Main fundraiser photo

አደባባይ ሚዲያ-Adebabay Media- ኑ!ለሀገራችን ኢትዮጵያ አብረን እንቁም

Donation protected
አደባባይ ሚዲያ በኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሀይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ዜናዎች፣ ሐተታዎች፣ ዘገባዎች እና ዶኩመንታሪዎችን በላቀ ጥራት እና በብዙ ባለሙያዎች ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ማቅረብን ተልእኮው ያደረገ ለትርፍ ያልተቋቋመ (Nonprofit) ድርጅት ነው። በዚህ ዘመን መልካም ሕብረተሰብ ለመፍጠር ሚድያ ወሳኝ ሚና አለው። አደባባይ ሚድያ በወገንተኝነት ላይ የተመሠረተ፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት እውቀት እና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ የሆነ ባለ ብዙ ቋንቋና አማራጭ የሆነ ሚድያ ሆኖ የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ (nonprofit organization) የሚድያ ተቋም ነው።

ግባችን ሀገራችንና ሕዝቦቿን የሚጠቅም ሁሉን አቀፍ፣ ሚዛናዊ መረጃና «የነጠረ እውነታ» ማቅረብ፣ በሀገራችን ስለሚደረገው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ» ኢኮኖሚያዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ለማንም ያልወገነ መረጃ በተለያየ መንገድ ማቅረብ ነው። ሥራ ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ነጻ የሕብተረሰብ በይነ-መረብ (internet) ወይም የማኅበረሰብ ትስስር መገናኛ መንገዶችን (Social Media) በመጠቀም የተለያዩ ዝግጅቶችን አደባባይ ሚድያ ስናቀርብ ቆይተናል። ይሁን እንጂ በፌስቡክ እና በዩ-ቲዩብ ብቻ ተወስኖ መረጃዎች ማስተላለፍ በቂ አይደለም።  

“የሁላችንም ስለሆነች ኢትዮጵያ በአደባባይ እንዘግባለን” የሚል መሪ መርህ ይዘን በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ለሌሎችም የዓለም ማኅበረሰብ ለመድረስ ዘመኑ የሚፈቅደው መገናኛ ዘዴዎችን ሁሉ ለመጠቀም የገንዘብ አቅም ውሱንነት አለብን። በሀገራችን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ተመልካቾቻችን በሳተላይት ቴሌቭዥንዝግጅታችንን ለማድረስ ዓላማችንን የተረዳችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ በጎ ሕሊና ያላችሁ ወገኖቻችን ሁሉ የቻላችሁን ያህል አስተዋጽዖ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።


አደባባይ ሚዲያ
(+1) [phone redacted]
[email redacted]
www.adebabay.com
በሁሉም ማኅበራዊ ድረ ገጾች
@AdebabayMedia ቢሉ ያገኙናል።

Donations 

  • Olympia Zeleke
    • $30 
    • 3 yrs
  • Anonymous
    • $100 
    • 3 yrs
  • Shimelis Markos
    • $100 
    • 3 yrs
  • Eshetu Tesema
    • $100 
    • 3 yrs
  • Anonymous
    • $50 
    • 3 yrs

Organizer

Ephrem Eshete Ephrem
Organizer
New Braunfels, TX

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.