
For funeral purpose
Donation protected
እጅግ የምንወዳቸው ወንድማችን መኮንን አበበ (ራጁ) እና ባለቤቱ እህታችን ሜሮን ታደሰ በጣም በምታሳሳ ሴት ልጅ አምላክ ባርኮአቸው ነበር። ዳሩ ግን የምድር ዘመንዋ በወራት ተወሰነና ሰሞኑን በስጋ ተለይታናለች።
ወላጆችዋ የምታሳሳ የልጃቸውን አይን አይተው፣ ድምፅዋን ሰምተው፣ ገላዋን ዳሰው፣ መአዛዋን አሽተው፣ አቅፈዋትና ስመው ሳይጠግብዋት፣ እንዲህ በቶሎ ስትለያቸው ልብን በሚያፈስ ሃዘን ውስጥ እያለፉ ነው።
ከሃዘናቸው ፈጥኖ አምላክ እንዲያፅናናቸው በፀሎታችን እያስብናቸው። የልጃቸውን አካል በክብር ያሳርፉ ዘንድ ደግሞ የሚጠበቅባቸውን ወጪ ለማገዝ ልብዋ የፈቀደውን እየለገሱ ሃዘናችንና ፍቅራችንን እንገልፅላቸው ዘንድ ወዳጆቻቸው ይህን go fund me ከፍተናል።
ፈጣሪ በፀጋው ያፅናናቸው ለእርሶም ባጎደሉበት ይሙላሎት።
Organizer
Tesfatsiyon Tariku
Organizer
Chicago, IL