Foto principal de la recaudación de fondos

የአገር ሕልውናን ለማስከበር ለተጎዱ ወገኖቻችን እንድረስ!

Deducible
ማሳሰቢያ፤  እርዳታ በሚያደርጉበት ጊዜ ቲፕ መክፈል አይኖርብዎትም። ጎፈንድሚ ሰርቪስ ከሚለው ስር  የሚያዩትን አስራ ሁለት ነጥብ አምስት ፐርሰንት የሚለውን ወደ ዜሮ ፐርሰንት መቀየር ይኖርብዎታል።
===================================================
አሸባሪ የጥፋት ኃይሎች እና ግብረ አበሮቻቸው በከፈቱት ጦርነት ምክንያት በተለይ በአማራ እና አፋር ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የጦርነት ሰለባ እየሆኑ፣ ሰብዓዊ መብታቸው እየተረገጠ፣ ሃብታቸው እና ንብረታቸው እየወደመ፣ የዕለት ጉርሳቸው ሳይቀር እየተዘረፈ፣ አሰቃቂ ወንጀል እና ጅምላ ጭፍጨፋ እየተፈጸመባቸው ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያም በውስጥም በውጭም በሚደርስባት ጫና የሕልውና አደጋ ተደቅኖባት በከባድ እና ታሪካዊ ፈተና ዉስጥ ትገኛለች፡፡ ወገኖቻችን ተገደው በገቡበት ጦርነት ምክንያት ውድ እና ክቡር የሆነውን ህይወታቸውን እየሰዉ እና የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው ሲሆን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው ያለ መጠለያ እና ምግብ፣ በረሃብ፣ በበሽታ እና በዕርዛት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ እኛም በዓለም ዙሪያ የምንገኝ ትዉልደ ኢትዮጵያን በሃገራችን እየሆነ ያለው የሰላማዊ ሰዎች እልቂት፣ ስደት፣ የወገኖቻችን ስቃይ እና መከራ እንዲሁም የአገራችን ሕልውና እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመውደቁ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተውና ብሔራዊ ሕልውናን በማስቀደም ለወገኖቻችን ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያደርገው በጋራ በመቆም ደጀንነታችንን በተግባር ለማሳየት የዓለምአቀፍ ትብብር  ለኢትዮጵያ ሕልዉና የተሰኘ ግብረ ኃይል አቋቁመን እንቅስቃሴ ጀምረናል። 

ወገኖቻችን ይህን ከባድ ጊዜ መሻገር እንዲችሉ እና በአገራችን ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ በጋራ ለመመከት የሁላችንም የገንዘብ እና የሞራል ድጋፍ እንዲሁም ለአገራችን ጠበቃ መሆን (Advocacy) በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበን ይህንን የወገን እርዳታ ጥሪ ሁላችንም እንድንቀላቀል ግብረ ኃይሉ ከታላቅ አደራ ጋር ተማጽኖ ያቀርባል፡፡ ስለዚህ በተዘጋጀው ድጋፍ መሰብሰቢያ (GoFundMe) ዛሬ ነገ ሳንል የምንችለውን እየለገስን የወገኖቻችንን ጥሪ እንድንመልስ እና ለሃገራችን ጥብቅና እንድንቆም ጥሪያችንን በአክብሮት እያስተላለፍን ለምታደርጉት ወገናዊ እርዳታ በቅድሚያ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ኢትዮጵያ በነጻነቷና በአንድነቷ ፀንታ ለዘለዓለም ትኑር!

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ሕልውና ግብረ ኃይል
Donar

Donativos 

    Donar

    Organizador

    Global Alliance for the Rights of Ethiopians
    Organizador
    Rancho Cordova, CA
    GARE Global Alliance for the Rights of Ethiopians
    Beneficiario

    Un sitio fácil, eficaz y de confianza donde encontrar ayuda

    • Fácil

      Dona de forma rápida y sencilla

    • Eficaz

      Envía ayuda a la gente y a las causas que te importan

    • De confianza

      Nuestro equipo de seguridad trabaja sin descanso día y noche para proteger a nuestra comunidad.