Main fundraiser photo

Abdi's Family Fundraising

Donation protected
የወንድማችን የአብዲ ቤተሰቦችን ይርዱልን

ወንድማችን አብዱራዛቅ ኢብራሂም በአካባቢያችን በሚታወቅበት መጠሪያ ስሙ "አብዲ" ብለን በመጥራት ቤተሰቦቹ
ያልተቆጠበ ድጋፋችሁን የሚፈልጉበት ድንገተኛ ሁኔታ ላይ መገኘታቸውን ስንገልጽ ሐዘን እየተሰማን ነው :: አብዲ ለረጅም
ጊዜ በሳን ሆዜ ከተማ የኖረ ባለትዳርና የሁለት ዐቅመ ሔዋን ያልደረሱ ቆንጆ ሴት ልጆች አባት ነው :: ሁሌም ልጆቼን ለቁም
ነገር ባደረስኩ ነበር የእየዕለት ምኞቱና ሕልሙ ::

በሌላ በኩል ደግሞ አብዲ በሚኖርበት አካባቢ ሕብረተሰብ ውስጥ በሚያደርገው የነቃ ተሳትፎ የታወቀና ለፍትህ
ሲታገል የኖረ ግንባር ቀደም እንዲሁም ብዙዎችን አስፈላጊ በነበረበት ጊዜ የረዳ አርአያ የነበረ ወንድም ነው :: አብዲ ኢሳት
(የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራድዮ ) ሲቁአቁም በሚኖርበት አካባቢ በነበረው ኮሚቴ በንቃት ከመሳተፉ ባሻገር ጌዜና
ገንዘቡን በመስጠት ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደረገ ወንድማችን ኢሳትን እሳት ካደረጉት አንዱ ነበር :: አብዲ በአካባቢውም
አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን የሚመለከቱ ስብሰባዎችን ከመሰሎቹ ጋር በማዘጋጀት ገንዘቡን የቸረ ጊዜውን የሰጠ አገር
ወዳድ ወገን ነው :: በበርካታ ሕዝባዊ ሰልፎች የተሳተፈና ድምጹን ከፍ አድርጎ ለአገሩ ያሰማና የጮኸ ቆራጥና ከግንባር ቀደም የትዕይንተ-ሕዝብ መሪዎቹ አንዱ ነበር :: በአሜሪካ ፐብሊክ ራዲዮ ጭምር ስለአገሩ ኢትዮጵያ የሞገተ ደራሽ ልጅዋ ነው ::
በአሁኑ ወቅት ግን ባጋጠመው ከፍተኛ የሆነ የጤና እክል ሳና ክላራ ካውንቲ የሕክምና ማዕከል ICU ከገባ ቀናት
ተቆጥረዋል:: ራሱን ከሳተም ሳምንታት እየተቆጠሩ ነው :: የአምላካችን ተአምር ካልጎበኘው በስተቀር የመዳን ተስፋውም እጅግ የተመናመነ እንደሆነ ሐኪሞቹ ይገልጻሉ ::

ይህ በእንዲህ እንዳለ አብዲ የቤተሰቡ ዋነኛ የገቢ ምንጭ በመሆኑ ባለቤቱና አቅመ ሔዋን የልደረሱት ሁለት ልጆቹ
ከፍተኛ ችግር ተደቅኖባቸዋልና ወዳጆቻቸውንና የአገራቸውን ዜጎች ዕርዳታ ከመጠየቅ ሌላ አማራጭ ለጊዜው አላገኙም ::
አብዲን በማስታመም ላይ ስለሆኑ ምንም የተለየ ለዕለታዊ ኑሮ የሚሆን ጥሪት የላቸውም ::
ሰለሆነም ይህንን መልዕክት ለወገን ሁሉ እንዲደርስ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት እየጠየቅን በበኩልዎም አቅምዎ
የፈቀደውን በመርዳት እጅዎን እንዲዘረጉ ኮሚቴው በትህትና ያሳስባል :: በፀሎትዎም ቤተሰቡን እንዲያስቡ በማክበር
ልናስታውስዎት እንወዳለን::

የሚሰጡት ዕርዳታ በሙሉ ለአብዲ ቤተስብ ማለትም ሁለቱን ልጆቻቸውን ለያዘችው እናትና ባለቤቱ ወ /ሮ ትርሲት
አስፋው በቀጥታ እንዲደርስ የሚድረግ መሆኑን እናረጋግጣለን ::
ኮሚቴው:


Please Help Support Abdi's Family

Brother Abedurezak Ebrahim affectionately known as Abdi to those around him, needs his community’s support. Abdi lives in San Jose, California, with his wife Tirsit Asfaw and their two beautiful young daughters. Abdi has been a pillar of his community in the Bay Area for many years, always willing to go the extra miles whether in his pursuit of social justice or providing help for those in need.

Abdi was one of the active community members who unreservedly participated in the Bay Area ESAT (The Ethiopian Satellite Television and Radio) committee and contributed during its critical needy days. He was one of the front runners in organizing public meetings regarding Ethiopia in the Bay Area, volunteering his time and resources. There was a time he appeared on Public radio to defend his loved country Ethiopia.

As a result of serious medical complications, he is currently in a coma in the Santa Clara Valley Medical Center ICU in San Jose. His doctors have informed his family that his treatment requires extended in-patient hospitalization due to his complex and life-threatening condition.

Abdi is the primary source of income for his family, and due to his condition, he cannot provide that support. As his family, friends and extended community members, we hope to help alleviate some of the financial burdens from his family during this stressful time. Therefore, we are asking his community to the fundraiser to help offset expenses for his family.

We kindly ask you to share this message with your friends and relatives. We also invite you to support Abdi's family with prayers and resources. Your donation is greatly appreciated and all funds contributed will be directly given to his spouse Tirsit Asfaw who is caring for their two daughters.

Organizing Committee:
1. Zenebe Asfir
2. Dawit Asfir
3. Daniel Asfaw
4. Belay Birhane
5. Hussien Desta
6. Mekbib Siamergne
7. Seble Jimma
8. Dr. Demissie Oluma
9. Melesse Moges
Donate

Donations 

    Donate

    Co-organizers (7)

    Melesse Moges
    Organizer
    San Jose, CA
    Tirsit Asfaw
    Beneficiary
    Zenebe Asfir
    Co-organizer
    Dawit Asfir
    Co-organizer
    Daniel Asfaw
    Co-organizer
    Demissie Oluma
    Co-organizer

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee