- K
- E
*ኑ የኢትዮጵያን ተስፋ በባሕር ዳር እንገንባ!
*ራዕያችን እውን ሊሆን ጥቂት ቀርቶናል!
በኢትዮጵያ እምብርት፣ በውቧ እና ታሪካዊቷ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ ታላቅ መንፈሣዊና ታሪካዊ ለውጥ እየተካሄደ ይገኛል። የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ለበርካታ ዓመታት መንፈሣዊና ትምህርታዊ የሆኑ ታላላቅ ተቋማትን ሲገነባ ቆይቷል። ይህ በወረቀት ላይ ያለ ዕቅድ ብቻ አይደለም፤ 90% የሚሆነው የግንባታ ሥራ ተጠናቋል።* አዎ! ራዕያችን በሥጋ ተገልጧል!
በታሪክ መድረክ
+ የመጀመሪያው የግዕዝ ዩኒቨርሲቲ ፣
+ ጥንታዊ መጻሕፍትና ቅርሶች የሚቀመጡበት ቤተመጻሕፍትና ቤተ መዘክር፣ እንዲሁም
+ ታሪካዊቷና ባለግርማ ሞገሷ የጽርሐ ጽዮን ማርያም ገዳም በአካል ቆመው ይታያሉ።
አሁን የቀረውን 10% አጠናቅቀን ነፍሳት የሚድኑበት፤ የተጨነቁ እረፍት የሚያገኙበት፣ ያዘኑ የሚጽናኑበት ባለ ራዕይ የሆነውን ታላቋን ጽርሐ ጽዮንን ለመጨረስ የእርስዎ ድጋፍ ያስፈልገናል።
የመጨረሻው 10%፡ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ
በአሁኑ ወቅት እነዚህን ሕንጻዎች ለአገልግሎት ዝግጁ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ውብ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ በሆነው የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። የእርስዎ ልግስና በቀጥታ ለሚከተሉት ተግባራት ይውላል፦
• ለገዳሙ በሮች እና መስኮቶች፡ ቅዱሳን ቦታዎቻችን አስፈላጊው ጥበቃና ደህንነት እንዲኖራቸው ለማድረግ።
• ቅዱሳት ሥዕላት እና ጥበባት፦ የቤተክርስትያንን አስተምህሮ የሚገልጹ፣ የስነ ሥዕልና ስነ ቅርጽ ትውፊታችንን የሚያንጸባርቁና ቅርሳችንን ለመጭው ትውልድ የሚያስተላልፉ የመጨረሻዎቹን የቤተ ክርስቲያን የሥነ-ጥበብ ሥራዎች ለማከናወን።
• የውስጥ ሥራ ማጠናቀቂያ ሥራዎች፦ ሕንጻዎቹ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆኑ የሚያስፈልጉ የቀለም፣ የወለል ንጣፍ (Floor) እና ሌሎች መዋቅራዊ የማጠናቀቂያ ሥራዎችን ለመፈጸም።
• የግቢ ውበት (Landscaping)፦ የገዳሙን ቅጥር ግቢ በተለያዩ እጽዋት፤ ምንጣፎችና ማረፊያ፣ መጸለያ ቦታዎች ለማስዋብና ለዐይን ማራኪ ለማድረግ።
ከበረከቱ ይሳተፉ፤ የዚህ ታሪካው ሥራ ባለቤት ይሁኑ፣ አሻራዎን ያሳርፉ!
- በዓለም አቀፍ የሦስት ቀናት የቀጥታ ስርጭት መርኅ ግብር ላይ ይሳተፉ፣ በዚህ ጎፈንድሚ ያለገደብ ይለግሱ ለሌሎችም እንዲደርስ ሊንኩን ያሰራጩ!
በመጪው ዓርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚተላለፍ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት (Live-Stream) ይኖረናል። ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ይህንን ቀሪ ክፍተት ለመሙላት በባሕር ዳር ይታደማሉ።
ጥሪያችን ለእርስዎ ነው፤ ድጋፍ በማድረግ ብቻ ሳይሆን የዚህ ታሪክ የበረከት ሥራ አካልና አጋር በመሆን አብረውን ይቁሙ። በገንዘብዎ፣ በሙያዎ ወይም በጸሎትዎ ያግዙ—ለቀሪው 10% ስኬት ቁልፉ እርስዎ ነዎትና።
እነዚህ በሮች በመጨረሻው ጥረት ማነስ ምክንያት ተዘግተው እንዲቆይ አይፍቀዱ። ለበሮቹ መከፈት ምክንያት ይሁኑ!
"የእናታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት ተራዳኢነት አይለየን። አሜን።"
**Building Ethiopia’s Future in Bahir Dar
*The Vision is Real!
In the heart of Ethiopia, a historic transformation is taking place. The Bahir Dar Diocese has spent years building a network of spiritual and educational landmarks. This isn't just a plan on paper—*90% of the work is already done. Now, we need your help to cross the finish line and finish the remaining 10%.
The roofs are on. The vision is alive. Institutions like the first-ever Ge’ez University, a Diocesan Museum and Library for ancient artifacts, and the historic, majestic Tsirha Tsion Mariam Monastery are already standing.
*The Final 10%: The Finishing Phase
We are currently raising funds for the most critical stage: making these buildings functional, secure, and beautiful. Your donation will go directly toward:
Monastery Doors & Windows: Providing essential security and protection for our holy sites.
Sacred Icons & Art: Commissioning the final ecclesiastical artwork that defines our heritage.
Interior Finishing: The final paint, flooring and structural touches required to open the doors to the public.
Landscaping: For the beautification of the sacred compound.
Join Our Global 3-Day Live Event
This coming Friday, Saturday, and Sunday, we are hosting a global Live-Stream Event. Archbishops, scholars, and artists are gathering in Bahir Dar to bridge this final gap.
We are calling on you—not just to donate, but to become a partner in history. Whether through financial support, professional skills, or your prayers, you are the key to the final 10%.
*Don’t let these doors stay closed for lack of a final push. Be the reason we open them.
*
"May the intercession of our Most Holy Mother, the Virgin Mary, and the assistance of the righteous martyrs be with us all. Amen."
Organizer
Tsireha Tsion Kidist Mariyam Gedam EOTC
Beneficiary





