Main fundraiser photo

አንከር ሚዲያን ይደግፉ

Donation protected
ሰላም ወገኖቼ

አንከር ሚዲያን ጠንካራና ወቅቱን የጠበቀ የሚዲያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ጉዞ ጀምሯል። ባለፉት ሶስት ወራት አንከር ሚዲያ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ተደማጭነትን ያገኘ ሚዲያ ለመሆን በቅቷል። በአንድ ሰው ጥረትና በተወሰኑ ሰዎች የሞራል ድጋፍ የቆመው አንከር ሚዲያ አሁን ከሚያበረክተው አስተዋጽዖ የተሻለና ተጨማሪ ስራዎችን አካቶ የሚተላለፍበት አቅም ለመፍጠር የኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ከሚፈልግበት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። በሀገር ቤት አሁን ባለው አቅም ለሶስት ባለሙያዎች መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም በኤዲቲንግና በሪፖርቲንግ የቀጠራቸው ሲኖሩ ከኢትዮጵያ የቆዳ ስፋትና በየዕለቱ ከሚስተናገዱት አጀንዳዎች አንጻር በጣም አነስተኛ አቅም እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም አንከር ሚዲያ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ የኢትዮጵያን ጉዳዮች በዜናና በውይይት በማንሳት ህበረተሰቡን ለማገልገል እንዲችል የእናነተን ድጋፍ ይፈልጋልና በምትችሉት የገንዘብ መጠን እንድታግዙት በኢትዮጵያ ስም እንጠይቃለን።
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Mesay Mekonnen
    Organizer
    Alexandria, VA

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee