Abune Gebre Menfes Kidus Gedam Fund

  • G
  • z
  • S
38 donors
0% complete

$3,305 raised of $50K CAD

Abune Gebre Menfes Kidus Gedam Fund

Donation protected

የቀደሌት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አጭር ታሪክ እና  የግንባታ ዕቅድ ዘገባ

https://abunegebremenfeskidusgedam.wordpress.com/

ይህ ታላቅ ገዳም በላስታ ወረዳ ውስጥ ከቅዱስ ላሊበላ ከተማ በምስራቅ በኩል በግምት በአሥራ ስምንት ኪ.ሜ ከቅዱስ ነአኩቶላብ በምሥራቅ አቅጣጫ በአሥራ ሁለት ኪ .ሜ ርቀት ከእመኪና ልደታ ማዶ ለማዶ የሚገኝ ታላቅ ጥንታዊ ገዳም ነው ።

የገዳሙ አመሰራረትን በተመለከተ ሶስት ቅዱሳን አባቶች አባ ዮሐንስ  ከደብረዋላ ፣ አባ ተንስኣ ክርስቶስ ከአእሩገ ደብር እና አባ ታዴዎስ ከደብረ አንምባ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ተገናኝተው በሰባተኛው ክፍለ ዘመን ገዳሙን መስርተዋል ።

ቦታው ቀደሌት የተባለበት ምክንያት አባ ታዴዎስ ከደብረ አንምባ ወደ አባ ዮሐንስ ዘወትር እየመጡ ቡራኬ ይቀበሉ ስለ ነበር ሲመጡ እና ሲሄዱ የአካባቢው ሰው ስለማያያቸው ኵደሌት አሉአቸው በዚህ ምክንያት ቦታውም ቀደሌት እየተባለ መጠራት ጀመረ ።

በዘመኑ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ነገስታት ስራቸው የተቃና እንዲሆን ከገዳሙ እየመጡ ከቅዱሳን አባቶች ቡራኬ እየተቀበሉ ይሄዱ ነበር ። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ከገዳሙ በላይ በኩል የሚመጣው ጎርፍ በቅርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረስ እና የቅዱሳኑ አጽም ሳይቀር እየፈለስ በአሳዛኝ ሁኔታ በጎርፍ ታጥቦ እየተወሰደ ይገኛል ፤ በገዳሙ አካባቢ የሚኖሩ አብዛኛዎቹ ህዝቦች ከቦታው እየለቀቁ ሙቅውሃ ወደተባለችው ትንሽ የገጠር ከተማ እየፈለሱ በመሄዳቸው ምክንያት ቦታውን የሚንከባከበው እና ከጉዳት የሚታገደው አካል አልተገኘም ፣ በዚህ ምክንያት እድሜ ጠገብ የሆኑ ባለታሪክ ቦታዎች እንዲህ እየፈራረሱ ዝም ብሎ መመልከት ፣ በአንድ በኩል የታሪክ ምንጭ የሆኑ ቦታዎችን ማጣት እና ታሪክ አልባ መሆን ሲሆን ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ዘመን ጸበሉ ብዙ ገቢረ ታምራትን የሚያደርግ ጥንታዊ ገዳም ማጣት በእግዚአብሔር ዘንድ የቤተ ክርስቲያንን ልጆችን ከተጠያቂነት አያድነንም ።

የገዳሙ ሰበካ ጉባዔ የችግሩን አሳሳቢነት ተመልክቶ የህንጻ ኮሚቴ በማዋቀር የአጭር እና የረጅም ግዜ እቅድ በመንደፍ መንቀሳቀስ ከጀመረ ጥቂት አመታትን አስቆጥሯል ፣ በሕንጻ ኮሚቴው እቅድ መሰረት ግንባታው ከታች በተዘረዘሩት ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን ፣ እነሱም

በዋሻው ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ የሚፈሰውን የወንዝ ውሃ አቅጣጫ ማስቀየር
በውሃ የተጎዳውን የዋሻውን ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ደጋፊ ግንብ ( ሪቴኒንግ ሆል ) መገንባት
የዋሻ ቤተ ክርስቲያኑን አካል ፣ ፊት ለፊት የሚገኘውን ክፍል በግንብ መሸፈን
ሲሆን በዚሁ እቅድ  መሰረት ከብዙ እልህ አስጨራሽ ድካም እና ውጣ ውረድ በኃላ ፣ በቅድሚያ ትኩረት እና አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ ለሚገባው ፣  በገዳሙ ላይ ትልቅ ጥፋት በማስከተል ላይ ያለውን ፣ ከገዳሙ በላይ  በኩል የሚመጣው ጎርፍ በቅርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረስ እና የቅዱሳኑ አጽም ሳይቀር እየፈለስ በአሳዛኝ ሁኔታ በጎርፍ ታጥቦ ይወሰድ የነበረውን ፣ በአካባቢው ተወላጅ የማህበረስብ ክፍል እና በበጎ አድራጊ ክርስቲያኖች ያላሰለሰ እርዳታ የወንዙ ውሃን አቅጣጫ ለማስቀየር ተችሏል ።

ቀሪዎቹን ሁለት ዋና ዋና ግንብታዎች ለማከናወን ማንኛውም ኢትዮጵያውያን በውጭ ሀገር እና በአገር ውስጥ የሚኖሩ ፣ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ቅን አመለካከት ያላቸው ወገኖች በሙሉ የችግሩን አሳሳቢነት ተገንዝበው ይረዱናል በማለት ኮሚቴው በቅዱስ ላሊበላ ከተማ የባንክ አካውንት ከፍቶ እንቀስቃሴ ላይ ይገኛል ። በመሆኑም የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ልጆች እና ወዳጆች  የሆናችሁ መዕመናን እና የዚህ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ስፍራ ባለቤት ነን የምትሉ ኢትዮጵያኖች በሙሉ ፣ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም መንፈሳዊ ትብብራችሁን እድትለግሱ ፣ ከበረከቱ እድትሳተፉ ፣ የጻድቁ በረከት አይለያችሁ ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለስጋችሁ ፈውስ ፣ ለነፍሳችሁ ዋስ ይሁናችሁ በማለት ፣ አባቶች እና የአካባቢው ማህበረሰብ  ይማጸኗችኃል ።

የፕሮጀክቱ አዘጋጅ ;- የቀደሌት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የጥገና ኮሚቴ
አድራሻ :- ላስታ ወረዳ ቀደሌት

የቀደሌት  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ባንክ አካውንት ቁጥር ;- 1000192001963 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ;- 0333360082 / 0911553276 ወይም 0910217651 / 0913447862 / 0911083158 / ይደውሉ

የገዳሙ የህንጻ ጥገና አስተባባሪ ኮሚቴ
ወስባት ለእግዚአብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

Organizer

Aden Juzepe Pipino
Organizer
Vancouver, BC
  • Faith
  • Donation protected

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee