✨ Help Build a New Tewahedo Sanctuary: Debre Genet St. Michael Church in Columbus, OH: Preserving Our Faith for Generations ✨
Debre Genet Saint Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Columbus, OH, has grown to over 200 active members and 80+ children in our faith program. But our current building can no longer support our spiritual family.
The Urgent Need for Change:
● Members stand outside during prayer due to lack of space.
● Children are forced to learn their faith in the parking lot.
● Our current site has persistent flooding, insufficient parking, and cannot accommodate necessary expansion for our worship and education needs.
Our Vision: A New Spiritual Center on 10 Acres We have secured a promising new 10-acre location to create a vibrant spiritual home that reflects the glory of our Tewahedo tradition. Your donation will help us build:
● A spacious sanctuary for worship and fellowship.
● Indoor classrooms to nurture our children.
● A center for community celebrations like ጥምቀት (Epiphany) and a sacred ገዳም (monastery) for prayer and retreat.
This is a sacred journey to build a house of worship, a center of education, and a home that will safeguard our heritage for future generations.
We humbly ask for your prayers and support to make this vision a reality. Every donation, no matter the amount, lays a stone in this holy place.
✨ Let's build a sanctuary that reflects our Tewahedo tradition and glory! ✨ (የተዋሕዶ እምነት ሥርዓታችንንና ትውፊታችንን የሚጠብቅ ቤተ መቅደስ በጋራ እንገንባ!)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤፤ መጽ ነህ ፪፥፳
ችግራችንን ተረድተው ወደዚህ ድኅረ ገፅ ስለመጡ በልዑል እግዚአብሔር ስም ከልብ እናመሰግናለን፤፤
ይህ የምንገለገልበት ቤተክርስቲያን ከምዕመናን ቁጥር በላይ መሆን፤ ልጆቻችንን በእድሜና በክህሎታው ከፋፍሎ ለማስተማር አለመቻል ፤ መዘምራን መዝሙር የሚያጠኑበት፤ ልብሳቸውን የሚቀይሩበት አለመኖር፤፤ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ምዕመናን ውጪ ሆነው ለመከታተል ቢምክሩም በተለይ እንደዚህ በሚበርድበት ጊዜና በበጋ ሀይለኛ ሙቀት የማይታሰብ ነው፤፤ እንደዚህ ያጋጠመው ምዕምን ድጋሚም ላይመለስ ይችላል፤፤ ካህናቱ ፤ ዲያቆናቱና መዘምራን ወረብ በሚያቀቡበት ጊዜ እየተገፋፉ ነው፤፤ የቤተክርስቲያኑ A/C ለማስተካከል ብዙ ጥረት ቢደረግም ሌሊት ላይ በጣም ይቀዘቅዛል፤ ቅዳሴ ሰዐት ላይ ደግሞ ሙቀቱ ከፍተኛ ይሆናል፤፤ መፀዳጃ ቤት ቤተክርስቲያኑ የለውም ብሎ መናገር ይቻላል፤፤ የቤተክርስቲያኑ ውሃ ከጉርጎድ የሚገኝ ሲሆን ለመጠጣት ፤ እቃ ለማጠብ፤ምግብ ለማብሰል መዋል አይቻልም፤፤ ለንግስና ለተለያዩ የምግብ ዝግጅቶች ውሃ ከገበያ ገዝተን ተሸክመን እያመላለስን ነው የምናሰዳው፤፤ ከውጭ በኩል ደግሞ በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ካለመኖሩም በላይ የመኪና ማቆሚያው ትንሽ ዝናብ ከዘነብ ውሃ ኳትሮ መኪና አያስቆምም፤፤ ለመምጠጥ ቢሞከርም ትርፉ ድካም ብቻ ነው የሆነው፤፤
የእርስዎ ልግስና ከዚህ በታች ለተጠቀሱት አገልግሎቶች ይውላል፤፤
ቤተ መቅደሱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት ለማስተካከል፤፤፫ ጉልላቶችን በኢትዮጱያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህንፃ አሰራር መሰረት ለመትከል፤፤ጣሪያውን በሮችንና መስታወቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመቀየር፤መኪና ማቆሚያውን ለማደስ፤ ለአዳሪ አብነት ትምህርት ቤት የህፃናትን አስተዳደግ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማቋቋሚያ፤ ለመጠመቂያ፤ለፀበል ቦታ ፤ ምዕመናን ሱባዔ በሚይዙበት ጊዜ ለማረፊያ የሚውሉ ክፍሎች ለማደስ/ለመስራት፤ በየሳምንቱ ቅዳሜ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሙሉ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የታሰበውን ሐሳብ በቅርቡ ለማከናውን ያስችላል፤፤ ከዚህም በተጨማሪ ለሰውነት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያነት የሚያገለግሉ (የእግር ኳስ፤ ቅርጫት ኳስ፤ የእጅ ኳስ፤ የሩጫ) ሜዳዎችን ለማሰናዳት፤፤
Co-organizers4
S
Saint Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Beneficiary




