆናቸው ከሽንፈቱ በላይ የሚመረው ለእኔ ይሄ ነው፡፡

ባለፈው ዓመት በተካሄደው ተመሳሳይ ውድድር በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ሆነው ተጫዋቾቻችን፣ በሚሊየን በጀት ከተመደበላቸው ክለቦችና የክልል ከተሞች ጋር ተወዳድረው 3ኛ ወጥተዋል፡፡

በጣም የሚገርመው የድሬ ዳዋ ቡድን እነ ጭሮ (አሰበ ተፈሪ)፣ ወልቂጤ ከነማ፣ የካ ክፍለ ከተማ ሳይቀሩ አንድ ሚሊየን (እደግመዋለሁ አንድ ሚሊየን) ብር ገደማ ሲመድቡ የኛዋ ድሬ ዳዋ እስካሁን ለአንድም ተጫዋች አይደለም ደሞዝ እና ተገቢ ትጥቅ መግዛት ከጨዋታ በፊት እና በኀላ ምግብ መመገብ እንኳን አልቻለም፡፡

አስተዳደሩ ለስፖርቱ ያደረገው ድጋፍ ከሌሎች ከተሞች አንፃር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ የድሬ ዳዋ ከነማ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾቹን እንዲያቅፋቸው ሲጠየቅ የሰጠው ምላሽም አሳፋሪ ነው፡፡

ምንም ይሁን ምን ግን እደለመንም ይሁን እየተበደርን - የድሬ ዳዋ ቅርጫት ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ይጫወታሉ፡፡ ቡድኑም አይፈርስም፡፡

በየስብሰባው ለቲሸርት እና ኮፍያ ለማሳተም ሚሊየን ብሮች የሚወጣባት ከተማ ላይ ወጣቶቹ በስፖርት ሰው ለመሆን የሚያደርጉትን ጥረት የሚደግፍ አካል መጥፋቱ ያሳዝናልም/ያስተዛዝባልም፡፡

እንደመውጫ - የፌስቡክ ወዳጆቼ የተቻላችሁን ድጋፍ ለቡድኑ ብታደርጉ ደስተኞች ነን!!

#share #tagyourelf #HELP #DONATE
Donate

Donations 

  • Wondu Mulugeta
    • $50 
    • 6 yrs
Donate

Organizer

Natnael Poupy
Organizer
Alexandria, VA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.